ኢሳይያስ 50

የእስራኤል ኀጢአትና የእግዚአብሔር ባሪያ ታዛዥነት

1 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤

“እናታችሁን የፈታሁበት

የፍቺ ወረቀት የት አለ?

ወይስ እናንተን የሸጥኋችሁ

ለየትኛው አበዳሪዬ ነው?

እነሆ፤ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤

ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁ ተፈታለች።

2 በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም?

በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ?

ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ አጥራ ነበርን?

እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን?

እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤

ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤

ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤

በጥማትም ይሞታሉ።

3 ሰማይን ጨለማ አለብሰዋለሁ፤

ማቅን መሸፈኛው አደርጋለሁ።

4 ልዑልእግዚአብሔርየተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤

ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤

በየማለዳው ያነቃኛል፤

በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።

5 ልዑልእግዚአብሔርጆሮዬን ከፍቶታል፤

እኔም ዐመፀኛ አይደለሁም፤

ወደ ኋላም አላፈገፈግሁም።

6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣

ጢሜን ለሚነጩ ጒንጬን ሰጠሁ፤

ፊቴን ከውርደት፣

ከጥፋትም አልሰወርሁም።

7 ልዑልእግዚአብሔርስለሚረዳኝ አልዋረድም፤

ስለዚህ ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ

አድርጌአለሁ፤

እንደማላፍርም ዐውቃለሁ።

8 ንጹሕ መሆኔን የሚያረጋግጥልኝ በአጠገቤ አለ፤

ታዲያ ማን ሊከሰኝ ይችላል?

እስቲ ፊት ለፊት እንጋጠም!

ተቃዋሚዬስ ማን ነው?

እስቲ ይምጣ!

9 የሚረዳኝ እርሱ ጌታእግዚአብሔርነው፤

የሚፈርድብኝስ ማን ነው?

እነሆ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤

ብልም ይበላቸዋል።

10 ከእናንተእግዚአብሔርንየሚፈራ፣

የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው?

ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣

ብርሃንም ከሌለው፣

በእግዚአብሔርስም ይታመን፤

በአምላኩም ይደገፍ።

11 አሁን ግን እናንተ እሳት አንድዳችሁ፣

የራሳችሁን የሚንቦገቦግ ችቦ የያዛችሁ ሁሉ፣

በሉ በእሳታችሁ ብርሃን ሂዱ፤

ባንቦገቦጋችሁትም የችቦ ብርሃን ተመላለሱ።

እንግዲህ ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፤

በሥቃይም ትጋደማላችሁ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *