ኢሳይያስ 55

ጥሪ ለተጠሙ

1 እናንት የተጠማችሁ ሁሉ ኑ፤

እናንት ገንዘብ የሌላችሁ፣

ወደ ውሆች ኑ፤

ኑና ግዙ፤ ብሉም፤

ኑና ያለ ገንዘብ፣ ያለ ዋጋ፣

የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።

2 ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ?

በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጒልበታችሁን ትጨርሳላችሁ?

ስሙ፤ እኔን ስሙኝ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤

ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች።

3 ጆሮአችሁን ከፍታችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤

ነፍሳችሁም እንድትኖር አድምጡኝ።

ለዳዊት በገባሁት በጽኑ ፍቅሬ፣

ከእናንተም ጋር የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።

4 እነሆ፤ እርሱን ለሕዝቦች ምስክር፣

መሪ፣ የጦር አዝማችም አድርጌዋለሁ።

5 እነሆ፤ የማታውቃቸውን መንግሥታት ትጠራለህ፤

የማያወቁህ መንግሥታት በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ፤

ምክንያቱምእግዚአብሔርአምላክህ፣

የእስራኤል ቅዱስ፣

በክብሩ ከፍ ከፍ አድርጎሃል።

6 እግዚአብሔርበሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤

ቀርቦም ሳለ ጥሩት።

7 ክፉ ሰው መንገዱን፣

በደለኛም ሐሳቡን ይተው።

ወደእግዚአብሔርይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤

ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።

8 “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣

መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና”

ይላልእግዚአብሔር።

9 “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣

መንገዴ ከመንገዳችሁ፣

ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።

10 ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣

ምድርን በማራስ፣

እንድታበቅልና እንድታፈራ

ለዘሪው ዘር፣

ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣

ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣

11 ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣

በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤

ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤

የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል።

12 በደስታ ትወጣላችሁ፤

በሰላምም ትሸኛላችሁ፤

ተራሮችና ኰረብቶች፣

በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤

የሜዳ ዛፎች ሁሉ፣

ያጨበጭባሉ።

13 በእሾኽ ፈንታ የጥድ ዛፍ፣

በኵርንችት ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል።

ይህምየእግዚአብሔርመታሰቢያ፣

ሊጠፋ የማይችል፣

የዘላለም ምልክት ይሆናል።”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *