ኢሳይያስ 62

አዲሱ የጽዮን ስም

1 ጽድቋ እንደ ማለዳ ወጋገን እስኪፈነጥቅ፣

ድነቷ እንደሚያንጸባርቅ ፋና እስኪታይ፣

ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤

ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም።

2 መንግሥታት ጽድቅሽን፣

ነገሥታት ክብርሽን ያያሉ፤

የእግዚአብሔርአፍ በሚያወጣልሽ፣

በአዲስ ስም ትጠሪያለሽ።

3 በእግዚአብሔርእጅ የክብር አክሊል፣

በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።

4 ከእንግዲህ፣ “የተተወች” ብለው አይጠሩሽም፤

ምድርሽም፣ “የተፈታች” አትባልም፤

ነገር ግን፣ “ደስታዬ በእርሷ” ትባያለሽ፤

ምድርሽም፣ “ባለ ባል” ትባላለች፤

እግዚአብሔርበአንቺ ደስ ይለዋል፤

ምድርሽም ባለ ባል ትሆናለች።

5 ጐልማሳ ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣

ልጆችሽእንዲሁ ያገቡሻል፤

ሙሽራ በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፣

አምላክሽም በአንቺ ደስ ይለዋል።

6 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤

ቀንም ሆነ ሌሊት ፈጽሞ አይታክቱም።

እናንት ወደእግዚአብሔርአቤት፣ አቤት የምትሉ፤

ፈጽሞ አትረፉ፤

7 ኢየሩሳሌምን እስኪያጸናት፣

የምድርም ምስጋና እስኪያደርጋት ዕረፍት አትስጡት።

8 እግዚአብሔርበቀኝ እጁ፣

በኀያል ክንዱም እንዲህ ሲል ምሎአል፤

“ከእንግዲህ እህልሽን፣

ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤

ከእንግዲህ የደከምሽበትን፣

አዲስ የወይን ጠጅ ባዕዳን አይጠጡትም።

9 ነገር ግን መከሩን የሰበሰቡ ይበሉታል፤

እግዚአብሔርንምያመሰግናሉ፤

የወይኑን ፍሬ የለቀሙም በመቅደሴ

አደባባዮች ይጠጡታል።”

10 ዕለፉ፤ በበሮቹ በኩል ዕለፉ፤

ለሕዝቡ መንገድ አዘጋጁ፤

አስተካክሉ፤ ጐዳናውን አስተካክሉ፤

ድንጋዩን አስወግዱ፤

ለመንግሥታትም ምልክት አሳዩ።

11 እግዚአብሔርእስከ ምድር ዳርቻ፣

እንዲህ ሲል ዐውጆአል፤

“ለጽዮን ሴት ልጅ፣

‘እነሆ፤ አዳኝሽ መጥቶአል፤

ዋጋሽ በእጁ አለ፤

ዕድል ፈንታሽም ከእርሱ ጋር ነው’ በሏት።”

12 እነርሱም ቅዱስ ሕዝብ፣

እግዚአብሔርየተቤዣቸው ተብለው ይጠራሉ፤

አንቺም የምትፈለግ፣

ከእንግዲህም የማትተው ከተማ ትባያለሽ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *