ሕፃን ተወለደልን
1 ነገር ግን ተጨንቀው የነበሩ ከእንግዲህ ተስፋ ቢስ አይሆኑም። በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ፤ በሚመጣው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ማዶ፣ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል፤
2 በጨለማ የሚኖር ሕዝብ
ታላቅ ብርሃን አየ፤
በሞት ጥላምድር ለኖሩትም
ብርሃን ወጣላቸው።
3 ሕዝብን አበዛህ፤
ደስታቸውንም ጨመርህ፤
ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣
ምርኮንም ሲከፋፈሉ
ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣
እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
4 ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደሆነው፣
የከበዳቸውን ቀንበር፣
በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣
የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።
5 የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣
በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣
ለእሳት ይዳረጋል፤
ይማገዳልም።
6 ሕፃን ተወልዶልናልና፤
ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤
አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።
ስሙም፣ ድንቅ መካር፣
ኀያል አምላክ፣
የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።
7 ለመንግሥቱ ስፋት፣
ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤
ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣
መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤
ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል።
በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤
አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤
የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርቅናት
ይህን ያደርጋል።
የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ
8 ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤
በእስራኤልም ላይ ይወድቃል።
9 ሕዝቡ በሙሉ፣
ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች
ይህን ያውቃሉ፤
በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤
10 “ጡቦቹ ወድቀዋል፤
እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤
የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤
እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።”
11 ነገር ግንእግዚአብሔርየረአሶንን ጠላቶች ያጠናክራል፤
በእነርሱም ላይ ያመጣባቸዋል፤
ባለጋራዎቻቸውንም ያነሣሣባቸዋል።
12 ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤
አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫ ጭቋታል።
ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤
እጁ እንደ ተዘረጋ ነው።
13 ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤
የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርንምአልፈለጉም።
14 ስለዚህእግዚአብሔርራስንና ጅራትን፣
የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸምበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል።
15 ሽማግሌዎችና የተከበሩ ሰዎች ራስ፣
ሐሰትን የሚያስተምሩ ነቢያት ደግሞ ጅራት ናቸው።
16 ይህን ሕዝብ የሚመሩት ያስቱታል፤
የሚመራውም ሕዝብ ከመንገድ ወጥቶ ይባዝናል።
17 ስለዚህ ጌታ በጐበዛዝት ደስ አይሰኝም፤
አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀእግዚአብሔርያላደረ በትና ክፉ አድራጊ ነው፤
የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና።
ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤
እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
18 እንግዲህ ርኵሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤
እሾህንና ኵርንችትን ይበላል፤
ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነዳል፤
ጢሱም ተትጐልጒሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።
19 በሰራዊት ጌታበእግዚአብሔርቍጣ ምድር ትጋያለች፤
ሕዝቡም እሳት ውስጥ እንደሚጨመር
ማገዶ ይሆናል፤
ወንድሙንም ማዳን የሚችል ማንም የለም።
20 በቀኝ በኩል ይጐርሳሉ፤
ነገር ግን ራባቸው አይታገሥም፤
በግራም በኩል ይበላሉ፤
ነገር ግን አይጠግቡም፤
እያንዳንዱም የገዛ ወገኑንሥጋ ይበላል።
21 ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤
በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ፤
ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤
እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።