ኤርምያስ 13

ከተልባ እግር የተሠራ መቀነት

1 እግዚአብሔር፣ “ሄደህ ከተልባ እግር የተሠራ መቀነት ግዛ፤ ወገብህንም ታጠቅበት፤ ነገር ግን ውሃ አታስነካው” አለኝ።

2 ስለዚህእግዚአብሔርእንዳዘዘኝ መቀነቱን ገዛሁ፤ ወገቤንም ታጠቅሁበት።

3 ለሁለተኛም ጊዜየእግዚአብሔርቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤

4 “ገዝተህ የታጠቅህበትን መቀነት ይዘህ፣ ወደ ኤፍራጥስሂድ፤ በዚያም በዐለት ንቃቃት ውስጥ ሸሽገው።”

5 ስለዚህእግዚአብሔርበነገረኝ መሠረት ወደ ኤፍራጥስዠ ሄጄ ሸሸግሁት።

6 ከብዙ ቀን በኋላምእግዚአብሔር፣ “ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፤ በዚያ እንድት ሸሽገው የነገርሁህን መቀነት አምጣ” አለኝ።

7 እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ፤ መታጠቂያውን ከሸሸግሁበት ቦታ ቈፍሬ አወጣሁ፤ መታጠቂያውም ተበላሽቶ፣ ከጥቅም ውጭም ሆኖ ነበር።

8 የእግዚአብሔርምቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤

9 “እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘የይሁዳን ትዕቢትና የኢየሩሳሌምን እብሪት እንደዚሁ አጠፋለሁ።

10 ቃሌን መስማት እምቢ ብለው በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ ሊያመልኳቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን ጣዖቶች የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝቦች ከጥቅም ውጭ እንደሆነው እንደዚህ መቀነት ይበላሻሉ።

11 መቀነት በሰው ወገብ ላይ እንደሚታሰር፣ መላው የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ከእኔ ጋር ተጣብቆ ለስሜ ምስጋናና ክብር፣ የኔ ሕዝብ እንዲሆንልኝ አድርጌው ነበር፤ ሕዝቤ ግን አልሰማም’ ይላልእግዚአብሔር።

የወይን ጠጅ ማድጋ

12 “እንዲህ በላቸው፤ ‘የእስራኤል አምላክእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ “ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል” ይላል። እነርሱም፣ “ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ እንደሚሞላ እኛ አናውቅምን?” ቢሉህ፣

13 እንዲህ በላቸው፤ “እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡትን ነገሥታት፣ ካህናትን፣ ነቢያትን እንዲሁም በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ሁሉ ጨምሮ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።’ ”

14 አንዱን ሰው ከሌላው ጋር፣ አባትንና ወንድ ልጅን እርስ በእርስ አጋጫለሁ፤ ይላልእግዚአብሔር፤ ያለ ሐዘኔታ፣ ያለ ምሕረትና ያለ ርኅራኄ አጠፋቸዋለሁ።’ ”

የትዕቢት ውጤት

15 እግዚአብሔርተናግሮአልና፣

ስሙ፤ ልብ በሉ፤

ትዕቢተኛም አትሁኑ።

16 ጨለማን ሳያመጣ፣

በሚጨልሙትም ተራሮች ላይ፣

እግሮቻችሁ ሳይሰናከሉ፣

ለአምላካችሁለእግዚአብሔርክብርን ስጡ።

ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ፤

እርሱ ወደ ጨለማ ይለውጠዋል፤

ድቅድቅ ጨለማም ያደርገዋል።

17 ባትሰሙ ግን፣

ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ፣

በስውር ታለቅሳለች፤

የእግዚአብሔርመንጋ ተማርኮአልና፣

ዐይኔ አምርሮ ያለቅሳል፤

እንባዬም እንደ ጐርፍ ይወርዳል።

18 ለንጉሡና ለእናቱ ለእቴጌዪቱ፣

የክብር ዘውዳችሁ፣

ከራሳችሁ ይወድቃልና፣

ከዙፋናችሁ ውረዱ” በላቸው።

19 በኔጌቭ ያሉ ከተሞች ይዘጋሉ፤

የሚከፍታቸውም አይኖርም፤

ይሁዳ ሁሉ ተማርኮ ይሄዳል፤

ሙሉ በሙሉም ይዘጋል።

20 ዐይኖቻችሁን ከፍታችሁ፣

ከሰሜን የሚመጡትን እዩ።

ለአንቺ የተሰጠው መንጋ፣

የተመካሽባቸው በጎች የት አሉ?

21 ልዩ ወዳጆች እንዲሆኑሽ

ያስተማርሻቸው፣

ባለ ሥልጣን ሲሆኑብሽ ምን ትያለሽ?

እንደምትወልድ ሴት፣

ምጥ አይዝሽምን?

22 “ይህ ለምን ደረሰብኝ?” ብለሽ

ራስሽን ብትጠይቂ፣

ልብስሽን ተገልበሽ የተገፈተርሽው፣

በሰውም እጅ የተንገላታሽው፣

ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ነው።

23 ኢትዮጵያዊመልኩን፣

ነብርስ ዝንጒርጒርነቱን መለወጥ ይችላልን?

እናንት ክፉ ማድረግ የለመዳችሁትም፣

መልካም ማድረግ አትችሉም።

24 “የበረሓ ነፋስ ብትንትኑን እንደሚያወጣው ገለባ፣

እንዲሁ እበታትናችኋለሁ።

25 እኔን ረስተሽ፣

በከንቱ አማልክት ስለታመንሽ፣

ያወጅሁልሽ ድርሻሽ፣

ዕጣ ፈንታሽ ይህ ነው፤”

ይላልእግዚአብሔር፤

26 “ኀፍረትሽ እንዲገለጥ፣

ልብስሽን ፊትሽ ድረስ እገልባለሁ፤

27 በኰረብቶችና በሜዳዎች ላይ፣

አስጸያፊ፣ ተግባርሽን፣

ምንዝርናሽንና ማሽካካትሽን፣

ኀፍረተቢስ ግልሙትናሽን አይቻለሁ።

ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ወዮልሽ፤

ከርኵሰትሽ የማትጸጂው እስከ መቼ ነው?”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *