ሐሰተኛው ነቢይ ሐናንያ
1 በዚያው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንደ ነገሠ በዐራተኛው ዓመት፣ አምስተኛ ወር፣ የገባዖኑ ሰው የዓ ዙር ልጅ ነቢዩ ሐናንያበእግዚአብሔርቤት በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፤
2 “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘የባቢሎን ንጉሥ የጫነባችሁን ቀንበር እሰብራለሁ፤
3 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርከእግዚአብሔርቤት ወደ ባቢሎን የወሰዳቸውን ዕቃዎች ሁሉ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መልሼ አመጣለሁ።
4 የይሁዳንም ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፣ሌሎች ከይሁዳ ወደ ባቢሎን ተማርከው የተወሰዱትንም ሁሉ ወደዚህ ስፍራ እመልሳለሁ’ ይላልእግዚአብሔር፤ የባቢሎን ንጉሥ የጫነባቸውን ቀንበር እሰብራለሁና።’ ”
5 ነቢዩ ኤርምያስም በካህናቱናበእግዚአብሔርቤት ቆመው በነበሩት ሕዝብ ሁሉ ፊት፣ ለነቢዩ ለሐናንያ እንዲህ ብሎ መለሰለት፦
6 “አሜን፤እግዚአብሔርያድርገው፤የእግዚአብሔርንቤት ዕቃ ሁሉ፣ ተማርከው የተወሰዱትንም ምርኮኞች ሁሉ ከባቢሎን በመመለስ፣እግዚአብሔርየተናገርኸውን ቃል ይፈጽም።
7 ነገር ግን ለአንተም ለዚህም ሕዝብ የምናገረውን ቃል ስማ፤
8 ከአንተና ከእኔ በፊት ጥንት የተነሡ ነቢያት፣ በብዙ አገሮችና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ስለ ጦርነት፣ ስለ ጥፋትና ስለ መቅሠፍት ትንቢት ተናግረዋል።
9 ነገር ግን ስለ ሰላም ትንቢት የተናገረ ነቢይእግዚአብሔርበእውነት እንደላከው የሚታወቀው የተናገረው ትንቢት ሲፈጸም ነው።
10 ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ኤርምያስ ዐንገት ወስዶ ሰበረው፤
11 በሕዝቡም ፊት፣ “እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የና ቡከደናፆርን ቀንበር ከሕዝቡ ሁሉ ጫንቃ ላይ ልክ እንደዚህ እሰብራለሁ’ አለ። በዚህ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ትቶት መንገዱን ቀጠለ።
12 ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ አንገት ወስዶ ከሰበረ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣የእግዚአብሔርቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤
13 “ሄደህ ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ አንተ የዕንጨት ቀንበር ሰብረሃል፤ እኔ ግን በምትኩ የብረት ቀንበር እሠራለሁ።
14 የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እንዲያገለግሉ፣ በእነዚህ ሕዝቦች ላይ የብረት ቀንበር አደርጋለሁ፤ እነርሱም ይገዙለታል፤ በዱር አራዊት ላይ እንኳ ሥልጣን እሰጠዋለሁ።’ ”
15 ነቢዩ ኤርምያስም ለነቢዩ ሐናንያ እንዲህ አለው፤ “ሐናንያ ሆይ፤ ስማ!እግዚአብሔርሳይልክህ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል፤
16 ስለዚህእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፦ ‘ከምድር ገጽ አስወግድሃለሁ፤በእግዚአብሔርምላይ ዐመፅ ተናግረሃልና፣ በዚህ ዓመት ትሞታለህ።”
17 ነቢዩም ሐናንያ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ።