ኤርምያስ 30

የእስራኤል ሕዝብ መመለስ

1 ከእግዚአብሔርዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤

2 “የእስራኤል አምላክእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው።

3 እነሆ፣ ሕዝቤን እስራኤልንና ይሁዳን’ ይላልእግዚአብሔር፤ ‘ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር የምመልስበት ጊዜ ተቃርቦአል፤እነርሱም ይወርሷታል’ ይላልእግዚአብሔር።”

4 እግዚአብሔርስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤

5 “እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤

“ ‘የፍርሀትና የሽብር ጩኸት ተሰምቶአል፤

ሰላምም የለም።

6 እስቲ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤

ወንድ መውለድ ይችላል?

ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣

እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣

የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው?

7 ያ ቀን ምንኛ አስጨናቂ ይሆናል!

እንደዚያም ያለ አይኖርም፤

ለያዕቆብ የመከራ ጊዜ ነው፤

ነገር ግን ይተርፋል።

8 “ ‘በዚያን ቀን’ ይላል የሰራዊት ጌታእግዚአብሔር፤

‘በጫንቃቸው ላይ ያለውን ቀንበር እሰብራለሁ፤

እስራታቸውንም እበጥሳለሁ፤

ከእንግዲህ ባዕዳን አይገዙአቸውም።

9 ነገር ግን ለአምላካቸውለእግዚአብሔር፣

ለማስነሣላቸውም ለንጉሣቸው፣

ለዳዊት ይገዛሉ።

10 “ ‘ስለዚህ፤ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤

እስራኤል ሆይ፤ አትደንግጥ፤’

ይላልእግዚአብሔር፤

‘አንተን ከሩቅ አገር፣

ዘርህንም ከተማረኩበት ምድር እታደጋለሁ፤

ያዕቆብ ተመልሶ በሰላምና በርጋታ ይቀመጣል፣

የሚያስፈራውም አይኖርም።

11 እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ አድንሃለሁም፣

ይላልእግዚአብሔር፤

‘በአሕዛብ መካከል በትኜሃለሁ፤

እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤

አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም፤

በመጠኑ እቀጣሃለሁ እንጂ፣

ያለ ቅጣት አልተውህም።

12 “እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤

“ ‘ስብራትህ የማይጠገን፣

ቍስልህም የማይድን ነው።

13 የሚሟገትልህ ሰው የለም፤

ለቍስልህ መድኃኒት አይኖርም፤

ፈውስም አታገኝም።

14 ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤

ስለ አንተም ግድ የላቸውም።

ጠላት እንደሚመታ መታሁህ፤

እንደ ጨካኝም ቀጣሁህ፤

በደልህ ታላቅ፣

ኀጢአትህም ብዙ ነውና።

15 ፈውስ ለማይገኝለት ሕመምህ፣

ስለቍስልህ ለምን ትጮኻለህ?

በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ስለ ሆነ፣

እነዚህን ሁሉ አድርጌብሃለሁና።

16 “ ‘ነገር ግን አሟጠው የበሉህ ሁሉ እንደዚያው ይበላሉ፤

ጠላቶችህ ሁሉ ለምርኮ ዐልፈው ይሰጣሉ፤

የሚዘርፉህ ይዘረፋሉ፤

የሚበዘብዙህም ሁሉ ይበዘበዛሉ።

17 አንተን ግን መልሼ ጤነኛ አደርግሃለሁ፤

ቍስልህንም እፈውሳለሁ፤’

ይላልእግዚአብሔር።

“ ‘የተናቀች፣

ማንም የማይፈልጋት ጽዮን” ብለውሃልና።’

18 “እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤

“ ‘እነሆ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፤

ለማደሪያውም እራራለሁ፤

ከተማዪቱ በፍርስራሿ ጒብታ ላይ ትሠራለች፤

ቤተ መንግሥቱም በቀድሞ ቦታው ይቆማል።

19 ከእነርሱም የምስጋና መዝሙር፣

የእልልታ ድምፅ ይሰማል።

እኔ አበዛቸዋለሁ፤

ቍጥራቸውም አይቀንስም፣

አከብራቸዋለሁ፤

የተናቁም አይሆኑም።

20 ልጆቻቸው እንደ ቀድሞው ይሆናሉ፤

ማኅበረ ሰቡም በፊቴ የጸና ይሆናል፤

የሚጨቍኗቸውን ሁሉ እቀጣለሁ።

21 መሪያቸው ከራሳቸው ወገን ይሆናል፤

ገዣቸውም ከመካከላቸው ይነሣል፤

ወደ እኔ አቀርበዋለሁ፤ እርሱም ይቀርበኛል፤

አለዚያማ ደፍሮ፣

ወደ እኔ የሚቀርብ ማን ነው?

ይላልእግዚአብሔር።

22 “ ‘ስለዚህ እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤

እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።’ ”

23 እነሆ፣የእግዚአብሔርማዕበል፣

በቍጣ ይነሣል፤

የሚገለባብጥም ዐውሎ ነፋስ፣

በክፉዎች ዐናት ላይ ይወርዳል።

24 የልቡን ሐሳብ ሳይፈጽም፣

የእግዚአብሔርቍጣ፣

እንዲሁ አይመለስም፤

በሚመጡትም ዘመናት፣

ይህን ታስተውላላችሁ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *