ኤርምያስ 33

የመመለስ ተስፋ

1 ኤርምያስ በዘብ ጠባቂዎች አደባባይ በግዞት ሳለየእግዚአብሔርቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እርሱ መጣ፦

2 “ምድርን የፈጠራት፣ ያበጃትና የመሠረታትእግዚአብሔር፣ ስሙእግዚአብሔርየሆነ፣ እርሱ እንዲህ ይላል፤

3 ‘ወደ እኔ ጩኽ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና የማይመረመር ነገር እገልጥልሃለሁ፤’

4 የእስራኤል አምላክእግዚአብሔርከባቢሎናውያንጋር ባለው ውጊያ፣ ዐፈር በመደልደልና በሰይፍ የሚደረገውን ጥቃት ለመከላከል ስለ ፈረሱት ስለዚህች ከተማ ቤቶችና ስለ ይሁዳ ነገሥታት ቤተ መንግሥት እንዲህ ይላል፤

5 ‘እነዚህ በቍጣዬና በመዓቴ በምገድላቸው ሰዎች ሬሳ ይሞላሉ፤ ስለ ክፋቷ ሁሉ ከዚህች ከተማ ፊቴን እሰውራለሁ።

6 “ ‘ይሁን እንጂ፣ ፈውስንና ጤንነትን እንደ ገና እሰጣታለሁ፤ ሕዝቤንም እፈውሳለሁ፤ በብዙ ሰላምና በርጋታ እንዲኖሩ አደርጋለሁ።

7 የይሁዳን ምርኮና የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፤ቀድሞ እንደ ነበሩት ሁኔታ አድርጌ አበጃቸዋለሁ፤

8 እኔን ከበደሉበት ኀጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ በእኔ ላይ ያመፁበትንም ኀጢአታቸውን ሁሉ ይቅር እላለሁ።

9 ይህች ከተማ፣ ለእርሷ ያደረግሁትን በጎ ነገር ሁሉ በሚሰሙት የምድር ሕዝቦች ሁሉ ፊት ለዝና፣ ለደስታ፣ ለምስጋናና ለክብር ትሆናለች፤ ከምሰጣትም የተትረፈረፈ ብልጽግናና ሰላም የተነሣ ይፈራሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም።’

10 “እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ይህችን ስፍራ፣ ‘ሰውና እንስሳት የማይኖሩባት ባድማ ናት’ ትላላችሁ፤ ነገር ግን ሰውም ሆነ እንስሳ ባልነበሩባቸውና ባድማ በሆኑት በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች፣ እንደ ገና ድምፅ ይሰማል፤

11 የሐሤትና የደስታ ድምፅ፣ የሙሽራውና የሙሽራዪቱ ድምፅ፣ እንዲሁም፦

“እግዚአብሔርቸር ነውና፤

ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤

የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርንአመስግኑ፤”

የሚል የምስጋናን መሥዋዕት ይዘው ወደእግዚአብሔርቤት የሚመጡ ሰዎች ድምፅ ይሰማል፤ የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ እመልሳለሁና፤ ይላልእግዚአብሔር።

12 “የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘ሰውም ሆነ እንስሳት በማይኖሩበት በዚህ ባዶ ስፍራ፣ በከተማዎቹም ሁሉ እረኞች መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት እንደ ገና ያገኛሉ።

13 በተራራማው አገር፣ በምዕራብ ተራሮች ግርጌና በኔጌብ ባሉ ከተሞች በብንያም አገር፣ በይሁዳ ከተሞች እንዲሁም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች መንጎች እንደ ገና በሚቈጥራቸው ሰው እጅ ሥር ያልፋሉ’ ይላልእግዚአብሔር።

14 “ ‘ለእስራኤል ቤትና ለይሁዳ ቤት የገባሁትን የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ይመጣል’ ይላልእግዚአብሔር።

15 “ ‘በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ፣

ከዳዊት ቤት ጻድቅ ቅርንጫፍ አበቅላለሁ፤

በምድሪቱም ፍትሕንና ጽድቅን ያደርጋል።

16 በዚያ ዘመን ይሁዳ ይድናል፤

ኢየሩሳሌም በሰላም ትኖራለች፤

የምትጠራበትም ስም፣

“እግዚአብሔርጽድቃችን” የሚል ይሆናል።’

17 እግዚአብሔርእንዲህ ይላልና፤ ‘ከዳዊት ዘር በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አይታጣም፤

18 ሌዋውያን ከሆኑት ካህናትም የሚቃጠል መሥዋዕት ለማቅረብ፣ የእህል ቍርባን ለማቃጠልና ሌላውንም መሥዋዕት ለመሠዋት ሁል ጊዜ በፊቴ የሚቆም ሰው አይታጣም።’ ”

19 የእግዚአብሔርቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

20 “እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘ለቀንና ለሌሊት የወሰንሁትን ሥርዐት በማፋለስ ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዳይፈራረቁ ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፣

21 በዚያ ጊዜ ከአገልጋዬ ከዳዊት ጋር የገባሁትን ኪዳን፣ እንዲሁም በፊቴ በክህነት ከሚያገለግሉት ሌዋውያን ጋር የገባሁትን ኪዳን ማፍረስ ይቻላል፤ ዳዊትም ከእንግዲህ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ዘር አይኖረውም።

22 የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር እንዲሁም በፊቴ የሚቆሙትን ሌዋውያን እንደማይቈጠሩ እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደማይሰፈር የባሕር አሸዋ አበዛቸዋለሁ።’ ”

23 የእግዚአብሔርቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

24 “ይህ ሕዝብ፣ ‘እግዚአብሔር፣ የመረጣቸውን ሁለቱን መንግሥታትጥሎአል’ እንደሚሉ አላስተዋልህምን? ሕዝቤን ንቀዋል፤ እንደ ሕዝብም አልቈጠሯቸውም።

25 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘የቀንና የሌሊት ኪዳኔን፣ የሰማይንና የምድርንም ሥርዐት ያጸናሁ እኔ ካልሆንሁ፣

26 የያዕቆብንና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ፤ ከልጆቹም በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ ዘር ላይ ገዥ እንዲሆኑ አልመርጥም፤ ይህንም የምለው ምርኮአቸውን ስለምመልስናስለምራራላቸው ነው።’ ”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *