ስለ ፍልስጥኤማውያን የተነገረ መልእክት
1 ፈርዖን ጋዛን ድል ከማድረጉ በፊት፣ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣውየእግዚአብሔርቃል ይህ ነው፤
2 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
“እነሆ፤ በሰሜን በኩል ውሃ እየሞላ ነው፣
ኀይለኛ ጐርፍ ይሆናል፤
አገሪቷንና በውስጧ ያሉትንም ሁሉ፣
ከተሞቿንና ነዋሪዎቻቸውን ያጥለቀልቃል።
ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤
የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላል፤
3 ከፈረስ ኮቴ ድምፅ፣
ከጠላት ሠረገላ ጩኸትና፣
ከሠረገላው ሽክርክሪት ፍትጊያ ድምፅ የተነሣ፣
አባቶች ልጆቻቸውን ለመርዳት ወደ ኋላ መለስ አይሉም፤
እጃቸውም ስንኩል ይሆናል።
4 ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት፣
ተርፈውም የሚረዷቸውን ሁሉ፣
ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ፣
ቀኑ ደርሶአልና።
እግዚአብሔርበከፍቶርዳርቻ የቀሩትን፣ ፍልስጥኤማውያንን ሊያጠፋ
ተነሥቶአል።
5 ጋዛ በማዘን ራሷን ትላጫለች፣
አስቀሎና አፏን ትይዛለች።
በሜዳማ ስፍራ የምትገኙ ትሩፋን ሆይ፤
እስከ መቼ ሰውነታችሁን ትቧጥጣላችሁ?
6 “ ‘የእግዚአብሔርሰይፍ ሆይ፤
የማታርፈው እስከ መቼ ነው?
ወደ ሰገባህ ተመልሰህ ግባ፤
ጸጥ ብለህ ተቀመጥ’ ትላላችሁ።
7 ነገር ግንእግዚአብሔርአስቀሎናንና የባሕሩን ዳርቻ፣
እንዲወጋ ሲያዝዘው፣
እንዲፈጽመውም ትእዛዝ ሲሰጠው፣
እንዴት ማረፍ ይችላል?”