ኤርምያስ 5

ቅን ሰው አለመገኘቱ

1 “በኢየሩሳሌም መንገዶች እስቲ ውጡ፤ ወደ ላይ ወደታችም ውረዱ፤

ዙሪያውን ተመልከቱ ቃኙ፤

በአደባባይዋም ፈልጉ፤

እውነትን የሚሻና በቅንነት የሚሄድ፣

አንድ ሰው እንኳ ብታገኙ፣

እኔ ይህቺን ከተማ እምራታለሁ።

2 ‘ሕያውእግዚአብሔርን! ቢሉም፣

የሚምሉት በሐሰት ነው።”

3 እግዚአብሔርሆይ፤ ዐይኖችህ እውነትን አይመለከቱምን?

አንተ መታሃቸው፤ እነርሱ ግን አልተሰማቸውም፤

አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን አልታረሙም፤

ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠነከሩ

በንስሓ ለመመለስም አልፈለጉም።

4 እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ “እነዚህ ድኾች ናቸው፤

ሞኞች ናቸው፤

የእግዚአብሔርንመንገድ፣

የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና።

5 ስለዚህ ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ፤

ለእነርሱም እናገራለሁ፤

በእርግጥ እነርሱየእግዚአብሔርንመንገድ፣

የአምላካቸውንም ሕግ ያውቃሉና።”

ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ ያው እንደዚያው ቀንበሩን ሰብረዋል፤

እስራቱንም በጥሰዋል።

6 ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰባብራቸዋል፣

የበረሓ ተኵላም ይቦጫጭቃቸዋል፤

ብቅ የሚለውን ሰው ሁሉ ለመገነጣጠል፣

ነብር በከተሞቻቸው ዙሪያ ያደባል፤

ዐመፃቸው ታላቅ፣

ክሕደታቸው ብዙ ነውና።

7 “ታዲያ፣ እንዴት ይቅር ልልሽ እችላለሁ?

ልጆችሽ ትተውኛል፤

እውነተኛውን አምላክ ትተው አማልክት ባልሆኑት ምለዋል፤

እስኪጠግቡ ድረስ መገብኋቸው፤

እነርሱ ግን አመነዘሩ፤

ወደ ጋለሞቶችም ቤት ተንጋጉ።

8 እንደ ተቀለበ ብርቱ ድንጒላ ፈረስ ሆኑ፤

እያንዳንዱም የሌላውን ሚስት ተከትሎ አሽካካ።

9 ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀጣቸውምን?”

ይላልእግዚአብሔር።

“እኔ ራሴ እንደዚህ ዐይነቱን ሕዝብ፣

አልበቀልምን?

10 “ወደ ወይን አትክልቷ ስፍራ ገብታችሁ አበላሹት፤

ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉት፤

ቅርንጫፎቿን ገነጣጥሉ፤

የእግዚአብሔርአይደሉምና፤

11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት፣

ፈጽመው ከድተውኛል፤”

ይላልእግዚአብሔር።

12 በእግዚአብሔርላይ ሐሰትን ተናገሩ፤

እንዲህም አሉ፤ “እሱ ምንም አያደርግም!

ክፉ ነገር አይደርስብንም፤

ሰይፍም ራብም አናይም፤

13 ነቢያቱ ነፋስ እንጂ ሌላ ነገር አይደሉም፤

ቃሉም በውስጣቸው የለም፤

ያሉት ሁሉ በእነርሱ ላይ ይመለስ።”

14 ስለዚህ የሰራዊትጌታ እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤

“ሕዝቡ ይህን ቃል ስለ ተናገረ፣

ቃሌን በአፍህ ውስጥ የሚፋጅ እሳት፣

ይህንም ሕዝብ ማገዶ አደርጋለሁ፤

እሳቱም ይበላቸዋል።

15 የእስራኤል ቤት ሆይ፣” ይላልእግዚአብሔር፤

“ከሩቅ ሕዝብን አመጣባችኋለሁ፤

ጥንታዊና ብርቱ፣

ቋንቋውን የማታውቁት፣ ንግግሩንም

የማትረዱት ሕዝብ ነው።

16 የፍላጻቸው ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤

ሁሉም ብርቱ ተዋጊዎች ናቸው።

17 ሰብልህንና ምግብህን ጠራርገው ይበሉብሃል፤

ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይውጣሉ፣

በጎችህንና ከብቶችህን ይፈጃሉ፤

የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ያወድማሉ፤

የታመንህባቸውንም የተመሸጉ ከተሞች፣

በሰይፍ ያጠፉአቸዋል።

18 “ይሁን እንጂ፣ በዚያን ዘመን እንኳ” ይላልእግዚአብሔር፤ “ፈጽሜ አላጠፋችሁም።

19 ሕዝቡ፣ ‘እግዚአብሔርአምላካችን ይህን ሁሉ ነገር ለምን አደረገብን?’ ብለው ቢጠይቁ ‘እኔን፣ እንደ ተዋችሁኝና በራሳችሁ ምድር ባዕዳን አማልክትን እንዳገለገላችሁ፣ እንደዚሁ የእናንተ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።

20 “በያዕቆብ ቤት ይህን አሰሙ፣

በይሁዳም እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤

21 እናንት ዐይን እያላችሁ የማታዩ፣

ጆሮ እያላችሁ የማትሰሙ፣

ሞኞችና የማታስተውሉ ሰዎች ይህን ስሙ፤

22 ልትፈሩኝ አይገባችሁምን?” ይላልእግዚአብሔር፤

“በእኔ ፊት ልትንቀጠቀጡስ አይገባምን?

ለዘላለም ዐልፎት መሄድ እንዳይችል፣

አሸዋን ለባሕር ድንበር አደረግሁ፤

ማዕበሉ እየጋለበ ቢመጣ ከዚያ አያልፍም፤

ሞገዱ ቢጮኽም ሊያቋርጠው አይችልም።

23 ይህ ሕዝብ ግን የሸፈተና እልከኛ ልብ አለው፤

መንገድ ለቆ ሄዶአል፤

24 በልባቸውም፣

‘የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚያዘንበውን፣

መከርን በወቅቱ የሚያመጣልንን፣

አምላካችንንእግዚአብሔርንእንፍራ’ አላሉም።

25 በደላችሁ እነዚህን አስቀርቶባችኋል።

ኀጢአታችሁ መልካሙን ነገር ከልክሎአችኋል።

26 “በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና፤

ወፍ እንደሚያጠምዱ ሰዎች፣

ወጥመድ ዘርግተው ሰው እንደሚይዙ ሰዎችም ያደባሉ።

27 ወፎች እንደሞሉት ጐጆ፣

ቤታቸው በማጭበርበር የተሞላ ነው፤

ባለጠጎችና ኀያላን ሆነዋል፤

28 ወፍረዋል፤ ሰብተዋልም።

ክፋታቸው ገደብ የለውም፤

ወላጅ የሌላቸው ፍትሕ እንዲያገኙ

አልቆሙላቸውም፤

ለድኾችም መብት አልተከራከሩም።

29 ስለ እነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን?”

ይላልእግዚአብሔር።

እንዲህ ዐይነቶቹን ሕዝብ፣

እኔ ራሴ ልበቀላቸው አይገባኝምን?

30 “የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ነገር፣

በምድሪቱ ላይ ሆኖአል፤

31 ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤

ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤

ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወዳሉ፤

ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *