ዘካርያስ 2

የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰው

1 ደግሞም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰውም በፊቴ አየሁ፤

2 እኔም፣ “የት ልትሄድ ነው?” አልሁት።

እርሱም፣ “የኢየሩሳሌም ርዝመትና ስፋትምን ያህል እንደሆነ ለመለካት መሄዴ ነው” አለኝ።

3 ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ፤

4 እንዲህም አለው፣ “ሩጥና ለዚያ ጒልማሳ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘በውስጧ ካለው የሰውና የከብት ብዛት የተነሣ፣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች፤

5 እኔ ራሴ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፤ ይላልእግዚአብሔር‘በውስጧም ክብሯ እሆናለሁ።’

6 “ኑ! ኑ! ውጡ ከሰሜን ምድር አምልጡ” ይላልእግዚአብሔር፤ “ለአራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና፤” ይላልእግዚአብሔር።

7 “አንቺ ጽዮን ነዪ፤ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፤ ኰብልዪ።”

8 እግዚአብሔርጸባኦት እንዲህ ይላልና፤ “ካከበረኝና በዘረፉአችሁ አሕዛብ ላይ ከላከኝ በኋላ፣ የሚነካችሁ የዐይኑን ብሌን ይነካል፤

9 እነሆ፤ እጄን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል፤ ከዚያምእግዚአብሔርጸባኦት እኔን እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።

10 “የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ ደስም ይበልሽ፤ እኔ እመጣለሁና፤ በመካከልሽም እኖራለሁ” ይላልእግዚአብሔር።

11 “በዚያ ቀን ብዙ አሕዛብ ወደእግዚአብሔርይጠጋሉ፤ የእኔም ሕዝብ ይሆናሉ። በመካከልሽ እኖራለሁ፤እግዚአብሔርጸባኦት ወደ አንቺ እንደ ላከኝም ታውቃላችሁ።

12 እግዚአብሔርምበተቀደሰችው ምድር ይሁዳን ርስቱ አድርጎ ይወርሳል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደ ገና ይመርጣል።

13 እግዚአብሔርከተቀደሰ ማደሪያው ተነሥቶአልና፣ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሆይ፤ በፊቱ ጸጥ በል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *