ዘካርያስ 3

ለሊቀ ካህኑ የሚሆን ንጹሕ ልብስ

1 እርሱም ሊቀ ካህኑን ኢያሱንበእግዚአብሔርመልአክ ፊት ቆሞ፣ ሰይጣንምሊከሰው በስተ ቀኙ ቆሞ አሳየኝ።

2 እግዚአብሔርምሰይጣንን፣ “አንተ ሰይጣን፤እግዚአብሔርይገሥጽህ፤ ኢየሩሳሌምን የመረጠእግዚአብሔርይገሥጽህ፤ ይህ ሰው ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን?” አለው።

3 ኢያሱም ያደፈ ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር።

4 መልአኩም ከፊቱ ቆመው የነበሩትን፣ “ያደፉ ልብሶቹን አውልቁለት” አላቸው።

ኢያሱንም፣ “እነሆ፤ ኀጢአትህን ከአንተ አስወግጃለሁ፤ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ” አለው።

5 እኔም፣ “ንጹሕ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉለት” አልሁ።የእግዚአብሔርምመልአክ በአጠገቡ ቆሞ እያለ፣ ንጹሕ ጥምጥም በራሱ ላይ አደረጉለት፤ ልብስም አለበሱት።

6 የእግዚአብሔርምመልአክ ለኢያሱ ይህን ማስጠንቀቂያ ሰጠው፤

7 “እግዚአብሔርጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘በመንገዴ ብትሄድ፣ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፣ ቤቴን ታስተዳድራለህ፤ በአደባባዮቼም ላይ ኀላፊ ትሆናለህ፤ በዚህ በቆሙት መካከል ቦታ እሰጥሃለሁ።

8 “ ‘ሊቀ ካህኑ ኢያሱ ሆይ፤ ስማ፤ በፊትህ የሚቀመጡትም ረዳቶችህ ገና ወደ ፊት ለሚመጡት ምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፤ እነሆ፤ ባሪያዬን ቊጥቋጡን አመጣለሁ።

9 በኢያሱ ፊት ያስቀመጥሁት ድንጋይ እነሆ! በዚያ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዐይኖችአሉ፤ በእርሱም ላይ ቅርጽ እቀርጻለሁ፤ የዚህችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ፤’ ይላልእግዚአብሔርጸባኦት።

10 “ ‘በዚያን ቀን እያንዳንዱ በገዛ ወይኑና በለሱ ሥር ሆኖ ባልንጀራውን ይጋብዛል፤’ ” ይላልእግዚአብሔርጸባኦት።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *