ዘካርያስ 7

ፍትሕና ምሕረት የተወደደ ነው

1 ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ካሴሉ በተባለው በዘጠነኛው ወር፣ በአራተኛው ቀንየእግዚአብሔርቃል ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

2 የቤቴል ሰዎችእግዚአብሔርንለመለመን ሳራሳርንና ሬጌ ሜሌክን አብረዋቸው ከነበሩት ሰዎች ጋር ላኩ፤

3 እነርሱምየእግዚአብሔርጸባኦት ቤት ካህናትና ነቢያት፣ “ብዙ ዓመት እንዳደረግሁት፣ በአምስተኛው ወር ማዘንና መጾም ይገባኛልን?” ብለው ጠየቁ።

4 ከዚያምየእግዚአብሔርጸባኦት ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

5 “የምድሩን ሕዝብ ሁሉና ካህናቱን እንዲህ በላቸው፤ ‘ባለፉት ሰባ ዓመታት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር የጾማችሁትና ያዘናችሁት በእርግጥ ለእኔ ነበርን?

6 ትበሉና ትጠጡ የነበረውስ ለራሳችሁ አይደለምን?

7 ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች በሰላምና በብልጽግና ላይ ሳሉ፣ የደቡብና የምዕራብ ኰረብቶች ግርጌ የሰው መኖሪያም በነበሩበት ጊዜ፣እግዚአብሔርበቀደሙት ነቢያት የተናገረው ቃል ይህ አልነበረምን?’ ”

8 የእግዚአብሔርቃል እንደ ገና ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

9 “እግዚአብሔርጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘እውነተኛ ፍትሕ አስፍኑ፣ እርስ በርሳችሁ ምሕረትና ርኅራኄን አድርጉ፤

10 መበለቲቱን ወይም ድኻ አደጉን፣ መጻተኛውን ወይም ድኻውን አታስጨንቁ፤ በልባችሁም አንዳችሁ በአንዳችሁ ላይ ክፉ አታስቡ።’

11 “እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም፤ በእልኸኝነት ጀርባቸውን አዞሩ፤ ጆሮአቸውንም ደፈኑ።

12 ልባቸውን እንደ ባልጩት አጠነከሩ፤እግዚአብሔርጸባኦት በቀደሙት ነቢያት በኩል በመንፈሱ የላከውን ቃል ወይም ሕግ አልሰሙም፤ ስለዚህእግዚአብሔርጸባኦት እጅግ ተቈጣ።

13 “ ‘ስጠራቸው አልሰሙም፤ ስለዚህ ሲጠሩኝ አልሰማም’ ይላልእግዚአብሔርጸባኦት።

14 በማያውቋቸው በባዕዳን አሕዛብ መካከል በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው፤ ከእነርሱ በኋላ ማንም እስከማይመጣባትና እስከማይሄድባት ድረስ ምድሪቱ ባድማ ሆነች፤ መልካሚቱን ምድር ባድማ ያደረጓት በዚህ ሁኔታ ነው።’ ”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *