መሳፍንት 2

የእግዚአብሔር መልአክ በቦኪም

1 የእግዚአብሔርመልአክ ከጌልገላ ወደ ቦኪም ወጥቶ እንዲህ አለ፤ “ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፤ ለቀደሙትም አባቶቻችሁ ልሰጣቸው ወደማልሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፤ እንዲህም አልሁ፤ ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አላፈርስም፤

2 እናንተም ከዚህች ምድር ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን አታድርጉ፤ መሠዊያቸውንም አፍርሱ፤ እናንተ ግን አልታዘዛችሁኝም፤ ይህን ያደረጋችሁት ለምንድ ነው?

3 ስለዚህ አሁንም ከፊታችሁ አሳድጄ እንደማላስ ወጣቸው እነግራችኋለሁ፤ ነገር ግን እነርሱ የጐን ውጋት፣ አማልክቶቻቸውም ወጥመድ ይሆኑባችኋል።”

4 የእግዚአብሔርምመልአክ ይህን ቃል ለእስራኤላውያን ሁሉ በተናገረ ጊዜ፣ ሕዝቡ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤

5 ያንን ስፍራ ቦኪምብለው ጠሩት፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ።

ያለመታዘዝ ውጤት

6 ኢያሱ ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ እያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ ምድሪቱን ለመውረስ ወደየርስቱ ሄደ።

7 ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ እንዲሁም ከእርሱ በኋላእግዚአብሔርለእስራኤል ያደረገውን ታላላቅ ነገሮች ሁሉ ያዩ አለቆች በነበሩበት ዘመን ሁሉ ሕዝቡእግዚአብሔርንአመለከ።

8 የእግዚአብሔርአገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ በመቶ ዐሥር ዓመቱ ሞተ።

9 እነርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በምትገኘው ከገዓስ ተራራ በስተ ሰሜን ባለችው በራሱ ርስት ላይ በተምናሔሬስ ቀበሩት።

10 ያ ሁሉ ትውልድ ወደ አባቶቹ ከተከማቸ በኋላእግዚአብሔርንምሆነ እርሱ ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ነገር የማያውቅ ሌላ ትውልድ ተነሣ።

11 ከዚያም እስራኤላውያንበእግዚአብሔርፊት ክፉ ነገር አደረጉ፤ የበኣል አማልክትንም አመለኩ።

12 ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክእግዚአብሔርንተዉ፤ በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም።እግዚአብሔርንምአስቈጡት፤

13 እርሱን ትተው በኣልንና አስታሮትን አምልከዋልና

14 እግዚአብሔርበእስራኤል ላይ በመቈጣቱ ለሚዘርፏቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸው ላሉ ጠላቶቻቸው ሸጣቸው።

15 እስራኤላውያን ለውጊያ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉእግዚአብሔርአስቀድሞ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረውና እንደ ማለው ይሸነፉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ ትከፋባቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እጅግ ተጨነቁ።

16 እግዚአብሔርምከእነዚህ ወራሪዎች የሚያድኗቸውን መሳፍንትአስነሣ፤

17 እስራኤላውያን ግን ሌሎችን አማልክት ተከትለው አመነዘሩ፤ ሰገዱላቸውም እንጂ መሳፍንታቸውን አልሰሙም። አባቶቻቸውእግዚአብሔርንበመታዘዝ በሄዱበት መንገድ ሳይሆን፣ አባቶቻቸውየእግዚአብሔርንሕግ በመከተል ከሄዱበት መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ።

18 እግዚአብሔርመሳፍንትን ባሰነሣላቸው ቍጥር ከመስፍኑ ጋር ስለሚሆን፣ እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስእግዚአብሔርከጠላቶቻቸው ያድናቸው ነበር፤ ከጠላቶቻቸው ሥቃይና መከራ ሲደርስባቸው በሚጮኹበት ጊዜ እግዚአብሔር ይራራላቸው ነበር።

19 መስፍኑ ከሞተ በኋላ ግን ሕዝቡ ሌሎችን አማልክት በመከተል፣ እነርሱን በማገልገልና በማምለክ ከአባቶቻቸው ይልቅ ወደ ክፉ መንገድ ተመለሱ፤ ክፉ ሥራቸውንና የእልኸኝነት መንገዳቸውንም አይተውም ነበር።

20 ስለዚህእግዚአብሔርበእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እንዲህም አለ፤ “ይህ ሕዝብ ለቀደሙ አባቶቹ የሰጠሁትን ቃል ኪዳን ስለ ተላለፈ፣ እኔንም ስላልሰማ፣

21 ኢያሱ በሞተ ጊዜ ከተዋቸው በምድሪቱ ከነበሩት ሕዝቦች አንዳቸውንም እንኳ በፊታቸው አሳድጄ አላስወጣም።

22 ይህን የማደርገውም አባቶቻቸው እንዳደረጉት ሁሉ፣ እስራኤላውያንየእግዚአሔርንመንገድ የሚጠብቁ መሆን አለመሆናቸውን ለማወቅ እፈትናቸው ዘንድ እነርሱን መሣሪያ ለማድረግ ነው።”

23 ስለዚህእግዚአብሔርእነዚያን ሕዝቦች በዚያው እንዲኖሩ አደረገ፤ በኢያሱ እጅ አሳልፎ በመስጠት ወዲያውኑ አሳዶ አላስወጣቸውም።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *