መሳፍንት 5

የዲቦራ መዝሙር

1 በዚያን ዕለት ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህን ቅኔ ተቀኙ፤

2 “በእስራኤል ያሉ መሳፍንት ሲመሩ፣

ሕዝቡም በፈቃዱ ራሱን ሲያስገዛ፣

እግዚአብሔርንአመስግኑ።

3 “እናንት ነገሥታት ይህን ስሙ፤

ገዦችም አድምጡ፤

ለእግዚአብሔርእዘምራለሁ፤ ደግሜም

ለእስራኤል አምላክለእግዚአብሔርእቀኛለሁ።

4 “እግዚአብሔርሆይ፤ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣

ከኤዶም ምድርም በተነሣህ ጊዜ፣

ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዝናብ አዘነቡ፤

ደመናዎችም ውሃ አፈሰሱ።

5 ተራሮች በሲና አምላክበእግዚአብሔርፊት፣

በእስራኤልም አምላክበእግዚአብሔርፊት ተናወጡ።

6 “በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣

በኢያዔል ጊዜ መንገዶች ባድማ ሆኑ፤

ተጓዦችም በጠመዝማዛ መንገድ ሄዱ።

7 ለእስራኤል እናት ሆኜ

እኔ ዲቦራ እስክነሣ ድረስ

በእስራኤል ያለው የከተማ ኑሮ አበቃለት፤

8 አዳዲስ አማልክትን በተከተሉ ጊዜ፣

ጦርነት እስከ ከተማው በር መጣ፤

ጋሻም ሆነ ጦር፣

በአርባ ሺህ እስራኤላውያን መካከል አልተገኘም።

9 ልቤ ከእስራኤል መሳፍንት፣

ፈቃደኞችም ከሆኑ ሰዎች ጋር ነው፤

እግዚአብሔር ይመስገን።

10 “እናንት በነጫጭ አህዮች የምትጋልቡ፣

በባለ ግላስ ኮርቻ ላይ የምትቀመጡ፣

በመንገድ ላይ የምትጓዙ፣

በውሃ ምንጮች ዙሪያ ያለውን፣

11 የዝማሬ ድምፅስሙ።

ይህምየእግዚአብሔርየጽድቅ ሥራ፣

ጦረኞቹም በእስራኤል ያደረጉትን ያስታውሳል።

“ከዚያምየእግዚአብሔርሕዝቦች፣

ወደ ከተማዪቱበሮች ወረዱ፤

12 ‘ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፤ ንቂ፤

ንቂ፤ ንቂ፤ ቅኔም ተቀኚ፤

የአቢኒኤል ልጅ ባራቅ ሆይ፤ ተነሣ፤

ምርኮኞችህንም ማርከህ ውሰድ’ አሉ።

13 የቀሩትም ሰዎች፣

ወደ መኳንንቱ ወረዱ፤የእግዚአብሔርሕዝብ፣ እንደ ኀያል ጦረኛ ወደ እኔ መጣ።

14 መሠረታቸው ከአማሌቅ የሆነ አንዳንዶች

ከኤፍሬም መጡ፤ ብንያም አንተን ከተከተሉ ሰዎች ጋር ነበር፤

የጦር አዛዥች ከማኪር፣

የሥልጣን በትር የያዙም ከዛብሎን ወረዱ።

15 የይሳኮር መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤

ይሳኮርም ራሱ ወደ ሸለቆው ከኋላው

በመከተል፣ ከባርቅ ጋር ነበረ።

በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብ

ምርምር ነበር።

16 በበጎች ጒረኖመካከል ለምን ተቀመጥህ?

መንጎችን የሚጠራውን ፉጨት ለመስማት ነውን?

በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብ

ምርምር ነበር።

17 ገለዓድ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፤

ዳን ለምን በመርከብ ውስጥ ዘገየ?

አሴር በጠረፍ ቀረ፤

በባሕሩ ዳርቻም ተቀመጠ።

18 የዛብሎን ሰዎች ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ

የንፍታሌም ሰዎች እንደዚሁ በምድሪቱ ኰረብታዎች አደረጉ።

19 “ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤

የከነዓን ነገሥታት፣ በመጊዶ ውሆች”

አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፤

ብርም ሆነ ሌላ ምርኮ ተሸክመው አልሄዱም።

20 ከሰማያት ከዋክብት ተዋጉ፤

በአካሄዳቸውም ሲሣራን ገጠሙት።

21 ጥንታዊው ወንዝ፣ የቂሶን ወንዝ፣

የቂሶን ወንዝ ጠርጐ ወሰዳቸው፤

ነፍሴ ሆይ፤ በኀይል ገሥግሺ

22 የፈረሶች ኮቴ ድምፅ በኀይል ተሰማ፤

ጋለቡ፤ በኀይልም ፈጥነው ጋለቡ።

23 የእግዚአብሔርመልአክ፣ ‘ሜሮዝን ርገሙ፤’

‘ሕዝቧንም አብራችሁ ርገሙ፤

ከኀያላን ሰልፍእግዚአብሔርንለመርዳት፣

በእግዚአብሔርም ጐን ለመቆም አልመጡምና’ አለ።

24 ‘የቄናዊው የሔቤር ሚስት ኢያዔል፣

ከሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን፤

በድንኳን ከሚኖሩ ሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን።

25 ውሃ ለመነ፤ ወተት ሰጠችው፤

ለመኳንንት በሚገባ ዕቃ፣ እርጎ አቀረበችለት።

26 እጇዋ ካስማ ያዘ፤

ቀኝ እጇም የሠራተኛ መዶሻ ጨበጠ፤

ሲሣራን መታችው፤ ራሱንም ተረከከችው፤

ክፉኛ ወጋችው፤ ጆሮ ግንዱን በሳችው።

27 በእግሯ ሥር ተደፋ፤ ወደቀ፤

በዚያም ተዘረረ፤ በእግሯ ሥር ተደፋ፤

ወደቀ፤ በተደፋበት በዚያ ወደቀ፤

ሞተም።

28 “የሲሣራ እናት በመስኮት ተመለከተች፤

በዐይነ ርግቡ ቀዳዳም ጮኻ ተጣራች፤

‘ለምን ሠረገላው ሳይመጣ ዘገየ?

የሠረገሎቹስ ድምፅ ለምን ጠፋ?’ አለች።

29 ብልሃተኞች ወይዛዝርቷም መለሱላት፤

እርሷ ግን ለራሷ እንዲህ አለች፤

30 ‘ምርኮ አግኝተው እየተከፋፈሉ፣

እያንዳንዱም ሰው አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረዶች እየወሰደ አይደለምን?

ይህ ሁሉ ምርኮ፣ በቀለም ያጌጡ ልብሶች

ለሲሣራ ደርሰውት፣

በጌጣጌጥ የተጠለፉ ልብሶች ለአንገቴ

ይዞልኝ እየመጣ አይደለምን?’

31 “እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ይጥፉ፤

አንተን የሚወዱህ ግን፣ የንጋት ፀሐይ

በኀይል እንደሚወጣ እንዲያ ይሁኑ።”

ከዚያም በኋላ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *