ከክፉ ዓለም ለመዳን የቀረበ ጸሎት
ለመዘምራን አለቃ፤ በስምንተኛው ቅኝት የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ደግ ሰው የለምና አንተው ድረስልኝ!
ከሰዎችም መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም።
2 እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤
በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ፤
3 ሸንጋዩን ከንፈር ሁሉ፣
ነገር የምታበዛውንም ምላስእግዚአብሔርያጥፋ!
4 እነዚህም፣ “በአንደበታችን እንረታለን፤
ከንፈራችን የእኛ ነው፤ጌታችንስ ማነው?”
የሚሉ ናቸው።
5 እግዚአብሔር፣“ስለ ድኾች መከራ፣
ስለ ችግረኞችም ጩኸት፣
አሁን እነሣለሁ፤
በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል።
6 የእግዚአብሔርቃል የጠራ ቃል ነው፤
ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣
በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው።
7 እግዚአብሔርሆይ፤ አንተ ትጠብቀናለህ፤
ከዚህም ትውልድ ለዘላለም ትከልለናለህ።
8 በሰዎች ዘንድ ክፋት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ፣
ዐመፀኞች በየአቅጣጫው በዛቻ ይዞራሉ።