በጭንቅ ጊዜ የቀረበ ጸሎት
ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር በሸሚኒት
1 እግዚአብሔርሆይ፤ በቍጣህ
አትገሥጸኝ፤
በመዓትህም አትቅጣኝ።
2 እግዚአብሔርሆይ፤ ዐቅመ ቢስ ነኝና ማረኝ፤
እግዚአብሔርሆይ፤ ዐጥንቶቼ ተናግተዋልና ፈውሰኝ።
3 ነፍሴ እጅግ ታውካለች፤
እስከ መቼ፤ አንተእግዚአብሔርሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል?
4 እግዚአብሔርሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤
ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤
5 በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤
በሲኦልስማን ያመሰግንሃል?
6 ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ፤
ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤
መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ።
7 ዐይኖቼ በሐዘን ብዛት ደክመዋል፤
ከጠላቶቼም ሁሉ የተነሣ ማየት ተስኖአቸዋል።
8 እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፤ ከእኔ ራቁ፤
እግዚአብሔርየልቅሶዬን ድምፅ ሰምቶአልና።
9 እግዚአብሔርልመናዬን አድምጦአል፤
እግዚአብሔርጸሎቴን ይቀበላል።
10 ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤ እጅግም ይደነግጣሉ፤
በመጡበት ይመለሳሉ፤ ድንገትም ይዋረዳሉ።