1 ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ።
2 በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው።
3 ለእነርሱም፣ “የኢየሩሳሌም በሮች ፀሓይ ሞቅ እስክትል ድረስ አይከፈቱም፤ በር ጠባቂዎቹ ዘብ በሚቆሙበት ጊዜ ሁሉ፣ በሮቹን ይዝጓቸው፤ መወርወሪያም ያደርጉባቸው፣ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዶቹን በየጥበቃ ቦታቸው፣ አንዳንዶቹን ደግሞ በየቤታቸው አጠገብ እንዲቆሙ መድቡ” አልኋቸው።
ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ዝርዝር
4 ከተማዪቱ ታላቅና ሰፊ ነበረች፤ የሚኖርባት ሕዝብ ግን ጥቂት ሲሆን፣ ቤቶች ገና አልተሠሩባትም ነበር።
5 ስለዚህ መኳንንቱን፣ ሹማምቱና ተራውን ሕዝብ ሰብስቤ በየቤተ ሰቡ ይመዘገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን በልቤ አኖረ። ወደ ምድራቸው ለመመለስ የመጀመሪያ የሆኑትን ሰዎች የትውልድ ሐረግ መዝገብ አገኘሁ፤ ተጽፎ ያገኘሁትም ይህ ነው።
6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደየራሳቸው ከተሞች ተመለሱ፤
7 የተመለሱትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከአዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከሚስጴሬት፣ ከበጉዋይ፣ ከነሑምና ከበዓና ጋር ነው።
የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር፤
8 ከፋሮስ ዘሮች 2,172
9 ከሰፋጥያስ ዘሮች 372
10 ከኤራ ዘሮች 652
11 ከኢያሱና ከኢዮአብ ዘር የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ዘሮች 2,818
12 ከኤላም ዘሮች 1,254
13 ከዛቱዕ ዘሮች 845
14 ከዘካይ ዘሮች 760
15 ከቢንዊ ዘሮች 648
16 ከቤባይ ዘሮች 628
17 ከዓዝጋድ ዘሮች 2,322
18 ከአዶኒቃም ዘሮች 667
19 ከበጉዋይ ዘሮች 2,067
20 ከዓዲን ዘሮች 655
21 በሕዝቅያስ የትውልድ ሐረግ ከአጤር ዘሮች 98
22 ከሐሱም ዘሮች 328
23 ከቤሳይ ዘሮች 324
24 ከሐሪፍ ዘሮች 112
25 ከገባዖን ዘሮች 95
26 ከቤተ ልሔምና ከነጦፋ ሰዎች 188
27 ከዓናቶት ሰዎች 128
28 ከቤት አዝሞት ሰዎች 42
29 ከቂርያትይዓሪም፣ ከከፊራና ከብኤሮት ሰዎች 743
30 ከራማና ከጌባ ሰዎች 621
31 ከማክማስ ሰዎች 122
32 ከቤቴልና ከጋይ ሰዎች 123
33 ከሌላው ናባው ሰዎች 52
34 ከሌላው ኤላም ዘሮች 1,254
35 ከካሪም ዘሮች 320
36 ከኢያሪኮ ዘሮች 345
37 ከሎድ፣ ከሐዲድና ከኦኖም ዘሮች 721
38 ከሴናዓ ዘሮች 3,930
39 ካህናቱ፦
በኢያሱ ቤተ ሰብ መስመር ከዮዳኤ ዘሮች 973
40 ከኢሜር ዘሮች 1,052
41 ከፋስኮር ዘሮች 1,247
42 ከካሪም ዘሮች 1,017
43 ሌዋውያኑ፦
በቀድምኤል በኩል በሆዳይዋ የትውልድ መስመር የኢያሱ ዘሮች 74
44 መዘምራኑ፦
ከአሳፍ ዘሮች 148
45 በር ጠባቂዎቹ፦
ከሰሎም፣ ከአጤር፣
ከጤልሞን፣ ከዓቁብ፣ ከሐጢጣና ከሶባይ ዘሮች 138
46 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦
ከሲሐ፣ ከሐሡፋ፣ ከጠብዖት ዘሮች፣
47 ከኬራስ፣ ከሲዓ፣ ከፋዶን፣
48 ከልባና፣ ከአጋባ፣ ከሰምላይ ዘሮች፣
49 ከሐናን፣ ከጌዴል፣ ከጋሐር ዘሮች፣
50 ከራያ፣ ከረአሶን፣ ከኔቆዳ ዘሮች፣
51 ከጋሴም፣ ከዖዛ፣ ከፋሴሐ ዘሮች
52 ከቤሳይ፣ ከምዑኒም፣ ከንፉሰሲም ዘሮች፣
53 ከበቅቡቅ፣ ከሐቀፋ፣ ከሐርሑር ዘሮች፣
54 ከበስሎት፣ ከምሒዳ፣ ከሐርሻ ዘሮች፣
55 ከቦርቆስ፣ ከሲሣራ፣ ከቴማ ዘሮች፣
56 ከንስያ፣ ከሐጢፋ ዘሮች።
57 የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦
የሶጣይ፣ የሶፌሬትና፣ የፍሩዳ ዘሮች፣
58 የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጊዴል ዘሮች፣
59 የሰፋጥያስ፣ የሐጢል፣ የፈከራት ዘሮች፣ የሐፂቦይምና የአሞን ዘሮች።
60 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አሽከሮች ዘሮች 392
61 ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የተመለሱ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ዘሮቻቸው ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፤
62 የዳላያ፣ የጦብያ፣ የኔቆዳ ዘሮች 642
63 ከካህናቱ መካከል፦
የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቶአል፤
64 እነዚህ የየቤተ ሰብ ትውልድ ሐረጋቸውን ከመዝገብ ለማግኘት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው ከክህነት ተከለከሉ።
65 ስለዚህም አገረ ገዡ በኡሪምና በቱሚም አገልግሎት የሚሰጥ ካህን እስኪነሣ ድረስ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።
66 የማኅበሩ ቍጥር በሙሉ 42,360 ነበር፤
67 ይህ 7,337 የወንድና የሴት አገልጋዮቻቸውን አይጨምርም፤ 245 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው።
68 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣
69 435 ግመሎችና 6,720 አህዮችም ነበሯቸው።
70 አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዡም 1,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ።
71 ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ2,200 የብር ምናን ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።
72 የቀረው ሕዝብ ባጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ2,000 የብር ምናንና 67 አልባሰ ተክህኖ ነበር።
73 ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ።
ዕዝራ ሕጉን አነበበ
ሰባተኛው ወር በደረሰና እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው በተቀመጡ ጊዜ፣