የተሸነፉ ነገሥታት ስም ዝርዝር
1 እንግዲህ እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸውና ከዮርዳኖስ ማዶ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን የዓረባን ክፍል በሙሉ ይዞ፣ ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ የሚዘልቀውን ግዛታቸውን የወሰዱባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤
2 መቀመጫውን በሐሴቦን አድርጎ የገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፣
ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ላይ ካለችው ከአሮዔር ማለት ከሸለቆው መካከል አንሥቶ፣ የአሞናውያን ወሰን እስከ ሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ገዝቶአል፤ ይህም የገለዓድን እኩሌታ ይጨምራል።
3 እንዲሁም ከኪኔሬት ባሕርእስከ ሙትባሕር ያለውን ምሥራቃዊውን ዓረባ፣ እስከ ቤት የሺሞትና ከዚያም በስተ ደቡብ እስከ ፈስጋ ተራራ ግርጌ ድረስ ገዝቶአል።
4 መቀመጫውን በአስታሮትና በኤድራይ አድርጎ የገዛውና ከመጨረሻዎቹ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነው የባሳን ንጉሥ ዐግ፣
5 የአርሞንዔምን ተራራ፣ ሰልካንን፣ ባሳንን ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ድንበሮች እንዲሁም ከገለዓድ እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ወሰን ድረስ ገዝቶአል።
6 የእግዚአብሔርባሪያ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ድል አደረጉ፤የእግዚአብሔርባሪያ ሙሴም ምድራቸውን ለሮቤል፣ ለጋድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጣቸው።
7 እንግዲህ ኢያሱና እስራኤላውያን ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ድል ያደረጓቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ ግዛታቸውም በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ ካለው ከበኣልጋድ ተነሥቶ በምዕራብ ሴይር እስካለው እስከ ሐላቅ ተራራ ይደርሳል፤ ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ምድር እንደ ነገዳቸው አከፋፈል ለእስራኤላውያን በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው፤
8 ይህም ተራራማው አገር፤ በስተ ምዕራብ ያለው የኰረብታ ግርጌ፣ ዓረባ፣ የተራራው ሸንተረሮች፣ ምድረ በዳውና ነጌብ ማለት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው፤ ነገሥታቱም እነዚህ ናቸው፤
9 የኢያሪኮ ንጉሥ፣ አንድ፤
ቤቴል አጠገብ ያለችው የጋይ ንጉሥ፣ አንድ፤
10 የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ አንድ፤
የኬብሮን ንጉሥ፣ አንድ፤
11 የየርሙት ንጉሥ፣ አንድ፤
የለኪሶ ንጉሥ፣ አንድ፤
12 የዔግሎን ንጉሥ፣ አንድ፤
የጌዝር ንጉሥ፣ አንድ፤
13 የዳቤር ንጉሥ፣ አንድ፤
የጌድር ንጉሥ፣ አንድ፤
14 የሔርማ ንጉሥ፣ አንድ፤
የዓራድ ንጉሥ፣ አንድ፤
15 የልብና ንጉሥ፣ አንድ፤
የዓዶላም ንጉሥ፣ አንድ፤
16 የመቄዳ ንጉሥ፤ አንድ፤
የቤቴል ንጉሥ፣ አንድ፤
17 የታጱዋ ንጉሥ፣ አንድ፤
የኦፌር ንጉሥ፣ አንድ፤
18 የአፌቅ ንጉሥ፣ አንድ፤
የለሸሮን ንጉሥ፣ አንድ፤
19 የማዶን ንጉሥ፣ አንድ፤
የሐጾር ንጉሥ፣ አንድ፤
20 የሺምሮን ሚሮን ንጉሥ፣ አንድ፤
የአዚፍ ንጉሥ፣ አንድ፤
21 የታዕናክ ንጉሥ፣ አንድ፤
የመጊዶ ንጉሥ፣ አንድ፤
22 የቃዴስ ንጉሥ፣ አንድ፤
በቀርሜሎስ የሚገኘው የዮቅንዓም ንጉሥ፣ አንድ፤
23 በዶር ኰረብታየሚገኘው የዶር ንጉሥ፣ አንድ፤
በጌልገላ የሚገኘው የጎይም ንጉሥ፣ አንድ፤
24 የቲርሳ ንጉሥ፣ አንድ፤
እነዚህ በድምሩ ሠላሳ አንድ ነገሥታት ናቸው።