ኢዮብ 25

በልዳዶስ

1 ሹሐዊውም በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ፤

2 “ገዢነትና ግርማ የእግዚአብሔር ናቸው፤

በሰማይም ከፍታ ሥርዐትን ያደርጋል።

3 ሰራዊቱ ሊቈጠር ይችላልን?

ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?

4 ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፣

ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ ይችላልን?

5 በፊቱ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፣

ከዋክብትም ንጹሓን ካልሆኑ፣

6 ይልቁን ከብል የሚቈጠር የሰው ልጅ፣

ትል የሆነውማ ሰው ምንኛ ያንስ!”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *