ወደ አገራቸው የተመለሱ ምርኮኞች ዝርዝር
1 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ማርኮ ከወሰዳቸው መካከል ከምርኮ ተመልሰው ወደየራሳቸው ከተሞች ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት የአገሩ ልጆች እነዚህ ናቸው፤
2 የመጡትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከሠራያ፣ ከረዕላያ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከመሴፋር፣ ከበጉዋይ፣ ከሬሁም፣ ከበዓና ጋር ነበር።
የተመለሱት የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፤
3 የፋሮስ ዘሮች 2,172
4 የሰፋጥያስ ዘሮች 372
5 የኤራ ዘሮች 775
6 ከኢያሱና ከኢዮአብ ዘር የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ዘሮች 2,812
7 የኤላም ዘሮች 1,254
8 የዛቱዕ ዘሮች 945
9 የዘካይ ዘሮች 760
10 የባኒ ዘሮች 642
11 የቤባይ ዘሮች 623
12 የዓዝጋድ ዘሮች 1,222
13 የአዶኒቃም ዘሮች 666
14 የበጉዋይ ዘሮች 2,056
15 የዓዲን ዘሮች 454
16 የሕዝቅያስ ልጅ የአጤር ዘሮች 98
17 የቤሳይ ዘሮች 323
18 የዮራ ዘሮች 112
19 የሐሱም ዘሮች 223
20 የጋቤር ዘሮች 95
21 የቤተ ልሔም ሰዎች 123
22 የነጦፋ ሰዎች 56
23 የዓናቶት ሰዎች 128
24 የዓዝሞት ዘሮች 42
25 የቂርያትይዓሪም፣ የከፊራና የብኤሮት ዘሮች 743
26 የራማና የጌባ ዘሮች 621
27 የማክማስ ሰዎች 122
28 የቤቴልና የጋይ ሰዎች 223
29 የናባው ዘሮች 52
30 የመጌብስ ዘሮች 156
31 የሌላው ኤላም ዘሮች 1,254
32 የካሪም ዘሮች 320
33 የሎድ፣ የሐዲድና 725
34 የኢያሪኮ ሰዎች 345
35 የሴናዓ ዘሮች 3,630
36 ካህናቱ፦
ከኢያሱ ቤተ ሰብ የዮዳኤ ዘሮች 973
37 የኢሜር ዘሮች 1,052
38 የፋስኮር ዘሮች 1,247
39 የካሪም ዘሮች 1,017
40 ሌዋውያኑ፦
በሆዳይዋ በኩል የኢያሱና የቀድምኤል ዘሮች 74
41 መዘምራኑ፦
የአሳፍ ዘሮች 128
42 የቤተ መቅደሱ በረኞች፦
የሰሎም፣
የአጤር፣ የጤልሞን፣
የዓቁብ፣ የሐጢጣና የሶባይ ዘሮች 139
43 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦
የሲሐ፣
የሐሡፋና የጠብዖት ዘሮች፤
44 የኬራስ፣ የሲዓ፣ የፋዶን ዘሮች፤
45 የልባና፣ የአጋባ፣ የዓቁብ ዘሮች፤
46 የአጋብ፣ የሰምላይ፣ የሐናን ዘሮች፤
47 የጌዴል፣ የጋሐር፣ የራያ ዘሮች፤
48 የረአሶን፣ የኔቆዳ፣ የጋሴም ዘሮች፤
49 የዖዛ፣ የፋሴሐ፣ የቤሳይ ዘሮች፤
50 የአስና፣ የምዑናውያን፣ የንፉሰሲም ዘሮች፤
51 የበቅቡቅ፣ የሐቁፋ፣ የሐርሑር ዘሮች፤
52 የበስሎት፣ የምሒዳ፣ የሐርሳ ዘሮች፤
53 የበርቆስ፣ የሲሣራ፣ የቴማ ዘሮች፤
54 የንስያና የሐጢፋ ዘሮች፤
55 የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦
የሶጣይ፣ የሶፌሬት፣ የፍሩዳ ዘሮች፤
56 የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጌዴል ዘሮች፤
57 የሰፋጥያስ፣ የሐጢል፣ የፈክራት፣ የሐፂ
ቦይም፣ የአሚ ዘሮች፤
58 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች 392
59 ከዚህ የሚከተሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር ከተሞች የመጡ ናቸው፤ ነገር ግን ቤተ ሰቦቻቸው የእስራኤል ዘር መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፤
60 የዳላያ፣
የጦብያና የኔቆዳ፣ ዘሮች 652
61 ከካህናቱ መካከል የኤብያ፣ የአቆስና የቤርዜሊ ዘሮች፤ ቤርዜሊ በዚህ ስም ሊጠራ የቻለው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ልጅ አግብቶ ስለ ነበር ነው።
62 እነዚህ በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የቤተ ሰባቸውን ዝርዝር ፈለጉ፤ ነገር ግን ማግኘት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው፣ ከክህነት አገልግሎት ተገለሉ።
63 አገረ ገዡም በኡሪምና በቱሚም እግዚአብሔርን የሚጠይቅ ካህን እስኪነሣ ድረስ፣ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።
64 ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ብዛት 42,360 ነበረ፤
65 ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 200 ወንድና ሴት ዘማሪዎችም ነበሯቸው።
66 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣
67 435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው።
68 በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ ጊዜ፣ አንዳንድ የቤተ ሰብ መሪዎች በቀድሞው ቦታ እንደ ገና ለሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት በበጎ ፈቃድ ስጦታ አደረጉ።
69 እንደየችሎታቸውም 61,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 5,000 ምናንብር፣ 100 ልብሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።
70 ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ መዘምራኑ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ፤ የቀሩት እስራኤላውያንም በየከተሞቻቸው ተቀመጡ።