ደም መብላት ስለ መከልከሉ
1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤
2 “ለአሮንና ለልጆቹ፣ ለእስራኤላውያንም ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እግዚአብሔር(ያህዌ)ያዘዘው ይህ ነው፤
3 ማንኛውም እስራኤላዊ በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈር ውጭ በሬ፣በግ ወይም ፍየል ቢያርድ፣
4 በእግዚአብሔር(ያህዌ)ማደሪያ ፊትለእግዚአብሔር(ያህዌ)መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፣ ያ ሰው በከንቱ ደም እንዳፈሰሰ ይቈጠራል፤ ደም በማፍሰሱም ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ።
5 እስራኤላውያን የሚሠዉትን መሥዋዕት ወደእግዚአብሔር(ያህዌ)የሚያመጡበት ምክንያት ከዚሁ የተነሣ ነው። ይህንም ካህኑ ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥተውለእግዚአብሔር(ያህዌ)የኅብረት መሥዋዕትበማድረግ ያቅርቡ።
6 ካህኑም ደሙን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባለውበእግዚአብሔር(ያህዌ)መሠዊያ ላይ ይርጭ፤ ሥቡንምእግዚአብሔርን(ያህዌ)ደስ የሚያሰኝ ሽታ እንዲሆን ያቃጥል።
7 ከዚህ በፊት ላመነዘሩባቸው አጋንንትከእንግዲህ ወዲህ ማንኛውንም መሥዋዕት ሊሠዉ አይገባም። ይህ ለእነርሱና ከእነርሱ በኋላ ለሚነሣው ትውልድ ሁሉ የዘላለም ሥርዐት ይሁን።’
8 “እንዲህም በላቸው፤ ‘የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ፣
9 ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍለእግዚአብሔር(ያህዌ)ባያቀርብ፣ ያ ሰው ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ።
10 “ ‘ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደም ቢበላ፣ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ፤
11 የፍጡር ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ በመሠዊያ ላይ ለሕይወታችሁ ማስተስረያ እንዲሆን ደሙን ሰጥቻችኋለሁ፤ ለሰውም ሕይወት ስርየት የሚያስገኝ ደም ነው።
12 ስለዚህ እስራኤላውያንን፣ “ከእናንተ ማንም ደም አይብላ፤ በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛም ቢሆን ደም አይብላ” አልሁ።
13 “ ‘እንዲበላ የተፈቀደውን ማንኛውንም እንስሳ ወይም ወፍ አድኖ የያዘ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደሙን ከውስጡ ያፍስስ፤ ዐፈርም ያልብሰው፤
14 የማንኛውም ፍጡር ሕይወት ደሙ ነውና። ስለዚህ እስራኤላውያንን፣ “የፍጡር ሁሉ ሕይወት ደሙ ነውና የማንኛውንም ፍጡር ደም አትብሉ፤ የበላው ሰው ሁሉ ተለይቶ ይጥፋ” አልኋቸው።
15 “ ‘ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የዘነጠለውን የበላ ማንኛውም የአገር ተወላጅ ወይም መጻተኛ ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ በሥርዐቱ መሠረት እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
16 ልብሱን ባያጥብ፣ ሰውነቱንም ባይታጠብ ግን ኀጢአት ሠርቶአልና ይጠየቅበታል።’ ”