ዘሌዋውያን 19

ልዩ ልዩ ሕግጋት

1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤

2 “ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ጉባኤ እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፤ ‘እኔእግዚአብሔርአምላካችሁ(ያህዌ ኤሎሂም)ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።

3 “ ‘ከእናንተ እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፤ ሰንበታቴን ጠብቁ፤ እኔእግዚአብሔርአምላካችሁ(ያህዌ ኤሎሂም)ነኝ።

4 “ ‘ወደ ጣዖታት ዘወር አትበሉ፤ ወይም ከቀለጠ ብረት ለራሳችሁ አማልክት አትሥሩ፤ እኔእግዚአብሔርአምላካችሁ(ያህዌ ኤሎሂም)ነኝ።

5 “ ‘የኅብረት መሥዋዕትለእግዚአብሔር(ያህዌ)በምታቀርቡበት ጊዜ፣ መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት እንዲያገኝላችሁ አድርጋችሁ አቅርቡ።

6 መሥዋዕቱም ባቀረባችሁት ዕለት ወይም በማግሥቱ ይበላ፤ እስከ ሦስተኛው ቀን የተረፈ ማንኛውም ነገር ይቃጠል።

7 በሦስተኛውም ቀን ቢበላ ርኩስ ነው፤ ተቀባይነትም የለውም።

8 ከመሥዋዕቱ የሚበላ ማንኛውም ሰውለእግዚአብሔር(ያህዌ)የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና ይጠየቅበታል፤ ያም ሰው ከወገኑ ተለይቶ ይጥፋ።

9 “ ‘የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ፣ በእርሻችሁ ዳርና ዳር ያለውን አትጨዱ፤ ቃርሚያውንም አትልቀሙ።

10 የወይንህን እርሻ አትቃርም፤ የወደቀውንም አትልቀም፤ ለድኾችና ለመጻተኞች ተውላቸው፤ እኔእግዚአብሔርአምላካችሁ(ያህዌ ኤሎሂም)ነኝ።

11 “ ‘አትስረቁ፤

“ ‘አትዋሹ፤

“ ‘ከእናንተ አንዱ ሌላውን አያታል።

12 “ ‘በስሜ በሐሰት አትማሉ፤ በዚህም የአምላካችሁን(ኤሎሂም)ስም አታርክሱ፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

13 “ ‘ባልንጀራህን አታጭበርብር፤ አትቀማውም፤

“ ‘የሙያተኛውን ደመወዝ ሳትከፍል አታሳድር።

14 “ ‘ደንቈሮውን አትርገም፤ በዐይነ ስውሩም ፊት ዕንቅፋት አታኑር፤ ነገር ግን አምላክህን(ኤሎሂም)ፍራ፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

15 “ ‘ፍርድ አታዛቡ፤ ለድኻው አታድላለት፤ ለትልቁም ሰው ልዩ አክብሮት አትስጥ፤ ለብርቱው አታዳላ፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በትክክል ፍረድ።

16 “ ‘በሕዝብህ መካከል ሐሜት አትንዛ፤

“ ‘የባልንጀራህን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም ነገር አታድርግ፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

17 “ ‘ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ የበደሉ ተካፋይ እንዳትሆን ባልንጀራህን በግልጽ ገሥጸው።

18 “ ‘ወገንህን አትበቀል፤ ወይም ምቀኛ አትሁንበት፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

19 “ ‘ሥርዐቴን ጠብቁ፤

“ ‘የተለያዩ እንስሳትን አታዳቅል፤

“ ‘በዕርሻህ ላይ ሁለት ዐይነት ዘር አትዝራ፤

“ ‘ከሁለት ዐይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።

20 “ ‘አንድ ሰው ለሌላ ከታጨች ሴት ባሪያ ጋር ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ ሴቲቱም ያልተዋጀች ወይም ነጻ ያልወጣች ብትሆን ይቀጣል፤ ነገር ግን ሴቲቱ ነጻ ስላልወጣች አይገደሉም።

21 ሰውየውም ለበደል መሥዋዕት የሚሆን አንድ አውራ በግ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍለእግዚአብሔር(ያህዌ)ያምጣ።

22 ካህኑም በበደል መሥዋዕቱ አውራ በግ፣ ሰውየው ስለ ሠራው ኀጢአትበእግዚአብሔር(ያህዌ)ፊት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።

23 “ ‘ወደ ምድሪቱ ገብታችሁ ማንኛውንም ዐይነት ፍሬ የሚሰጥ ዛፍ በምትተክሉበት ጊዜ፣ ፍሬው ለመብላት የተከለከለ መሆኑን ዕወቁ፤ ለሦስት ዓመትም የተከለከለበመሆኑ አይበላ።

24 በአራተኛውም ዓመት ፍሬው ሁሉለእግዚአብሔር(ያህዌ)የተቀደሰ የምስጋና መሥዋዕት ይሆናል።

25 በአምስተኛው ዓመት ግን ፍሬውን ትበላላችሁ፤ በዚህም ሁኔታ ፍሬው ይበዛላችኋል፤ እኔእግዚአብሔርአምላካችሁ(ያህዌ ኤሎሂም)ነኝ።

26 “ ‘ደም ያለበትን ማንኛውንም ሥጋ አትብሉ፤

“ ‘ጥንቈላ ወይም አስማት አትሥሩ።

27 “ ‘የራስ ጠጒራችሁን ዙሪያ አትከርከሙ፤ ጢማችሁንም አሳጥራችሁ አትቊረጡ።

28 “ለሞተ ሰው ሰውነታችሁን አትንጩ፤ በሰውነታችሁም ላይ ንቅሳት አታድርጉ፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

29 “ ‘ምድሪቱ ወደ ግልሙትና አዘንብላ በርኵሰት እንዳትሞላ፣ ሴት ልጅህ ጋለሞታ ትሆን ዘንድ አታዋርዳት።

30 “ ‘ሰንበታቴን ጠብቁ፤ መቅደሴንም አክብሩ፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

31 “ ‘እንዳትረክሱባቸው ወደ ሙታን ጠሪዎች ዘወር አትበሉ፤ መናፍስት ጠሪዎችንም አትፈልጉ፤ እኔእግዚአብሔርአምላካችሁ(ያህዌ ኤሎሂም)ነኝ።

32 “ዕድሜው ለገፋ ተነሥለት፤ ሽማግሌውን አክብር፤ አምላክህንም(ኤሎሂም)ፍራ፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

33 “ ‘መጻተኛ በምድራችሁ ላይ አብሮአችሁ በሚኖርበት ጊዜ አትበድሉት፤

34 አብሮአችሁ የሚኖረው መጻተኛ እንደገዛ ወገናችሁ ይታይ፤ እንደ ራሳችሁም ውደዱት፤ እናንተም በግብፅ መጻተኞች ነበራችሁና፤ እኔእግዚአብሔርአምላካችሁ(ያህዌ ኤሎሂም)ነኝ።

35 “ ‘በመስፈሪያ ወይም በሚዛን አታጭ በርብሩ።

36 እውነተኛ መለኪያ፣ እውነተኛ መመዘኛ፣ እውነተኛ የኢፍመስፈሪያ፣ እውነተኛ የኢንመስፈሪያ ይኑራችሁ። ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔእግዚአብሔርአምላካችሁ(ያህዌ ኤሎሂም)ነኝ።

37 “ ‘ሥርዐቴንና ሕጌን ሁሉ ጠብቁ፤ ተከተሏቸውም፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።’ ”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *