ዘሌዋውያን 21

ለካህናት የተሰጠ መመሪያ

1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤

2 ነገር ግን የቅርብ ዘመዶቹ ስለሆኑት እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድ ልጁ፣ ሴት ልጁ፣ ወይም ወንድሙ፣

3 እንዲሁም ባለማግባቷ ከእርሱ ጋር ስለ ምትኖር እኅቱ ራሱን ሊያረክስ ይችላል።

4 ከእርሱ ጋር በጋብቻ ለሚዛመዱትግን ራሱን አያርክስ።

5 “ ‘ካህናት ዐናታቸውን አይላጩ፤ የጢማቸውን ዙሪያ አይላጩ፤ ሰውነታቸውንም አይንጩ፤

6 ለአምላካቸው(ኤሎሂም)የተቀደሱ ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም(ኤሎሂም)ስም አያርክሱ።ለእግዚአብሔር(ያህዌ)በእሳት የሚቀርበውን መሥዋዕት የአምላካቸውን(ኤሎሂም)ምግብ ስለሚያቀርቡ ቅዱሳን ይሁኑ።

7 “ ‘ካህናት በዝሙት የረከሱትንም ሆነ ከባሎቻቸው የተፋቱትን ሴቶች አያግቡ፤ለእግዚአብሔር(ያህዌ)የተቀደሱ ናቸውና።

8 የአምላክህን(ኤሎሂም)ምግብ የሚያቀርብ ነውና ቀድሰው፤ እኔ የምቀድሳችሁእግዚአብሔር(ያህዌ)ቅዱስ ነኝና ቅዱስ ይሁንላችሁ።

9 “ ‘የካህን ሴት ልጅ ዝሙት አዳሪ ሆና ራሷን ብታረክስ፣ አባቷን ታዋርዳለች፤ በእሳት ትቃጠል።

10 “ ‘ከወንድሞቹ መካከል ተለይቶ በራሱ ላይ ዘይት የፈሰሰበትና የክህነት ልብስ እንዲለብስ የተቀባው ካህን የራስ ጠጒሩን አይንጭ፤ወይም ልብሱን አይቅደድ።

11 አስከሬን ወዳለበት ስፍራ አይግባ፤ ስለ አባቱም ሆነ ስለ እናቱ ራሱን አያርክስ።

12 የተቀደሰበት የአምላኩ(ኤሎሂም)የቅባት ዘይት በላዩ ስለ ሆነ የአምላኩን(ኤሎሂም)መቅደስ ትቶ በመሄድ መቅደሱን አያርክስ፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

13 “ ‘ካህኑ የሚያገባት ሴት ድንግል ትሁን።

14 ባል የሞተባትን፣ የተፋታችውን ወይም በዝሙት ዐዳሪነት የረከሰችውን ሴት አያግባ፤ ነገር ግን ከወገኖቹ መካከል ድንግሊቱን ያግባ።

15 በወገኖቹ መካከል ዘሩን አያርክስ። እርሱን የምቀድሰውእኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።’ ”

16 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤

17 “አሮንን እንዲህ በለው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ከዘርህ እንከን ያለበት ማንኛውም ሰው የአምላኩን(ኤሎሂም)ምግብ ይሠዋ ዘንድ አይቅረብ።

18 ዕውር ወይም አንካሳ፣ የፊቱ ገጽታ ወይም የሰውነቱ ቅርጽ የተበላሸ ማንኛውም የአካል ጒድለት ያለበት ሰው አይቅረብ።

19 እንዲሁም እግሩ ወይም እጁ ሽባ የሆነ፣

20 ጐባጣ ወይም ድንክ፣ ማንኛውም ዐይነት የዐይን እንከን ያለበት፣ የሚያዥ ቊስል ወይም እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ አይቅረብ።

21 ከካህኑ ከአሮን ዘር ማንኛውም ዐይነት የአካል ጒድለት ያለበት ሰውለእግዚአብሔር(ያህዌ)በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ሊያቀርብ አይምጣ፤ እንከን ያለበት ስለ ሆነ፣ የአምላኩን(ኤሎሂም)ምግብ ለማቅረብ አይምጣ።

22 እርሱም የተቀደሰውንና እጅግ ቅዱስ የሆነውን የአምላኩን(ኤሎሂም)ምግብ ይብላ።

23 ነገር ግን እንከን ያለበት ስለ ሆነ መቅደሴን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይቅረብ ወይም ወደ መሠዊያው አይጠጋ፤ የምቀድሳቸውእኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።’ ”

24 ሙሴም ይህን ለአሮን፣ ለልጆቹና ለእስራኤላውያን ሁሉ ነገራቸው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *