ዘሌዋውያን 22

1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤

2 “እስራኤላውያን ቀድሰው ለእኔ የለዩትን ቅዱስ መሥዋዕት በአክብሮት ባለመያዝ፣ ቅዱስ ስሜን እንዳያረክሱ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

3 “እንዲህም በላቸው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ከዘርህ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ ያልሆነ ማንኛውም ሰው፣ እስራኤላውያንለእግዚአብሔር(ያህዌ)ለይተው ወዳቀረቡት ቅዱስ መሥዋዕት ቢቀርብ ያ ሰው ከፊቴ ይወገድ፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

4 “ ‘ከአሮን ዘር ተላላፊ የቈዳ በሽታያለበት ወይም ከሰውነቱ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ማንኛውም ሰው እስኪነጻ ድረስ ቅዱሱን መሥዋዕት አይብላ፤ እንዲሁም በአስከሬን የረከሰውን ነገር ወይም የዘር ፈሳሽ ያለበትን ሰው ቢነካ፣

5 ወይም በደረቱ የሚሳብ የሚያረክስ ነገርን ወይም የሚያረክስ ማንኛውንም ሰው ቢነካ፣ የቱንም ዐይነት ርኵሰት ቢሆን፣

6 እንዲህ ያለውን ማንኛውንም ነገር የሚነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ሰውነቱንም በውሃ ካልታጠበ፣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን መሥዋዕት አይብላ።

7 ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ የተቀደሰውን መሥዋዕት መብላት ይችላል፤ ምግቡ ነውና።

8 እንዳይረክስ ማንኛውንም ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የዘነጠለውን አይብላ፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

9 “ ‘ካህናት ትእዛዛቴን በመናቅ በደለኛ እንዳይሆኑና እንዳይሞቱ ይጠብቋቸው፤ የምቀድሳቸውእኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

10 “ ‘ከካህን ቤተ ሰብ በቀር የካህኑ እንግዳም ሆነ ቅጥር ሠራተኛ የተቀደሰውን መሥዋዕት አይብላ።

11 ነገር ግን ካህኑ በገንዘብ የገዛው ወይም በቤቱ የተወለደ ባሪያ ቢኖረው፣ ያ ባሪያ ከካህኑ ድርሻ መብላት ይችላል።

12 የካህን ልጅ፣ ካህን ያልሆነ ሌላ ሰው ካገባች፣ ከተቀደሰው መሥዋዕት መብላት አትችልም።

13 ይሁን እንጂ የካህኑ ልጅ ባሏ ቢሞት ወይም ብትፋታ፣ ልጆችም ባይኖሩዋትና እንደ ልጅነት ጊዜዋ በአባቷ ቤት ለመኖር ብትመለስ፣ ከአባቷ ድርሻ መብላት ትችላለች፤ ያልተፈቀደለት ሰው ግን ከተቀደሰው መሥዋዕት መብላት አይችልም።

14 “ ‘ማንኛውም ሰው ባለማወቅ የተቀደሰውን መሥዋዕት ቢበላ፣ የመሥዋዕቱን አንድ አምስተኛ ጨምሮ ለካህኑ ይተካ።

15 እስራኤላውያንለእግዚአብሔር(ያህዌ)የሚያቀርቡትን የተቀደሰ መሥዋዕት ካህናቱ አያርክሱት፤

16 ይህንኑ የተቀደሰ መሥዋዕት እንዲበሉና ቅጣት የሚያስከትል በደል እንዲፈጽሙ አያድርጉ፤ የምቀድሳቸው እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

ለእግዚአብሔር መቅረብ የማይገባው መሥዋዕት

17 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤

18 “ለአሮን፣ ለልጆቹና ለእስራኤላውያን በሙሉ እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ከእናንተ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ስእለት ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማበርከትለእግዚአብሔር(ያህዌ)የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርብ ቢሆን፣

19 መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት እንዲኖረው ከላም ወገን ወይም ከበጎች ወይም ከፍየሎች እንከን የሌለበትን ተባዕት ያቅርብ።

20 እንከን ያለበትን ማንኛውንም ነገር አታቅርቡ፤ መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት አይኖረውምና።

21 ማንኛውም ሰው ስእለት ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማበርከት ከላም ወይም ከበግ ወይም ከፍየል መንጋለእግዚአብሔር(ያህዌ)የኅብረት መሥዋዕትሲያቀርብ፣ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ፍጹም የሆነውንና ነውር የሌለበትን ያቅርብ።

22 ዕውር ወይም ሰባራ ወይም ጒንድሽ ወይም ማንኛውንም ዐይነት እከክ ወይም ቋቊቻ ወይም የሚመግል ቊስል ያለበትን እንስሳለእግዚአብሔር(ያህዌ)አታቅርቡ፤ ከነዚህ መካከል የትኛውንም በመሠዊያው ላይ በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁለእግዚአብሔር(ያህዌ)አታቅርቡ።

23 አካሉ ከመጠን በላይ የረዘመን ወይም ያጠረን በሬወይም በግ የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ፤ ይሁን እንጂ ስእለት ለመፈጸም ተቀባይነት አይኖረውም፤

24 አባለዘሩ የተቀጠቀጠ ወይም የተኰላሸ፣ የተሰነጠቀ ወይም የተቈረጠ ማንኛውንም እንስሳለእግዚአብሔር(ያህዌ)አታቅርቡ፤ እነዚህንም በምድራችሁ አትሠው።

25 እንደነዚህ ያሉትን እንስሳት ከባዕዳን በመቀበል ለአምላካችሁ(ኤሎሂም)ምግብ አድርጋችሁ አታቅርቡ፤ ነውር ስላለባቸው ፍጹም አይደሉምና ተቀባይነት አይኖራቸውም።’ ”

26 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤

27 “ጥጃ ወይም የበግ ግልገል ወይም የፍየል ግልገል በሚወለድበት ጊዜ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቈይ፤ ከስምንተኛው ቀን ጀምሮ ግን ተቀባይነት ያለውለእግዚአብሔር(ያህዌ)በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ይሆናል።

28 ላምን ከጥጃዋ፣ በግንም ከግልገሏ ጋር በአንድ ቀን አትረዱ።

29 “ለእግዚአብሔር(ያህዌ)የምስጋና መሥዋዕት በምታቀርቡበት ጊዜ፣ መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት እንዲኖረው አድርጋችሁ አቅርቡት።

30 መሥዋዕቱ በዚያኑ ዕለት ይበላ፤ ለሚቀጥለውም ቀን አታሳድሩ፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

31 “ትእዛዛቴን ጠብቁ፤ አድርጓቸውም፤ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

32 ቅዱሱን ስሜን አታርክሱ፤ እኔ ቅዱስ መሆኔ በእስራኤላውያን ዘንድ ይታወቅ፤ የምቀድሳችሁእኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

33 አምላካችሁ(ኤሎሂም)እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔእግዚአብሔር(ያህዌ)ነኝ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *