ስለ ስጦታ የወጣ ሕግ
1 እግዚአብሔር(ያህዌ)ሙሴን እንዲህ አለው፤
2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ማንኛውም ሰው ተመጣጣኙን ዋጋ በመክፈልለእግዚአብሔር(ያህዌ)ሰውን ለመስጠት የተለየ ስእለት ቢሳል፣
3 ዕድሜው ከሃያ እስከ ሥልሳ ዓመት ለሆነ ወንድ፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅልሚዛን መሠረት፣ ግምቱ አምሳ ጥሬ ሰቅልብር ይሁን።
4 ለሴት ከሆነ ግምቱ ሠላሳ ሰቅልይሁን።
5 ዕድሜው ከአምስት እስከ ሃያ ዓመት ለሆነ ሰው፣ ወንድ ከሆነ ግምቱ ሃያ ሰቅል፣ሴት ከሆነች ግምቷ ዐሥር ሰቅልይሁን።
6 ዕድሜው ከአንድ ወር እስከ አምስት ዓመት ለሆነ ሰው፣ ወንድ ከሆነ ግምቱ አምስት ሰቅልጥሬ ብር፣ ለሴት ከሆነ ሦስት ሰቅልጥሬ ብር ይሁን።
7 ሥልሳ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ለሆነ ሰው፣ ወንድ ከሆነ ግምቱ ዐሥራ አምስት ሰቅል፣ ሴት ከሆነች ዐሥር ሰቅል ይሁን።
8 ስእለት የተሳለው ድኻ ከሆነና ግምቱን መክፈል ካልቻለ ግን፣ ለስጦታ ያሰበውን ሰው ወደ ካህኑ ያምጣ፤ ካህኑም የተሳለው ሰው ባለው ዐቅም መሠረት መክፈል የሚገባውን ይተምንለታል።
9 “ ‘ሰውየው የተሳለውለእግዚአብሔር(ያህዌ)መሥዋዕት ሆኖ መቅረብ የሚችል እንስሳ ከሆነ፣ እንዲህ ያለውለእግዚአብሔር(ያህዌ)የተሰጠ እንስሳ የተቀደሰ ይሆናል።
10 ሰውየው መልካም የሆነውን እንስሳ መልካም ባልሆነው፣ መልካም ያልሆነውንም መልካም በሆነው አይለውጥ ወይም አይተካ፤ አንዱን እንስሳ በሌላው ከተካም ሁለቱ የተቀደሱ ይሆናሉ።
11 እንስሳው በሥርዐቱ መሠረት የረከሰ፣ለእግዚአብሔርም(ያህዌ)መሥዋዕት ሆኖ መቅረብ የማይገባው ከሆነ፣ ሰውየው እንስሳውን ወደ ካህኑ ያቅርብ፤
12 መልካም ቢሆን ወይም ባይሆን፣ ካህኑ ዋጋውን ይወስን፤ የካህኑም ውሳኔ የጸና ይሆናል።
13 ባለቤቱ እንስሳውን መዋጀት ከፈለገ ግን፣ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛ መጨመር አለበት።
14 “ ‘አንድ ሰው ቤቱንለእግዚአብሔር(ያህዌ)ይሆን ዘንድ ቢቀድስ፣ መልካም ቢሆን ወይም ባይሆን ካህኑ ዋጋውን ይተምን፤ ካህኑም የተመነው ዋጋ የጸና ይሆናል።
15 ቤቱን የቀደሰው ሰው መልሶ ሊዋጀው ከፈለገ ግን፣ የዋጋውን አንድ አምስተኛ በዋጋው ላይ መጨመር አለበት፤ ቤቱም ዳግመኛ የራሱ ይሆናል።
16 “ ‘አንድ ሰው ከወረሰው ርስት ላይለእግዚአብሔር(ያህዌ)የዕርሻ መሬት ቢቀድስ፣ ዋጋው የሚተመነው ለመሬቱ በሚያስፈልገው ዘር መጠን ይሆናል፤ ይኸውም ለአንድ ሆሜርመስፈሪያ የገብስ ዘር አምሳ ሰቅል ጥሬ ብር ነው።
17 ሰውየው ዕርሻውን የቀደሰው በኢዮቤልዩ ዓመት ከሆነ፣ የተወሰነው ዋጋ አይለወጥም።
18 ዕርሻውን የሚቀድሰው ከኢዮቤልዩ በኋላ ከሆነ ግን፣ ካህኑ ዋጋውን የሚተምነው እስከሚመጣው የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ባሉት ዓመታት ቍጥር ልክ ነው፤ የተተመነውም ዋጋ ይቀነሳል።
19 ዕርሻውን የቀደሰው ሰው መልሶ መዋጀት ከፈለገ፣ በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛ መጨመር አለበት፤ ከዚያ በኋላ ዕርሻው እንደ ገና የራሱ ይሆናል።
20 ዕርሻውን ባይዋጅ ወይም ለሌላ ሰው አሳልፎ ቢሸጥ፣ ከዚያ በኋላ ሊዋጀው አይችልም።
21 እርሻው በኢዮቤልዩ በሚለቀ ቅበት ጊዜለእግዚአብሔር(ያህዌ)እንደተሰጠ ዕርሻ ተቈጥሮ ቅዱስና የካህናቱንብረት ይሆናል።
22 “ ‘አንድ ሰው የወረሰው ርስት ያልሆነውን፣ በገንዘቡ የገዛውን የዕርሻ መሬትለእግዚአብሔር(ያህዌ)ቢቀድስ፣
23 ካህኑ የእርሻውን መሬት ዋጋ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ባለው ጊዜ መጠን ይተምናል፤ ሰውየው የተተመነውን ዋጋለእግዚአብሔር(ያህዌ)የተቀደሰ አድርጎ በዚያኑ ዕለት ይክፈል።
24 በኢዮቤልዩ ዓመትም የዕርሻው መሬት የቀድሞው ባለ ርስት ለነበረው፣ ለሸጠውም ሰው ይመለሳል።
25 እያንዳንዱ ዋጋ የሚተመነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ልክ ሆኖ አንዱ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው።
26 “ ‘የእንስሳት በኵር ቀድሞውኑየእግዚአብሔር(ያህዌ)ስለ ሆነ፣ ማንም ሰው የእንስሳትን በኵርለእግዚአብሔር(ያህዌ)መቀደስ አይችልም፤ በሬምሆነ በግየእግዚአብሔር(ያህዌ)ነውና።
27 እንስሳው ርኩስ ከሆነ ግን፣ ባለቤቱ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛ ጨምሮ ሊዋጀው ይችላል፤ የማይዋጀው ከሆነ ግን በተተመነው ዋጋ ይሸጥ።
28 “ ‘ነገር ግንለእግዚአብሔር(ያህዌ)ተለይቶ የተሰጠማንኛውም ነገር፦ ሰውም ሆነ እንስሳ ወይም በውርስ የተገኘ መሬት አይሸጥም፤ አይዋጅምም።ለእግዚአብሔር(ያህዌ)የተሰጠ ማንኛውም ነገር እጅግ የተቀደሰ ነውና።
29 “ ‘እንዲጠፋ የተወሰነ ማንኛውም ሰው አይዋጅም፤መገደል አለበት።
30 “ ‘ከዕርሻ ምርትም ሆነ ከዛፍ ፍሬ፣ ማንኛውም ከምድሪቱ የሚገኝ ዐሥራትየእግዚአብሔር(ያህዌ)ነው፤ለእግዚአብሔርም(ያህዌ)የተቀደሰ ነው።
31 አንድ ሰው ከዐሥራቱ የትኛውንም መዋጀት ቢፈልግ፣ በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛ መጨመር አለበት።
32 ከቀንድ ከብቶች፣ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ የሚወጣው ዐሥራት ከእረኛ በትር በታች ከሚያልፉት ዐሥረኛው እንስሳ ይሆናል፤ ይህምለእግዚአብሔር(ያህዌ)የተቀደሰ ነው።
33 ሰውየው መልካም የሆነውን መልካም ካልሆነው አይለይ ወይም አይተካ፤ አንዱን በሌላው ቢተካ ግን ሁለቱም እንስሳት የተቀደሱ ይሆናሉ፤ ሊዋጁም አይችሉም።
34 እግዚአብሔር(ያህዌ)በሲና ተራራ ላይ በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ የሰጣቸው ትእዛዛት እነዚህ ናቸው።