እግዚአብሔርን ውደድ፤ ታዘዘውም
1 እንግዲህ አምላክህንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ውደድ፤ ግዴታውን፣ ሥርዐቱን፣
ሕጉንና ትእዛዙን ሁል ጊዜ ጠብቅ።
2 የአምላካችሁንየእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ተግሣጽ ይኸውም ግርማውን፣ ብርቱ እጁንና የተዘረጋች ክንዱን ያዩትና የተለማመዱት ልጆቻችሁ ሳይሆኑ እናንተ እንደሆናችሁ ዛሬ አስታውሱ፤
3 በግብፅ መካከል፣ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖንና በመላው አገሩ ላይ ያደረጋቸውን ምልክቶችና የሠራቸውን ነገሮች፣
4 በግብፃውያን ሰራዊት፣ በፈረሶቻቸውና በሠረገሎቻቸው ላይ፣ እናንተን ባሳደዷችሁ ጊዜ በቀይ ባሕርውሃ እንዴት እንዳሰጠማቸውናእግዚአብሔር(ያህዌ)ፈጽሞ እንዴት እንዳጠፋቸው አስታውሱ፤
5 ከምድረ በዳው አንሥቶ እዚህ እስከምትደርሱ ድረስ፣ ለእናንተ ያደረገላችሁን ያዩት ልጆቻችሁ አልነበሩም፤
6 የሮቤል ልጅ የኤልያብ ልጆች የሆኑትን ዳታንና አቤሮንን ከነቤተ ሰቦቻቸው፣ ከነድንኳናቸውና ከነእንስሳታቸው በመላው እስራኤል መካከል ምድር እንዴት አፏን ከፍታ እንደዋጠቻቸው እነርሱ አላዩም።
7 የእናንተ ዐይኖች ግንእግዚአብሔር(ያህዌ)ያደረጋቸውን ሥራዎች ሁሉ አይተዋል።
8 ስለዚህ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደምትወርሷት ምድር ለመግባትና ለመያዝ ብርታት እንድታገኙ፣ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ፤
9 ለአባቶቻቸውና ለዘሮቻቸውእግዚአብሔር(ያህዌ)ሊሰጣቸው በማለላቸው፣ በዚያች ማርና ወተት በምታፈሰው ምድር ረጅም ዕድሜ ትኖሩ ዘንድ፣
10 የምትገባባት ምድር እንደ ወጣህባትና ዘርህን ዘርተህባት በእግርህ ውሃ እንዳጠጣሃት የአትክልት ቦታ እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም።
11 ዮርዳኖስን ተሻግረህ ልትወርሳት ያለችው ምድር ግን፣ ከሰማይ ዝናብ የምትጠጣ፣ ተራሮችና ሸለቆች ያሉባት ምድር ናት።
12 ይህች ምድር አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)የሚንከባከባት፣ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ የአምላክህየእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ዐይን ምንጊዜም የማይለያት ናት።
13 ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፣ ይኸውም አምላካችሁንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ብትወዱና በፍጹም ልባችሁ፣ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል በታማኝነት ብትጠብቁ፣
14 እህልህን፣ ወይንህንና ዘይትህን እንድትሰበስብ የበልጉንና የክረምቱን ዝናብ በምድርህ ላይ በየወቅቱ አዘንባለሁ።
15 በሜዳ ላይ ለከብቶችህ ሣር እሰጣለሁ፤ አንተም ትበላለህ፤ ትጠግባለህም።
16 ተጠንቀቁ አለበለዚያ ተታላችሁ ሌሎች አማልክትን ታመልካላችሁ፤ ትሰግዳላችሁም።
17 ከዚያምየእግዚአብሔር(ያህዌ)ቊጣ በላያችሁ ይነዳል፤ እርሱም ዝናብ እንዳይዘንብ፣ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተምእግዚአብሔር(ያህዌ)ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ።
18 እነዚህን ቃሎቼን፣ በልባችሁና በአእምሮአችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፣ በግምባራችሁም ላይ ይሁኑ።
19 ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ ቤት ስትቀመጥ፣ መንገድ ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣ ስለ እነዚሁ አጫውታቸው።
20 በቤትህ መቃኖችና በግቢህ በሮች ላይ ጻፋቸው፤
21 ይህን ካደረጋችሁ፣እግዚአብሔር(ያህዌ)ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር የእናንተና የልጆቻችሁ ዘመን ከምድር በላይ ያሉ ሰማያትን ርቀት ያህል ይሆናል።
22 አምላክህንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ትወዱ ዘንድ፣ በመንገዶቹም ሁሉ ትሄዱና ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ እንድትከተሏቸው የምሰጣችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቁ፣
23 ከዚያምእግዚአብሔር(ያህዌ)እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል፤ እናንተም፣ ከእናንተ ይልቅ ታላላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ታስለቅቃላችሁ።
24 በእግራችሁ የምትረግጡት ስፍራ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፣ ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕርይደርሳል።
25 ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም፤ አምላካችሁእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማስደንገጣችሁንና መፈራታችሁን በምትሄዱበት በየትኛውም ምድር ሁሉ ላይ ያሳድራል።
26 እነሆ፤ ዛሬ በረከትንና መርገምን በፊታችሁ አኖራለሁ፤
27 በረከቱ ዛሬ የምሰጣችሁን የአምላካችሁንየእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ትእዛዞች ስትፈጽሙ ሲሆን፣
28 መርገሙ ደግሞ፣ የአምላካችሁንየእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ትእዛዞች የማትፈጽሙ፣ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ለመከተል እኔ ከማዛችሁ መንገድ የምትወጡ ከሆነ ነው።
29 ልትወርሳት ወደ ምትሄድባት ምድር አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በሚያስገባህ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፣ መርገሙን ደግሞ በጌባል ተራራ ላይ ታሰማለህ።
30 እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተ ምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊት ለፊት፣ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን?
31 አምላካችሁእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በሚሰጣችሁ ምድር ትገቡባትና ትወርሷት ዘንድ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ስለ ሆነ፣ ምድሪቱን ወርሳችሁ በምትኖሩባት ጊዜ፣
32 ዛሬ በፊታችሁ እኔ ያስቀመጥኋቸውን ሥርዐቶችና ሕጎች ሁሉ ለመፈጸም ተጠንቀቁ።