ፋሲካ
1 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በአቢብ ወር ከግብፅ በሌሊት ስላወጣህ፣ የአቢብን ወር ጠብቅ፤ የአምላክህንየእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ፋሲካ አክብርበት።
2 እግዚአብሔር(ያህዌ)ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ ከበግና ከፍየል ወይም ከመንጋህ አንዱን እንስሳ ለአምላክህለእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ፋሲካ አድርገህ ሠዋው።
3 ከቦካ ቂጣ ጋር አትብላው፤ ከግብፅ የወጣኸው በችኮላ ነውና ከግብፅ የወጣህበትን ጊዜ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ታስብ ዘንድ የመከራ ቂጣ ሰባት ቀን ብላ።
4 በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማናቸውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቈይ አታድርግ።
5 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በሚሰጥህ በማናቸውም ከተማ ፋሲካን መሠዋት አይገባህም፤
6 ነገር ግን ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በሚመርጠው ስፍራ፣ ፀሓይ ስትጠልቅ ምሽቱላይ ከግብፅ በወጣህበት ሰዓት ዓመታዊ መታሰቢያ በዚያ ፋሲካን ሠዋ።
7 ሥጋውንም ጠብሰህ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በሚመርጠው ስፍራ ብላ፤ ሲነጋም ወደ ድንኳንህ ተመልሰህ ሂድ።
8 ስድስት ቀን ያልቦካ ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛው ቀን ለአምላክህለእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)የተቀደሰ ጉባኤ አድርግ፤ ሥራም አትሥራበት።
የመከር በዓል
9 እህልህን ማጨድ ከምትጀምርበት ዕለት አንሥቶ ሰባት ሳምንት ቊጠር፤
10 ከዚያም በኋላ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በባረከህ መጠን፣ በፈቃድህ የምታመጣውን ስጦታ በማቅረብ በመከሩ በዓል አምላክህንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)አክብር።
11 አንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፣ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችህ፣ በከተሞችህ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ በመካከልህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህበእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ፊት ደስ ይበላችሁ።
12 አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስታውስ፤ ይህንንም በጥንቃቄ ጠብቅ።
የዳስ በዓል
13 የእህልህን ምርት ከዐውድማህ፣ ወይንህንም ከመጭመቂያህ ከሰበሰብህ በኋላ፣ የዳስን በዓል ሰባት ቀን አክብር።
14 በበዓልህ አንተ፣ ወንድና ሴት ልጅህ፣ ወንድና ሴት አገልጋይህ፣ በከተማው ያለ ሌዋዊ፣ መጻተኛ፣ አባት አልባውና መበለቲቱ ደስ ይበላችሁ።
15 እግዚአብሔር(ያህዌ)በመረጠው ስፍራ ለአምላክህለእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በዓሉን ሰባት ቀን አክብር፤ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በእህል ምርትህና በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክሃል፤ ደስታህም ፍጹም ይሆናል።
16 ወንዶችህ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ፣ በቂጣ በዓል፣ በመከር በዓልና በዳስ በዓል ላይ፣ እርሱ በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህበእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ፊት ይቅረቡ፤ ማንም ሰውበእግዚአብሔር(ያህዌ)ፊት ባዶ እጁን አይቅረብ።
17 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በባረከህ መጠን እያንዳንዱ እንደ ችሎታው ይስጥ።
ስለ ፍርድ አሰጣጥ
18 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ።
19 ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጒቦም አትቀበል፤ ጒቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።
20 በሕይወት እንድትኖርና አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ፣ ቅን ፍርድን ብቻ ተከተል።
ሌሎችን አማልክት ስለ ማምለክ
21 ለአምላክህለእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የአሼራን ምስል የዕንጨት ዐምድ አታቁም።
22 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)የሚጠላውን ማምለኪያ ዐምድ ለአንተ አታቁም።