ዘዳግም 30

ወደ እግዚአብሔር በመመለስ የሚገኝ በረከት

1 በፊትህ ያስቀመጥሁት ይህ በረከትና መርገም ሁሉ በአንተ ላይ ሲመጣና አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በትኖህ በምትኖርበት አሕዛብ መካከል ሆነህ ወደ ልብህ ተመልሰህ ነገሮቹን በምታስተውልበት ጊዜ፣

2 እንዲሁም ዛሬ እኔ በማዝህ ሁሉ መሠረት አንተና ልጆችህ ወደ አምላካችሁ ወደእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ተመልሳችሁ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ እርሱን ስትታዘዙ፣

3 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ምርኮህን ይመልስልሃል፤ ይራራልሃልም፤ አንተን ከበተነበት አሕዛብ መካከል እንደ ገና ይሰበስብሃል።

4 ከሰማይ በታች እጅግ ሩቅ ወደ ሆነ ምድር ብትጋዝ እንኳ፣ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ከዚያ ይሰበስብሃል፤ መልሶም ያመጣሃል።

5 የአባቶችህ ወደሆነችው ምድር ያመጣሃል፤ አንተም ትወር ሳታለህ። ከአባቶችህ ይበልጥ ያበለጽግሃል፤ ያበዛሃልም።

6 አምላክህንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ እንድትወደው፣ በሕይወትም እንድትኖር፣ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)የአንተንና የዘርህን ልብ ይገርዛል።

7 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ይህን ርግማን ሁሉ በሚጠሉህና በሚያሳድዱህ ጠላቶችህ ላይ ያደርገዋል።

8 አንተም ተመልሰህለእግዚአብሔር(ያህዌ)ትታዘዛለህ፤ ዛሬ እኔ የማዝህን ትእዛዝ ሁሉ ትጠብቃለህ።

9 ከዚያም አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በእጅህ ሥራ ሁሉና በወገብህ ፍሬ፣ በእንስሳትህ ግልገሎችና በምድርህ ሰብል እጅግ ያበለጽግሃል። በአባቶችህ ደስ እንደ ተሰኘ ሁሉ፣እግዚአብሔር(ያህዌ)አንተንም በማበልጸግ ደስ ይለዋልና።

10 ይህም የሚሆነው፣ አምላክህንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ከታዘዝህና በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዐቱን በመጠበቅ፣ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ስትመለስ ነው።

ሕይወትን ወይም ሞትን ስለ መምረጥ

11 በዛሬው ዕለት የምሰጥህ ትእዛዝ ይህን ያህል አስቸጋሪ ወይም ከአንተ የራቀች አይደለችም።

12 “እንድንፈጽማት አምጥቶ ይነግረን ዘንድ፣ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል?” እንዳትል፣ በላይ በሰማይ አይደለችም።

13 ደግሞም፣ “እንድናደርጋት አምጥቶ ይነግረን ዘንድ፣ ማን ባሕሩን ይሻገራል?” እንዳትልም፣ ከባሕር ማዶ አይደለችም።

14 ነገር ግን ቃሉ ለአንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ታደርገውም ዘንድ በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው።

15 እነሆ፤ ዛሬ ሕይወትንና በረከትን፣ ሞትንና ጥፋትን በፊትህ አኑሬአለሁ።

16 አምላክህንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)እንድትወድ፣ በመንገዱም እንድትሄድና ትእዛዙን፣ ሥርዐቱንና ሕጉን እንድትጠብቅ አዝሃለሁ፤ ከዚያም በሕይወት ትኖራለህ፤ ትበዛለህም፤ አምላክህምእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ትወርሳት ዘንድ በምትገባበት ምድር ይባርክሃል።

17 ዳሩ ግን ልብህ ወደ ኋላ ቢመለስና ባትታዘዝ፣ ለሌሎች አማልክት ለመስገድ ብትታለልና ብታመልካቸው፣

18 በርግጥ እንደምትጠፉ እኔ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ብዙ አትኖሩባትም።

19 ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና ርግማንን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ። እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤

20 ይኸውም አምላክህንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)እንድትወድ፣ ቃሉን እንድታደምጥና ከእርሱ ጋር እንድትጣበቅ ነው። ምክንያቱምእግዚአብሔር(ያህዌ)ሕይወትህ ነው፣ ለአባቶችህ፣ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር ረጅም ዕድሜ ይሰጥሃል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *