ዐሥርቱ ትዕዛዛት
1 ሙሴ እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “እስራኤል ሆይ፤ በዛሬዋ ዕለት በጆሮአችሁ የምነግራችሁን ሥርዐትና ሕግ ስሙ፤ አጥኗቸው፤ በጥንቃቄም ጠብቋቸው።
2 አምላካችንእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ገብቶአል።
3 እግዚአብሔር ይህን ቃል ኪዳን የገባውም ከአባቶቻችን ጋር ሳይሆን፣ ዛሬ እዚህ በሕይወት ከምንገኘው ከእኛ ከሁላችን ጋር ነው።
4 እግዚአብሔር(ያህዌ)እናንተን በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ፊት ለፊት አነጋገራችሁ።
5 እናንተ ግን እሳቱን በመፍራት ወደ ተራራው ስላል ወጣችሁ፣ በዚያን ጊዜየእግዚአብሔርን(ያህዌ)ቃል ለእናንተ እነግራችሁ ዘንድ እኔበእግዚአብሔርና(ያህዌ)በእናንተ መካከል ቆምሁ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤
6 “ከባርነት ምድር፣ ከግብፅ ያወጣሁህ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)እኔ ነኝ።
7 “ከእኔ በቀርሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
8 በላይ በሰማይ፣ በታች በምድር ላይ፣ ባለው ወይም ከምድር በታች ውሃ ውስጥ በሚኖር በማንኛውም ዐይነት ምስል ለራስህ ጣዖትን አታብጅ፤
9 እኔ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)፣ የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። ለእነርሱ አትስገድላቸው፤ ወይም አታምልካቸው።
10 ለሚወዱኝና ትእዛዛቴን ለሚጠብቁ ግን እስከ ሺህ ትውልድ ቸርነትንና ፍቅርን እገልጣለሁ።
11 “እግዚአብሔር(ያህዌ)ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን ሳይቀጣው አይቀርምና፤ የአምላክህንየእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ስም በከንቱ አታንሣ።
12 “አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ባዘዘህ መሠረት የሰንበትን ቀን ቀድሰህ አክብረው።
13 ስድስት ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አከናውን።
14 ሰባተኛው ቀን ግን የአምላክህየእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ሰንበት ነው። በዚህም ቀን አንተም ሆንህ ወንድ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ አገልጋይህም ሆነ ሴት አገልጋይህ በሬህ፣ አህያህ ወይም ማናቸውም እንሰሳህ፣ ወይም ደግሞ በደጅህ ያለ እንግዳ ምንም ዐይነት ሥራ አትሥሩ። ይህም አንተ እንዳረፍህ ሁሉ ወንድ አገልጋይህም ሆነ ሴት አገልጋይህ እንዲያርፉ ነው።
15 በግብፅ ሳለህ አንተም ባሪያ እንደ ነበርህ፣ ከዚያም አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ እንዳወጣህ አስታውስ፤ ስለዚህ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)የሰንበትን ቀን ታከብረው ዘንድ አዘዘህ።
16 “አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ፣ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር።
17 “አትግደል።
18 “አታመንዝር።
19 “አትስረቅ።
20 “በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
21 “የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ። በባልንጀራህ ቤትም ሆነ በመሬቱ፣ በወንድ ሆነ በሴት አገልጋዩ፣ በበሬውም ሆነ በአህያው ወይም የእርሱ በሆነው ነገር ላይ ዐይንህን አትጣል።”
22 እግዚአብሔር(ያህዌ)በተራራው ላይ በእሳቱ፣ በደመናውና በድቅድቁ ጨለማ ውስጥ ለማኅበራችሁ ሁሉ በከፍተኛ ድምፅ የተናገራችሁ ትእዛዛቱ እነዚህ ናቸው፤ የጨመረውም ሌላ የለም፤ ትእዛዛቱንም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጽፎ ሰጠኝ።
23 ተራራው በእሳት ሲቃጠል፣ ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ እናንተ የየነገዶቻችሁ አለቆችና ሽማግሌዎቻችሁም በሙሉ ወደ እኔ ዘንድ መጣችሁ፤
24 እንዲህም አላችሁ፤ “አምላካችንእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ክብሩንና ግርማውን አሳይቶናል፤ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል። እግዚአብሔር አነጋግሮትም እንኳ፣ ሰው በሕይወት ሊኖር እንደሚችል በዛሬው ቀን አይተናል።
25 ከእንግዲህ የአምላካችንንየእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ድምፅ ብንሰማ እንሞታለን፤ ይህችም ታላቅ እሳት ፈጽማ ታጠፋናለች፤ ታዲያ ለምን እንሙት?
26 ለመሆኑ ከእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር እኛ እንደ ሰማነው ሁሉ፣ የሕያው እግዚአብሔርን(ኤሎሂም)ድምፅ ሰምቶ በሕይወት ለመኖር የቻለ ከሥጋ ለባሽ ማን አለ?
27 አንተ ቅረብ፤ አምላካችንእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)የሚለውን ሁሉ አዳምጥ፤ ከዚያም አምላካችንእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)የሚነግርህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንሰማለን፤ እናደርገዋለንም።”
28 ይህን ስትነግሩኝእግዚአብሔር(ያህዌ)ሰማ፤እግዚአብሔርም(ያህዌ)አለኝ፤ “ይህ ሕዝብ ምን እንዳለህ ሰምቻለሁ፤ ያሉትም ሁሉ መልካም ነው።
29 ታዲያ ለእነርሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም እንዲሆንላቸው፣ እኔን እንዲፈሩና ሁል ጊዜ ትእዛዞቼን ሁሉ እንዲጠብቁ እንደዚህ ያለ ልብ ቢኖራቸው ምናለ!
30 ሄደህ ወደየድንኳናቸው እንዲመለሱ ንገራቸው።
31 አንተ ግን እንዲወርሷት በምሰጣቸው ምድር እንዲጠብቋቸው የምታስተምራቸውን ትእዛዞች፣ ሥርዐቶችና ሕጎች ሁሉ እንድሰጥህ እዚሁ ከእኔ ዘንድ ቈይ።”
32 እንግዲህ አምላካችሁእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ያዘዛችሁን ለመፈጸም ተጠንቀቁ፤ ቀኝም ግራም አትበሉ።
33 በምትወርሷት ምድር በሕይወት ለመኖር እንድትችሉ፣ መልካም እንዲሆንላችሁና ዕድሜያችሁም እንዲረዝም፣ አምላካችሁእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።