አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ
1 ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር እንድትጠብቁት አስተምራችሁ ዘንድ አምላካችሁእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)የሰጠኝ ትእዛዝ፣ ሥርዐትና ሕግ ይህ ነው፤
2 ይኸውም፣ የምሰጣችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፣ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም፣ አንተ፣ ልጆችህና ከእነርሱ በኋላ የሚመጡት ልጆቻቸው በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ አምላካችሁንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ትፈሩት ዘንድ ነው።
3 እንግዲህ እስራኤል ሆይ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በሰጠህ ተስፋ መሠረት፣ ማርና ወተት በምታፈሰው ምድር መልካም እንዲሆንልህና እጅግ እንድትበዛ፣ ትእዛዙንም ትጠብቅ ዘንድ ጥንቃቄ አድርግ።
4 እስራኤል ሆይ ስማ፤ አምላካችንእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)አንድእግዚአብሔር(ያህዌ)ነው።
5 አምላክህንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህ ውደድ።
6 ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዛት በልብህ ያዝ።
7 ለልጆችህም አስጠናቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር።
8 በእጅህ ላይ ምልክት አድርገህ እሰራቸው፤ በግንባርህም ላይ ይሁኑ።
9 በቤትህ መቃኖች በግቢህም በሮች ላይ ጻፋቸው።
10 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ሲያስገባህ፣ በዚያም ያልሠራሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞችን፣
11 የራስህ ባልነበሩ መልካም ነገሮች ሁሉ የተሞሉ ቤቶችን ያልቈፈርሃቸውን የውሃ ጒድጓዶች፣ ያልተከልሃቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ሲሰጥህና በልተህም ስትጠግብ፣
12 ከባርነት ምድር ከግብፅ ያወጣህንእግዚአብሔርን(ያህዌ)እንዳትረሳ ተጠንቀቅ!
13 አምላክህንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)ፍራ፤ እርሱን ብቻ አገልግል፤ በስሙም ማል።
14 በዙሪያህ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን ሌሎች አማልክት አትከተል፤
15 ምክንያቱም በመካከልህ ያለው አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ቀናተኛ አምላክ(ኤሎሂም)ስለ ሆነ፣ በአንተም ላይ ቊጣው ስለሚነድ፣ ከምድር ገጽ ያጠፋሃል።
16 በማሳህ እንዳደረጋችሁት አምላካችሁንእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)አትፈታተኑት።
17 አምላካችሁእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)የሰጣችሁን ትእዛዞች፣ መመሪያዎችና ሥርዐቶች በጥንቃቄ ጠብቁ።
18 መልካም እንዲሆንልህናእግዚአብሔር(ያህዌ)ለአባቶችህ በመሐላ እንድትወርሳት፣በእግዚአብሔር(ያህዌ)ፊት ተስፋ የሰጣቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ ቀናና መልካም የሆነውን አድርግ፤
19 እግዚአብሔር(ያህዌ)በተናገረው መሠረትም ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ታስወጣለህ።
20 በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፣ “አምላካችንእግዚአብሔር(ያህዌ ኤሎሂም)ያዘዛችሁ የመመሪያዎቹ፣ የሥርዐቶቹና የሕጎቹ ትርጒም ምንድ ነው?” ብሎ በሚጠይቅህ ጊዜ፣
21 እንዲህ በለው፤ “እኛ በግብፅ የፈርዖን ባሮች ነበርን፤እግዚአብሔር(ያህዌ)ግን በብርቱ እጅ ከግብፅ አወጣን።
22 እኛ በዐይናችን እያየንእግዚአብሔር(ያህዌ)ታላላቅና አስፈሪ የሆኑ ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆችን በግብፅ፣ በፈርዖንና በመላው ቤተ ሰዎቹ ላይ አደረገ።
23 እኛን ግን ለአባቶቻችን በመሐላ ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ሊያስገባንና ሊሰጠን ከዚያ አወጣን።
24 ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ምንጊዜም መልካም እንዲሆንልንና በሕይወት እንድንኖር ይህን ሥርዐት ሁሉ እንድንፈጽም፣ አምላካችንንምእግዚአብሔርን(ኤሎሂም ያህዌ)እንድንፈራእግዚአብሔር(ያህዌ)አዘዘን።
25 እንግዲህ ይህን ሁሉ ሕግ እርሱ ባዘዘን መሠረት፣ በአምላካችንበእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ፊት ተጠንቅቀን ከጠበቅን፣ ያ ለእኛ ጽድቃችን ይሆናል።”