ዘፍጥረት 3

የሰው ውድቀት

1 እባብእግዚአብሔርአምላክ(ያህዌ ኤሎሂም)ከፈጠራቸው የዱር አራዊት ሁሉ ተንኰለኛ ነበረ፤ ሴቲቱንም፣ “በእርግጥ እግዚአብሔር(ኤሎሂም)፣ ‘በአትክልቱ ስፍራ ካሉ ዛፎች ከማናቸውም እንዳትበሉ’ ብሎአልን?” አላት።

2 ሴቲቱም እባቡን እንዲህ አለችው፤ “በአትክልቱ ስፍራ ካሉት ዛፎች ፍሬ መብላት እንችላለን፤

3 ነገር ግን እግዚአብሔር(ኤሎሂም)‘በአትክልቱ ስፍራ መካከል ከሚገኘው ዛፍ ፍሬ እንዳትበሉ፤ እንዳትነኩትም፤ አለበለዚያ ትሞታላችሁ’ ብሎአል።”

4 እባቡም ሴቲቱን እንዲህ አላት፤ “መሞት እንኳ አትሞቱም፤

5 ከፍሬው በበላችሁ ጊዜ ዐይናችሁ እንደሚከፈትና መልካምና ክፉን በማወቅ፣ እንደ እግዚአብሔር(ኤሎሂም)እንደምት ሆኑ እግዚአብሔር(ኤሎሂም)ስለሚያውቅ ነው።”

6 ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደሆነ ባየች ጊዜ፣ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከእርሷም ጋር ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።

7 የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፤ ዕራቍታቸውን መሆናቸውንም ተገነዘቡ። ስለዚህ የበለስ ቅጠል ሰፍተው አገለደሙ።

8 ቀኑ መሸትሸት ሲል፣እግዚአብሔርአምላክ(ያህዌ ኤሎሂም)በአትክልቱ ስፍራ ሲመላለስ አዳምና ሔዋን ድምፁን ሰምተውከእግዚአብሔርአምላክ(ያህዌ ኤሎሂም)ፊት በዛፎቹ መካከል ተሸሸጉ።

9 እግዚአብሔርአምላክ(ያህዌ ኤሎሂም)ግን አዳምን ተጣርቶ፣ “የት ነህ?” አለው።

10 አዳምም፣ “ድምፅህን በአትክልቱ ስፍራ ሰማሁ፤ ዕራቍቴን ስለ ሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም” ብሎ መለሰ።

11 እግዚአብሔርም፣(ያህዌ)፣ “ዕራቍትህን መሆንህን ማን ነገረህ? ‘ከእርሱ እንዳትበላ’ ብዬ ካዘዝሁህ ዛፍ በላህን?” አለው።

12 አዳምም፣ “ይህች ከእኔ ጋር እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት፣ እርሷ ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ” አለ።

13 እግዚአብሔርአምላክ(ያህዌ ኤሎሂም)ሴቲቱን፣ “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” አላት። እርሷም፣ “እባብ አሳሳተኝና በላሁ” አለች።

14 እግዚአብሔርአምላክ(ያህዌ ኤሎሂም)እባብን እንዲህ አለው፤ “ይህን ስለ ሠራህ፣

“ከከብቶችና ከዱር እንስሳት ሁሉ

ተለይተህ የተረገምህ ሁን፤

በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ በደረትህ

እየተሳብህ ትሄዳለህ፤

ዐፈርም ትበላለህ።

15 በአንተና በሴቲቱ፣

በዘርህና በዘሯ መካከል፣

ጠላትነትን አደርጋለሁ፤

እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤

አንተም ተረከዙን ትቀጠቅጣለህ።”

16 ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤

“በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤

በሥቃይም ትወልጃለሽ፤

ፍላጐትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤

እርሱም የበላይሽ ይሆናል።”

17 አዳምንም እንዲህ አለው፤ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ፣ ‘ከእርሱ አትብላ’ ብዬ ያዘዝሁህን ዛፍ በልተሃልና፣

“ከአንተ የተነሣ ምድር የተረገመች ትሁን፤

በሕይወትህ ዘመን ሁሉ

ምግብህን ጥረህ ግረህ ከእርሷ ታገኛለህ።

18 ምድርም እሾኽና አሜከላ

ታበቅልብሃለች፤

ከቡቃያዋም ትበላለህ።

19 ከምድር ስለ ተገኘህ፣

ወደ መጣህበት መሬት እስክትመለስ

ድረስ

እንጀራህን በፊትህ ላብ ትበላለህ፤

ዐፈር ነህና

ወደ ዐፈር ትመለሳለህ።”

20 አዳምምየሕያዋን ሁሉ እናት ናትና ሚስቱን ሔዋንብሎ ጠራት።

21 እግዚአብሔርአምላክ(ያህዌ ኤሎሂም)ከቈዳ ልብስ አዘጋጅቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው።

22 ከዚያምእግዚአብሔርአምላክ(ያህዌ ኤሎሂም)፣ “ሰው መልካምንና ክፉውን ለይቶ በማወቅ ረገድ አሁን ከእኛ እንደ አንዱ ሆኗል፤ አሁን ደግሞ እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ቀጥፎ እንዳይበላ፣ ለዘላለምም እንዳይኖር ይከልከል” አለ።

23 ስለዚህ የተገኘበትን ምድር እንዲያርስ፣እግዚአብሔርአምላክ(ያህዌ ኤሎሂም)ሰውን ከዔድን የአትክልት ስፍራ አስወጣው፤

24 ሰውንም ካስወጣው በኋላ፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሠይፍ ከዔድን በስተ ምሥራቅ አኖረ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *