ሳሙኤል ያደረገው የመሰነባበቻ ንግግር
1 ሳሙኤል ለመላው እስራኤል እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ያላችሁኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ።
2 ንጉሥ ሆኖ የሚመራችሁንም ሰው እነሆ፤ አግኝታችኋል። እኔም ዕድሜዬ ገፍቶአል፤ ጠጒሬም ሸብቶአል፤ ልጆቼም አብረዋችሁ አሉ፤ ከወጣትነት ጊዜዬ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስመራችሁ ቈይቻለሁ።
3 እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤በእግዚአብሔርናእርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጒቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”
4 እነርሱም፣ “አላታለልኸንም ወይም ግፍ አልሠራህብንም፤ ከማንም እጅ አንዳች ነገር አልተቀበልህም” ብለው መለሱለት።
5 ሳሙኤልም፣ “በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁእግዚአብሔርናእርሱ የቀባው ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው” አላቸው።
እነርሱም፣ “እርሱ ምስክር ነው” አሉ።
6 ከዚያም ሳሙኤል ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ሙሴንና አሮንን የመረጠ፣ የቀድሞ አባቶቻችሁንም ከግብፅ ያወጣ እግዚአብሔር ነው።
7 አሁንም ለእናንተና ለአባቶቻችሁእግዚአብሔርስላደረገው የጽድቅ ሥራ ሁሉበእግዚአብሔርፊት ስለምሟገታችሁ በዚህ ቁሙ።
8 “ያዕቆብ ወደ ግብፅ ከገባ በኋላ፣ አባቶቻችሁእግዚአብሔርእንዲረዳቸው ወደ እርሱ ጮኹ፤እግዚአብሔርምየቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲኖሩ ያደረጉትን ሙሴንና አሮንን ላከላቸው።
9 “እነርሱ ግን አምላካቸውንእግዚአብሔርንረሱት፤ ስለዚህ ለሐጾር የጦር አዛዥ ለሲሣራ፣ ለፍልስጥኤማውያንና ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ሸጣቸው።
10 እነርሱም፣ ‘ኀጢአት ሠርተናል፤እግዚአብሔርንትተን በአሊምንና አስታሮትን አምልከናል። አሁን ግን ከጠላቶቻችን እጅ ታደገን፤ እኛም አንተን እናመልካለን’ ሲሉ ወደእግዚአብሔርጮኹ።
11 ከዚያምእግዚአብሔርይሩበኣልን፣ ባርቅን፣ ዮፍታሔንና ሳሙኤልንልኮ በሰላም ትኖሩ ዘንድ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ እጅ ታደጋችሁ።
12 የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ ግን፣ ምንም እንኳ አምላካችሁእግዚአብሔርንጉሣችሁ ቢሆንም፣ ‘አይሆንም፤ የሚገዛን ንጉሥ እንፈልጋለን’ አላችሁ።
13 “አሁንም የጠየቃችሁትና የመረጣችሁት ንጉሥ ይኸው፤ እነሆ፣እግዚአብሔርበላያችሁ ንጉሥ አንግሦአል።
14 እግዚአብሔርንየምትፈሩና የምታመልኩ፣ የምትታዘዙትና በትእዛዛቱ ላይ የማታምፁ ከሆነ፣ እንዲሁም እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁንእግዚአብሔርንከተከተላችሁ መልካም ይሆንላችኋል።
15 እግዚአብሔርንየማትታዘዙና በትእዛዛቱም ላይ የምታምፁ ከሆነ ግን፣ እጁ በአባቶቻችሁ ላይ እንደ ነበረች ሁሉ በእናንተም ላይ ትሆናለች።
16 “ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤እግዚአብሔርበዐይናችሁ ፊት የሚያደርገውንም ይህን ታላቅ ነገር ተመልከቱ፤
17 አሁን የስንዴ መከር ጊዜ አይደለምን? እኔ ነጐድጓድና ዝናብ እንዲልክ ወደእግዚአብሔርእጮኻለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቃችሁበእግዚአብሔርፊት የቱን ያህል የከፋ ድርጊት እንደፈጸማችሁ ያን ጊዜ ታውቃላችሁ።”
18 ከዚህ በኋላ ሳሙኤል ወደእግዚአብሔርጮኸ፤ በዚያኑ ዕለትእግዚአብሔርነጐድጓድና ዝናብ ላከ። ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉእግዚአብሔርንናሳሙኤልን እጅግ ፈሩ።
19 ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፣ “ሌላው በደላችን ሳያንስ፣ ንጉሥ እንዲነግሥልን በመጠየቃችን ተጨማሪ ክፋት ስላደረግን እንዳንሞት፣ ለአገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደእግዚአብሔርጸልይልን” አሉት።
20 ሳሙኤልም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “አትፍሩ፤ ይህን ሁሉ ክፋት አድርጋችኋል፤ ሆኖምእግዚአብሔርንበፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂእግዚአብሔርንከመከተል ፈቀቅ አትበሉ።
21 ሊጠቅሟችሁ ወይም ሊያድኗችሁ የማይችሉ ምናምንቴ ነገሮችን አትከተሉ፤ ከንቱ ናቸውና።
22 እግዚአብሔርየራሱ ሕዝብ ያደርጋችሁ ዘንድ ስለ ወደደ፣ ስለ ታላቅ ስሙ ሲልእግዚአብሔርሕዝቡን አይተውም።
23 ከዚህም በላይ እኔ ለእናንተ ከመጸለይ ወደ ኋላ በማለትእግዚአብሔርንመበደል ከእኔ ይራቅ፤ እኔ መልካምና ቅን የሆነውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።
24 ብቻእግዚአብሔርንፍሩ፤ በፍጹም ልባችሁ በታማኝነት አምልኩት፤ ያደረገላችሁንም ታላላቅ ነገሮች አትርሱ።
25 በክፉ ሥራችሁ ብትጸኑ ግን፣ እናንተም ንጉሣችሁም ትጠፋላችሁ።”