እግዚአብሔር የሳኦልን ንጉሥነት መናቁ
1 ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ቀብቼ እንዳነግሥህ፣እግዚአብሔርየላከው እኔን ነው፤ ስለዚህከእግዚአብሔርየመጣውን መልእክት አድምጥ።
2 የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ፣ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ ስለ ተቃወሙት እቀጣቸዋለሁ።
3 አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንና ሴቱን፣ ልጁንና ሕፃኑን፣ የቀንድ ከብቱንና በጉን፣ ግመሉንና አህያውን ግደል።” ’
4 ስለዚህ ሳኦል ሰዎቹን ጥላኢም በተባለ ቦታ ሰብስቦ ቈጠራቸው፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሺህ እግረኛ ወታደሮችና ከይሁዳም ዐሥር ሺህ ሰዎች ነበሩ፤
5 ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ሄዶ በአንዲት ሸለቆ ውስጥ አደፈጠ።
6 እርሱም፣ ቄናውያንን፣ “ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡ ጊዜ፣ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ።
7 ከዚያም ሳኦል አማሌቃውያንን ከኤውላጥ አንሥቶ በምሥራቅ ግብፅ እስካለው እስከ ሱር ድረስ ወጋቸው።
8 የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው።
9 ነገር ግን ሳኦልና ሰራዊቱ አጋግን፣ ምርጥ ምርጡን በግና የቀንድ ከብት፣ የሰባውን ጥጃናጠቦት፣ መልካም የሆነውን ሁሉ ሳይገድሉ ተውት። እነዚህን ፈጽመው ለማጥፋት ፈቃደኞች አልነበሩም፤ ነገር ግን የተናቀውንና የማይጠቅመውን ሁሉ አጠፉ።
10 ከዚህ በኋላየእግዚአብሔርቃል እንዲህ ሲል ወደ ሳሙኤል መጣ፤
11 “ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ፤ እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፣ ትእዛዜንም አልፈጸመምና።” ሳሙኤልም እጅግ ተጨንቆ፣ ሌሊቱን ሁሉ ወደእግዚአብሔርጮኸ።
12 ሳሙኤልም ጠዋት ተነሥቶ በማለዳ ሳኦልን ለመገናኘት ሄደ፤ ነገር ግን፣ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ ሄዶአል፤ ለራሱ ክብር የመታሰቢያ ሐውልት በዚያ ካቆመ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወርዶአል” ተብሎ ተነገረው።
13 ሳሙኤል ባገኘው ጊዜ ሳኦል፣“እግዚአብሔርይባርክህ፤የእግዚአብሔርንትእዛዝ ፈጽሜአለሁ” አለው።
14 ሳሙኤል ግን፣ “ታዲያ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ጩኸትና የበሬዎች ግሣት ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ።
15 ሳኦልም፣ “ሰራዊቱ ከአማሌቃውያን ማርከው ያመጧቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጦቹ በጎችና በሬዎችለእግዚአብሔርለአምላክህ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳይገድሉ የተዉአቸው ናቸው፤ የቀሩትን ግን በሙሉ አጥፍተናል” ብሎ መለሰ።
16 ሳሙኤልም ሳኦልን፣ “ስማ! ትናንት ማታእግዚአብሔርየነገረኝን ልንገርህ?” አለው።
ሳኦልም፣ “ንገረኝ” ሲል መለሰለት።
17 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “በዐይንህ ፊት ታናሽ የነበርህ ብትሆንም፣ የእስራኤል ነገዶች መሪ ሆነህ የለምን?እግዚአብሔርምበእስራኤል ላይ ቀብቶ አንግሦሃል።
18 እግዚአብሔርም፣ ‘ሄደህ እነዚያን ኀጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ጨርሰህ እስክታጠፋቸውም ድረስ ውጋቸው’ ብሎ ልኮህ ነበር።
19 ታዲያእግዚአብሔርንለምን አልታዘዝህም? ለምርኮውስ ተስገብግበህበእግዚአብሔርፊት ክፉ የሆነውን ነገር ለምን አደረግህ?”
20 ሳኦልም መልሶ እንዲህ አለ፤“እግዚአብሔርታዝዣለሁ፤ እግዚአብሔር በላከኝ መሠረት ሄጃለሁ፤ አማሌቃውያንን በሙሉ አጥፍቼ ንጉሣቸውን አጋግን አምጥቻለሁ።
21 ሰራዊቱ ግን ከምርኮው ለእግዚአብሔር ከተለዩት መካከል፣ ምርጥ ምርጡን በግና በሬ፣ በጌልገላ ለአምላክህለእግዚአብሔርይሠዉ ዘንድ ወስደዋል።”
22 ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤
“ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፣እግዚአብሔር፣
በሚቃጠል ቍርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን?
እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፣
ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል።
23 ዐመፅ እንደ ጥንቈላ ያለ ኀጢአት፣
እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው። አንተየእግዚአብሔርንቃል ስለ ናቅህ፣ እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”
24 ከዚያም ሳኦል ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “ኀጢአት ሠርቻለሁ፤የእግዚአብሔርንትእዛዝና የአንተን መመሪያ ጥሻለሁ፤ ሕዝቡን ፈርቼ ስለ ነበር፣ የጠየቁኝን ታዝዣለሁ።
25 አሁንም፣ ኀጢአቴን ይቅር እንድትለኝ፣ለእግዚአብሔርምእሰግድ ዘንድ አብረኸኝ እንድትመለስ እለምንሃለሁ።”
26 ሳሙኤል ግን፣ “ከአንተ ጋር አልመለስም፤ አንተየእግዚአብሔርንቃል ንቀሃል፤እግዚአብሔርምበእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል” አለው።
27 ሳሙኤል ለመሄድ ዘወር ባለ ጊዜ፣ ሳኦል የልብሱን ጫፍ ያዘ፤ ተቀደደም።
28 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔርየእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።
29 የእስራኤል ክብር የሆነውእግዚአብሔርአይዋሽም፤ አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለምና።”
30 ሳኦልም መልሶ፣ “ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ ነገር ግን በሕዝቤ አለቆች ፊትና በእስራኤል ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህለእግዚአብሔርእሰግድ ዘንድ እባክህ አብረኸኝ ተመለስ” አለው።
31 ስለዚህ ሳሙኤል አብሮት ተመለሰ፤ ሳኦልምለእግዚአብሔርሰገደ።
32 ከዚያም ሳሙኤል፣ “የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ።
አጋግም፣ “በውኑ ሞት እንዲህ መራራ ነውን? በማለት እየተንቀጠቀጠ መጣ።
33 ሳሙኤልም፣
“ሰይፍህ ሴቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፣
እናትህም በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች”
ሲል አጋግን ጌልገላ ላይበእግዚአብሔርፊት ቈራረጠው።
34 ከዚያም ሳሙኤል ወደ አርማቴም ሄደ። ሳኦል ግን ወደ ቤቱ ወደ ሳኦል ጊብዓ ወጣ።
35 ሳሙኤል ለሳኦል ቢያለቅስለትም እንኳ እስከ ሞተበት ዕለት ድረስ ዳግመኛ ሊያየው አልሄደም፤እግዚአብሔርምሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ ተጸጸተ።