1 ሳሙኤል 2

የሐና የምስጋና ጸሎት

1 ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፤

“ልቤበእግዚአብሔርጸና፤

ቀንዴምበእግዚአብሔርከፍ ከፍ አለ፤

አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤

በማዳንህ ደስ ይለኛልና።

2 “እንደእግዚአብሔርያለ ቅዱስማንም የለም፤

ከአንተም በቀር ሌላ የለም፤

እንደ አምላካችን ያለ ዐለት የለም።

3 “ይህን ያህል በመታበይ አትናገሩ፤

እንዲህ ያለውም የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፤

እግዚአብሔርአምላክ ዐዋቂ ነውና፤

ሥራም ሁሉ በእርሱ ይመዘናል።

4 “የኀያላን ቀስቶች ተሰባብረዋል፤

ደካሞች ግን በኀይል ታጥቀዋል።

5 ጠግበው የነበሩ ለእንጀራ ሲሉ ተገዙ፤

ተርበው የነበሩ ግን እንጀራ ጠገቡ፤

መካኒቱ ሰባት ልጆች ወልዳለች፤

ብዙ ወንዶች ልጆች ወልዳ የነበረችው ግን መከነች።

6 “እግዚአብሔርይገድላል፤ ያድናልም፤

ወደ መቃብርያወርዳል፤ ያወጣልም።

7 እግዚአብሔርያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤

ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል።

8 እርሱ ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤

ምስኪኑንም ከጒድፍ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤

ከመኳንንቱ ጋር ያስቀምጣቸዋል፤

የክብር ዙፋንም ያወርሳቸዋል።

“የምድር መሠረቶችየእግዚአብሔርናቸውና፣

ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጎአል።

9 እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል፤

ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ይጣላሉ፤

“ሰው በኀይሉ ድል አያደርግም፤

10 ከእግዚአብሔርጋር የሚጣሉ ይደቃሉ፤

እርሱ ከሰማይ ያንጐደጒድባቸዋል፤

እግዚአብሔርእስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል።

“ለንጉሡ ኀይልን ይሰጣል፤

የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”

11 ከዚያ በኋላ ሕልቃና ወደ ቤቱ ወደ ራማ ሄደ፤ ብላቴናው ግን በካህኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።

የዔሊ ልጆች ክፉ ድርጊት

12 የዔሊ ልጆች ምናምንቴዎች ነበሩ፤እግዚአብሔርንምአይፈሩም ነበር።

13 በዚያን ጊዜ ካህናቱ ከሕዝቡ ጋር ባላቸው ግንኙነት የሚፈጽሙት ወግ ነበር፤ ይኸውም ማንም ሰው መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሥጋው እየተቀቀለ ሳለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለውን ሜንጦ ይዞ ይመጣል፤

14 ወደ ድስቱ ወይም ወደ ቶፋው ወይም ወደ አፍላሉ፣ ወይም ወደ ምንቸቱ ይሰደዋል። ከዚያም ካህኑ ሜንጦው ያወጣውን ማናቸውንም ሥጋ ለራሱ ይወስደዋል። ወደ ሴሎ የሚመጡትን እስራኤላውያን ሁሉ የሚያስተናግዱት በዚህ ዐይነት ነበር።

15 ነገር ግን ሥቡ ገና ከመቃጠሉ በፊት የካህኑ አገልጋይ መጥቶ መሥዋዕት የሚያቀርበውን ሰው፣ “ካህኑ ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ ስለማይቀበል፣ ለካህኑ የሚጠበስ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።

16 ሰውየውም፣ “በመጀመሪያ ሥቡ ይቃጠል፤ ከዚያ በኋላ የምትፈልገውን ትወስዳለህ” ቢለው እንኳ አገልጋዩ፣ “አይሆንም፤ አሁኑኑ ስጠኝ፤ ያለዚያ በግድ እወስዳለሁ” ይለው ነበር።

17 ለእግዚአብሔርየሚቀርበውን መሥዋዕት ይንቁ ስለ ነበር፣ ይህ የወጣቶቹ ኀጢአትበእግዚአብሔርፊት እጅግ ታላቅ ነበረ።

18 ብላቴናው ሳሙኤል ግን ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶበእግዚአብሔርፊት ያገለግል ነበር።

19 እናቱም ከባሏ ጋር ዓመታዊ መሥዋዕት ለማቅረብ በምትሄድበት ጊዜ ሁሉ ትንሽ መደረቢያ እየሠራች ይዛለት ትሄድ ነበር።

20 ዔሊም፣ “በጸሎት ባገኘችውናለእግዚአብሔርበሰጠችው ልጅ ምትክእግዚአብሔርከዚህችው ሴት ዘር ይስጥህ” እያለ ሕልቃናንና ሚስቱን ይመርቃቸው ነበር፤ ከዚያ በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር።

21 እግዚአብሔርምሐናን ባረካት፤ ፀነሰችም፤ ሦስት ወንዶች፣ ሁለት ሴቶች ልጆችም ወለደች። ብላቴናውም ሳሙኤልበእግዚአብሔርፊት አደገ።

22 በዚህ ጊዜ ዔሊ እጅግ አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹም በመላው እስራኤል ያደርጉ የነበረውን፣ በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ሴቶች ጋር ዝሙት መፈጸማቸውን ሰማ።

23 ስለዚህም እንዲህ አላቸው፤ “ስለምትፈጽሙት ክፉ ድርጊት ከመላው ሕዝብ እሰማለሁ፤ ለምን እንዲህ ያለ ነገር ታደርጋላችሁ?

24 ልጆቼ ሆይ፤ ትክክል አይደላችሁም፤በእግዚአብሔርሕዝብ መካከል ተሠራጭቶ የምሰማባችሁ ወሬ ጥሩ አይደለም።

25 አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል፣ እግዚአብሔርጣልቃ ገብቶ ይፈርዳል፤ ነገር ግን ሰውእግዚአብሔርንቢበድል፣ ማን ይማልድለታል?” ይሁን እንጂእግዚአብሔርሊያጠፋቸው ስለ ፈለገ፣ ልጆቹ የአባታቸውን ተግሣጽ አልሰሙም።

26 ብላቴናውም ሳሙኤል በአካልና በሞገስበእግዚአብሔርናበሰው ፊት እያደገ ሄደ።

በዔሊ ቤተ ሰብ ላይ የተነገረ ትንቢት

27 በዚህ ጊዜ አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘የአባትህ ቤት በግብፅ ምድር በፈርዖን እጅ በነበረ ጊዜ ራሴን ገለጥሁለት?

28 የእኔ ካህን እንዲሆን፣ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፣ ዕጣን እንዲያጥን፣ በፊቴም ኤፉድ እንዲለብስ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ አባትህን መረጥሁት። ደግሞም እስራኤላውያን በእሳት የሚያቀርቡትን ቊርባን ሁሉ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።

29 ታዲያ በማደሪያዬ እንዲቀርብ ያዘዝሁትን መሥዋዕትና ቊርባን የናቃችሁ ለምንድን ነው? አንተና ልጆችህ ሕዝቤ እስራኤል ካቀረበው ቊርባን ሁሉ ምርጥ ምርጡን በልታችሁ ራሳችሁን በማወፈር ከእኔ ይልቅ ልጆችህን የምታከብራቸው ስለምንድን ነው?’

30 “ስለዚህ የእስራኤል አምላክእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘ቤትህና የአባትህ ቤት በፊቴ ለዘላለም ያገለግሉኝ ዘንድ ተስፋ ሰጥቼ ነበር፤’ አሁን ግንእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘ይህን ከእንግዲህ አላደርገውም፤ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ፤ የሚንቁኝም ፈጽሞ ይናቃሉ።

31 እነሆ፤ በዘርህ ሽማግሌ እንዳይገኝ ያንተን ኀይልና የአባትህን ቤተ ሰብ ኀይል የምሰብርበት ጊዜ ይመጣል፤

32 በማደሪያዬም መከራ ታያለህ፤ ምንም እንኳ ለእስራኤል በጐ ነገር ቢደረግም፣ በቤተ ሰብህ ውስጥ ሽማግሌ ፈጽሞ አይገኝም።

33 ከመሠዊያዬ የማላስወግዳቸው ዘሮችህ በሕይወት የሚተርፉትም ዐይኖችህን በእንባ ለማፍዘዝ፣ ልብህን በሐዘን ለማደንዘዝ ብቻ ነው፣ ሌሎቹ ዘሮችህ ግን በሙሉ በለጋነታቸው ባጭር ይቀጫሉ።

34 “ ‘በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚደርሰው ላንተ ምልክት ይሆንሃል፣ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።

35 እንደ ልቤና እንደ አሳቤ የሚያገለግል የታመነ ካህን ለራሴ አስነሣለሁ፤ ቤቱን አጽንቼ አቆማለሁ፣ እርሱም በቀባሁት ፊት ለዘላለም ያገለግላል።

36 ከዘሮችህም መካከል የተረፈው ማንኛውም ሰው፣ ለአንዲት ጥሬ ብርና ለቍራሽ እንጀራ ሲል በፊቱ ወድቆ ይሰግዳል፤ “የዕለት ጒርሴን እንዳገኝ እባክህ በማንኛውም የክህነት ሥራ ላይ መድበኝ” በማለት ይለምናል።’ ”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *