1 ሳሙኤል 7

1 የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተውየእግዚአብሔርንታቦት ይዘው ወጡ፤ ከዚያም በኰረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት ወሰዱት።የእግዚአብሔርንታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።

የፍልስጥኤማውያን መሸነፍ

2 ታቦቱ በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠ ረዥም ጊዜ ሆነው፤ በአጠቃላይ ሃያ ዓመት ቈየ። የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ አዘነ፤እግዚአብሔርንምፈለገ።

3 ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፣ “በፍጹም ልባችሁ ወደእግዚአብሔርየምትመለሱ ከሆነ፣ ሌሎችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ራሳችሁንምለእግዚአብሔርአሳልፋችሁ ስጡ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋችኋል።” አላቸው።

4 ስለዚህ እስራኤላውያን የበኣልንና የአስታሮትን አማልክት አስወግደው፣እግዚአብሔርንብቻ አመለኩ።

5 ከዚያ በኋላ ሳሙኤል፣ “እስራኤልን ሁሉ በምጽጳ ሰብስቡ፤ እኔም ስለ እናንተ ወደእግዚአብሔርእጸልያለሁ” አለ።

6 እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፣ ውሃ ቀድተውበእግዚአብሔርፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለት ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርንበድለናል” ብለው ተናዘዙ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር።

7 እስራኤል በምጽጳ መሰብሰባቸውን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ የፍልስጥኤማውያን ገዦች ሊወጓቸው ወጡ፤ እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ፣ ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ፤

8 ሳሙኤልንም፣ “አምላካችንእግዚአብሔርከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ስለ እኛ ወደ እርሱ መጸለይህን አታቋርጥ” አሉት።

9 ሳሙኤልም አንድ የሚጠባ የበግ ግልገል ወስዶ ሙሉ ለሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግለእግዚአብሔርአቀረበው፤ ስለ እስራኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤እግዚአብሔርምመለሰለት።

10 ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያሳርግበት ጊዜ፣ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት ቀረቡ። ይሁን እንጂ በዚያ ዕለትእግዚአብሔርበፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ የነጐድጓድ ድምፅ ስላንጐዳጐ ደባቸው እጅግ ተሸበሩ፤ ድልም ተመተው ከእስራኤላውያን ፊት ሸሹ።

11 እስራኤላውያንም ከምጽጳ ወጥተው ፍልስጥኤማውያንን በየመንገዱ እየገደሉ ከቤትካር በታች እስካለው ስፍራ ድረስ አሳደዷቸው።

12 ከዚህ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው፤ ስሙንም “እግዚአብሔርእስከ አሁን ድረስ ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዘር” ብሎ ጠራው።

13 በዚህ ሁኔታ ፍልስጥኤማውያን ድል ስለ ተመቱ፣ የእስራኤልን ምድር ዳግመኛ አልወረሩም።

ሳሙኤል በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ፣የእግዚአብሔርእጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከብዳ ነበር።

14 ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከአቃሮን እስከ ጌት የነበሩ ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱላት፤ ግዛታቸውም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ነፃ ወጣች፤ በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ሰላም ነበረ።

15 ሳሙኤል በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ እስራኤልን ይዳኝ ነበር።

16 በየዓመቱ በቤቴል፣ በጌልገላና በምጽጳ እየተዘዋወረ፣ በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።

17 ከዚያም በአርማቴም ወዳለው ቤቱ ይመለስ ነበር፤ በዚያም ደግሞ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር። በዚያምለእግዚአብሔርመሠዊያ ሠራ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *