1 ነገሥት 9

እግዚአብሔር ለሰሎሞን ዳግመኛ ተገለጠ

1 ሰሎሞንየእግዚአብሔርንቤተ መቅደስና የራሱን ቤተ መንግሥት ሠርቶ ከጨረሰና ለመሥራት የፈለገውንም ሁሉ ካከናወነ በኋላ፣

2 እግዚአብሔርለሰሎሞን በገባዖን ተገልጦለት እንደ ነበረ ሁሉ ዳግም ተገለጠለት።

3 እግዚአብሔርምእንዲህ አለው፤

“በፊቴ ያቀረብኸውን ጸሎትና ልመና ሰምቻለሁ፤ ይህን የሠራኸውንም ቤተ መቅደስ ስሜን በዚያ ለዘላለም እንዲኖር በማድረግ ቀድሼዋለሁ፤ ዐይኖቼና ልቤ ምንጊዜም በዚያ ይሆናሉ።

4 “አንተም አባትህ ዳዊት እንዳደረገው፣ በልበ ቅንነትና በትክክለኛነት ብትሄድ፣ የማዝህን ሁሉ ብትፈጽም፣ ሥርዐቴንና ሕጌን ብትጠብቅ፣

5 ለአባትህ ለዳዊት፣ ‘በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከዘርህ ሰው አታጣም’ በማለት በሰጠሁት ተስፋ መሠረት ዙፋንህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።

6 “ነገር ግን አንተምሆንህ ልጆችህ እኔን ከመከተል ወደ ኋላ ብትመለሱ፣ የሰጠኋችሁን ትእዛዞችና ሥርዐቶች ሳትጠብቁ ብትቀሩ፣ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩና ብትሰግዱላቸው፣

7 እኔም እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር እነቅላቸዋለሁ፤ ስለ ስሜ የቀደስሁትን ይህን ቤተ መቅደስም እተወዋለሁ፤ ከዚያም እስራኤል በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ መተረቻና መዘባበቻ ይሆናሉ፤

8 ይህ ቤተ መቅደስ አሁን የሚያስገርም ቢሆንም እንኳ፣ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ ዐላፊ አግዳሚውም ሁሉ ይገረማል፤ እያፌዘም፣ ‘እግዚአብሔርበዚህች ምድርና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያደረገው ስለ ምን ይሆን?’ ይላል፤

9 ራሱ መልሶም፣ ‘አዎንእግዚአብሔርይህን ሁሉ ጥፋት ያመጣባቸው አባቶቻቸውን ከግብፅ ምድር ያወጣውን አምላካቸውንእግዚአብሔርንትተው ሌሎች አማልክትን በመከተል ስለ ሰገዱላቸውና ስላመለኳቸው ነው’ ይላል።”

ሰሎሞን ያከናወናቸው ሌሎች ሥራዎች

10 ሰሎሞን ሁለቱን ሕንጻዎች፣ ማለትምየእግዚአብሔርንቤተ መቅደስና የንጉሡን ቤተ መንግሥት ሠርቶ በፈጸመ በሃያኛው ዓመት መጨረሻ፣

11 ንጉሥ ሰሎሞን በገሊላ የሚገኙትን ሃያ ከተሞች ለጢሮስ ንጉሥ ለኪራም ሰጠው፤ ንጉሡ ይህን ያደረገውም፣ የሚያስፈልገውን ሁሉ ዝግባ፣ ጥድና ወርቅ ኪራም ሰጥቶት ስለ ነበር ነው፤

12 ይሁን እንጂ ኪራም ከጢሮስ ተነሥቶ ሰሎሞን የሰጠውን ከተሞች ለማየት በሄደ ጊዜ አልተደሰተባቸውም፤

13 እርሱም፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ ከተሞች ምንድን ናቸው?” አለ፤ እነዚህንም ‘ከቡልምድር’ አላቸው፤ እስከ ዛሬም በዚሁ ስም ይጠራሉ።

14 በዚያን ጊዜ ኪራም ለንጉሡ መቶ ሃያ መክሊትወርቅ ልኮለት ነበር።

15 ንጉሥ ሰሎሞንየእግዚአብሔርንቤተ መቅደስ፣ የራሱን ቤተ መንግሥት፣ ሚሎን፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ ሐጾርን፣ መጊዶንና ጌዝርን ለመሥራት የጒልበት ሠራተኞች መልምሎ ነበር።

16 የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ወጥቶ በጌዝር ላይ አደጋ ጥሎ ያዛት፤ አቃጠላትም፤ ነዋሪዎቿን ከነዓናውያንን ገድሎ ለልጁ ለሰሎሞን ሚስት መዳሪያ አድርጎ ሰጥቶአት ነበር፤

17 ሰሎሞንም ጌዝርን መልሶ ሠራት፤ እንዲሁም የታችኛውን ቤትሖሮንን፣

18 ባዕላትን፣ በይሁዳ ምድር በምድረ በዳው የምትገኘውን ተድሞርንሠራ፤

19 ደግሞም ማናቸውንም በኢየሩሳሌም፣ በሊባኖስና በሌሎች ግዛቶቹ ሁሉ ለመሥራት የፈለገውን፣ ሥንቅ የሚከማችባቸውን፣ ሠረገሎችየሚጠበቁባቸውን እንዲሁም ፈረሰኞች የሚቀመጡባቸውን ከተሞችና መንደሮች ሁሉ ሠራ።

20 ከእስራኤል ሕዝብ ያልሆኑትን ከአሞራውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከፌርዛውያን፣ ከኤውያውንና ከኢያቡሳውያን ሕዝቦች ሁሉ የተረፉትን፣

21 እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ለማጥፋትያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን እነዚህን እስከ ዛሬ እንደሚደረገው ሁሉ፣ ሰሎሞን ለግዳጅ ሥራ መለመላቸው።

22 ይሁን እንጂ ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ማንንም ባሪያ አላደረገም፤ እነርሱ ወታደሮቹ፣ ሹማምቱ፣ የጦር አለቆቹ፣ ሻምበሎቹ፣ ባልደራሶቹ ነበሩ።

23 እነዚህም ሰሎሞን የሚያሠራውን የሕንጻ ሥራ የሚያከናውኑትን ሠራተኞች የሚቈጣጠሩ ናቸው፤ ቍጥራቸውም አምስት መቶ አምሳ ነበር።

24 የፈርዖን ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከመጣች በኋላ ሰሎሞን ሚሎንን ሠራ።

25 ሰሎሞንምለእግዚአብሔርባሠራው መሠዊያ ላይ በዓመት ሦስት ጊዜ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕትበማቅረብ፣ ከዚሁ ጋርበእግዚአብሔርፊት ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም የቤተ መቅደሱን ግዳጅ ተወጣ።

26 እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን በኤዶምያስ ምድር፣ በኤሎት አጠገብ፣ በቀይ ባሕርዳርቻ ላይ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ።

27 በመርከቦቹም ላይ ከሰሎሞን ሰዎች ጋር አብረው እንዲሠሩ፣ ኪራም ባሕሩን የሚያውቁ የራሱን መርከበኞች ላከ።

28 እነዚያም ወደ ኦፊር ሄደው አራት መቶ ሃያ መክሊትወርቅ ይዘው ተመለሱ፤ ይህንም ለንጉሥ ሰሎሞን ሰጡት።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *