1 ዜና መዋዕል 16

1 ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕትምበእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።

2 ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረቱን መሥዋዕት ከሠዋ በኋላ፣ ሕዝቡንበእግዚአብሔርስም ባረከ።

3 ከዚያም ለእስራኤል ሁሉ ለወንዱም ለሴቱም አንዳንድ ሙልሙል ዳቦ፣ አንዳንድ ጥፍጥፍ ተምር፣ ሙዳ ሙዳ ሥጋና አንዳንድ ጥፍጥፍ ዘቢብ ሰጠ።

4 በእግዚአብሔርታቦት ፊት እንዲያገለግሉና ለእስራኤል አምላክለእግዚአብሔርልመና፣ ምስጋናና ውዳሴ እንዲያቀርቡ ከሌዋውያን ሰዎች ሾመ፤

5 አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱ ቀጥሎ ዘካርያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ ከዚያም ይዒኤል፣ ሰሚራሞት፣ ይሒኤል፣ መቲትያ፣ ኤልያብ፣ በናያስ፣ ዖቤድኤዶም፣ ይዒኤል ተሾሙ፤ እነርሱም በመሰንቆና በበገና ይዘምሩ ነበር፤ አሳፍ ደግሞ ጸናጽል የሚጸነጽል ሆኖ ተመደበ።

6 እንዲሁም ካህናቱ በናያስና የሕዚኤል ዘወትር በእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ፊት መለከት እንዲነፉ ተመደቡ።

የዳዊት የምስጋና መዝሙር

7 በዚያም ቀን ዳዊት በመጀመሪያ ለአሳፍና ለሥራ ጓደኞቹ ይህንየእግዚአብሔርምስጋና መዝሙር ሰጠ፤

8 ለእግዚአብሔርምስጋና አቅርቡ፤ ስሙንም ጥሩ፤

ለአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ንገሩ፤

9 ዘምሩለት፤ ውዳሴም አቅርቡለት፤

ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤

10 በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤

እግዚአብሔርንየሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ።

11 ወደእግዚአብሔርናወደ ኀይሉ ተመልከቱ፤

ዘወትር ፊቱን ፈልጉ።

12 ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣

ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤

13 እናንተ የባሪያው የእስራኤል ዘሮች፣

እናንተ የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች።

14 እርሱእግዚአብሔርአምላካችን ነው፤

ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው፤

15 ኪዳኑን እስከ ዘላለም፣

ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺህ ትውልድ ያስባል።

16 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣

ለይስሐቅ የማለውን መሐላ።

17 ይህንንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ አጸና፤

ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አደረገ፤

18 እንዲህ ሲል፣ “የምትወርሰው ርስት እንዲሆን፣

የከነዓንን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ።”

19 ቍጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፣

በእርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፣

20 ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ፣

ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው መንግሥት ተንከራተቱ።

21 ማንም እንዲጨቍናቸው አልፈቀደም፤

ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤

22 እንዲህ ሲል፤ “የቀባኋቸውን አትንኩ፤

በነቢያቴ ላይ ክፉ አታድርጉ።

23 ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤

ማዳኑንም ዕለት ዕለት ዐውጁ።

24 ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፤

ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ።

25 እግዚአብሔርታላቅ ነው፤ ምስጋናውም ብዙ ነው፤

ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ የሚገባው ነው።

26 የአሕዛብ ሁሉ አማልክት ጣዖታት ናቸው፤

እግዚአብሔርግን ሰማያትን ሠራ።

27 በፊቱ ክብርና ሞገስ አለ፤

ብርታትና ደስታም በማደሪያው ስፍራ።

28 የአሕዛብ ወገኖችለእግዚአብሔርስጡ፤

ክብርና ኀይልንለእግዚአብሔርአምጡ።

29 ለስሙ የሚገባውን ክብርለእግዚአብሔርስጡ፤

መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤

በቅድስናውም ክብርለእግዚአብሔርስገዱ።

30 ምድር ሁሉ በፊቱ ትንቀጥቀጥ፤

ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥምም።

31 ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድር ሐሤት ታድርግ፤

በአሕዛብም መካከል፤ “እግዚአብሔርነገሠ!” ይበሉ።

32 ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ይናወጥ፤

ሜዳዎችና በእርሷ ላይ ያሉ ሁሉ ሐሤት ያድርጉ።

33 ያን ጊዜ የዱር ዛፎችበእግዚአብሔርፊት ደስ ይላቸዋል፤

በደስታ ይዘምራሉ፤

በምድረ በዳ ላይ ሊፈርድ ይመጣልና።

34 ቸር ነውናእግዚአብሔርንአመስግኑ፤

ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

35 “አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ ታደገን፤

ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣ በምስጋናህም እንድንከብር ሰብስበን፤

ከአሕዛብም መካከል ታደገን”

ብላችሁ ጩኹ።

36 ከዘላለም እስከ ዘላለም፣

ለእስራኤል አምላክለእግዚአብሔርምስጋና ይሁን።

ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣ “አሜን፤እግዚአብሔርይመስገን” አሉ።

37 ዳዊትም ለእያንዳንዱ ቀን በተመደበው መሠረት ዘወትር እንዲያገለግሉ አሳፍንና የሥራ ባልደረቦቹን በዚያውበእግዚአብሔርቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።

38 እንዲሁም ዖቤድኤዶምና ሥልሳ ስምንቱ የሥራ ባልደረቦቹ አብረዋቸው እንዲያገለግሉ በዚያው ተዋቸው። የኤዶታም ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖሳ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ሆኑ።

39 ዳዊት ካህኑን ሳዶቅንና የሥራ ባልደረቦቹን ካህናት በገባዖን ከፍተኛ ቦታ ላይ በሚገኘውበእግዚአብሔርድንኳን ተዋቸው፤

40 የተዋቸውም ለእስራኤል በተሰጠው ትእዛዝ መሠረትበእግዚእብሔርሕግ እንደ ተጻፈው ሁሉ በመሠዊያው ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ጧትና ማታ በየጊዜው እንዲያቀርቡ ነው።

41 እንዲሁም “ፍቅሩ ለዘላለም ነውና” እያሉ እንዲያቀርቡ ኤማንና ኤዶታም እንዲሁም ተመርጠውና ስማቸው ተመዝግቦ የተመደቡ ሌሎችም አብረዋቸው ነበሩ።

42 ድምፀ መለከቱንና ጸናጽሉን ለማሰማት፣ ደግሞም መንፈሳዊ መዝሙር ሲዘመር ለሚጠቀሙባቸው ሌሎች መሣሪያዎች ኀላፊዎቹ ኤማንና ኤዶታም ነበሩ፤ የኤዶታምም ልጆች በሩን እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር።

43 ከዚያም ሕዝቡ ተነሣ፤ እያንዳንዱም ወደየቤቱ ሄደ። ዳዊትም ቤተ ሰቡን ለመባረክ ወደ ቤቱ ተመለሰ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *