1 ዜና መዋዕል 29

ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የቀረቡ ስጦታዎች

1 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና ልምድም የሌለው ነው። ይህ ታላቅ ሕንጻ የሚሠራው ለሰው ሳይሆንለእግዚአብሔርአምላክ በመሆኑ፣ ሥራው ከባድ ነው።

2 እኔም ያለኝን ሀብት ለአምላኬ ቤተ መቅደስ ለወርቁ ሥራ ወርቁን፣ ለብሩ ሥራ ብሩን፣ ለናሱ ሥራ ናሱን፣ ለብረቱ ሥራ ብረቱን፣ ለዕንጨቱ ሥራ ዕንጨቱን እንዲሁም ለፈርጥ የሚሆነውን መረግድ፣ ኬልቄዶን፣ ልዩ ልዩ ኅብር ያላቸውን የከበሩ ድንጋዮች፣ ማናቸውንም ዐይነት የሚያምር ድንጋይና ዕብነበረድ፣ ይህን ሁሉ በብዛት አዘጋጅቻለሁ።

3 ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር የተነሣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤

4 ይህም ሦስት ሺህ መክሊትየኦፊር ወርቅና ሰባት ሺህ መክሊትንጹሕ ብር ለቤተ መቅደሱ የግድግዳ ግንብ ማስጌጫ

5 እንዲሁም ለወርቁ ሥራ፣ ለብሩ ሥራ፣ በባለ ሙያዎች ለሚሠራው ሥራ ሁሉ የሚሆን ነው። ታዲያ ዛሬ ራሱንለእግዚአብሔርለመቀደስ ፈቃደኛ የሚሆን ማን ነው?”

6 ከዚያም የቤተ ሰቡ መሪዎች፣ የነገዱ የእስራኤል ሹማምት፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም በንጉሡ ሥራ ላይ የተመደቡ ሹማምት በፈቃዳቸው ሰጡ፤

7 ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሰጡትም አምስት ሺህ መክሊትወርቅ፣ ዐሥር ሺህ ዳሪክወርቅ፣ ዐሥር ሺህ መክሊትብር፣ ዐሥራ ስምንት ሺህ መክሊትናስ አንድ መቶ ሺህ መክሊትብረት ነው።

8 የከበሩ ድንጋዮች ያለውም ሁሉ፣ በጌድሶናዊው በይሒኤል አማካይነት ወደእግዚአብሔርቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አስገባ።

9 ስጦታው በገዛ ፈቃድና በፍጹም ልብ የቀረበ በመሆኑ፣ አለቆቹ ስላደረጉት የበጎ ፈቃድ ስጦታ ሕዝቡ ደስ አለው፤ ንጉሥ ዳዊትም እንደዚሁ እጅግ ደስ አለው።

የዳዊት ጸሎት

10 ዳዊትም በመላው ጉባኤ ፊት እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል አመሰገነ፤

“የአባታችን የእስራኤል አምላክእግዚአብሔርሆይ፤

ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአንተ ምስጋና ይሁን።

11 እግዚአብሔርሆይ፤ በሰማይና

በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና፤

ታላቅነት፣ ኀይል፣ ክብርና ግርማ የአንተ ነው።

እግዚአብሔርሆይ፤ መንግሥትም የአንተ ነው፤

አንተም እንደ ራስ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልህ ነህ።

12 ባለጠግነትና ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤

አንተም የሁሉ ገዢ ነህ፤

ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም ብርታትን ለመስጠት፣

ብርታትና ኀይል በእጅህ ነው።

13 አምላካችን ሆይ፤ አሁንም እናመሰግንሃለን፤

ለከበረው ስምህም ውዳሴ እናቀርባለን።

14 “ሁሉ የተገኘው ከአንተ ነው፤ ለአንተም የሰጠንህ ከእጅህ የተቀበልነውን ብቻ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለ ቸርነት እናድርግ ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው?

15 እኛም እንደ ቀድሞ አባቶቻችን በፊትህ መጻተኞችና እንግዶች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፤ ተስፋ ቢስም ነው።

16 እግዚአብሔርአምላካችን ሆይ፤ ለተቀደሰው ስምህ ቤተ መቅደስ እንሠራልህ ዘንድ ይህ በብዛት ያዘጋጀነው ሁሉ፣ ከእጅህ የተገኘና ሁሉም የአንተ ነው።

17 አምላኬ ሆይ፤ ልብን እንደምትመረምርና ቅንነትን እንደምትወድ ዐውቃለሁ፤ እኔም ይህን ሁሉ የሰጠሁት በበጎ ፈቃድና በቀና መንፈስ ነው። አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በበጎ ፈቃዱ እንዴት እንደ ሰጠ አይቻለሁ።

18 የአባቶቻችን የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ዐሳብ ለዘላለም በሕዝብህ ልብ ጠብቀው፤ ልባቸውንም ለአንተ ታማኝ አድርገው።

19 ትእዛዞችህን፣ ደንብህንና ሥርዐትህን እንዲጠብቅ፣ እኔ ባዘጋጀሁለት ነገሮች ታላቅ ሕንጻ ለመሥራት እንዲችል፣ ለልጄ ለሰሎሞን ፍጹም ፈቃደኝነት ስጠው።

20 ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ፣ “አምላካችሁንእግዚአብሔርንወድሱት” አላቸው። ስለዚህ የአባቶቻቸውን አምላክእግዚአብሔርንወደሱ፤በእግዚአብሔርበንጉሡም ፊት ተደፍተው ሰገዱ።

ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑ በይፋ ታወቀ

21 በማግስቱምለእግዚአብሔርመሥዋዕት ሠዉ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም አቀረቡ፤ ይህም አንድ ሺህ ወይፈን፣ አንድ ሺህ አውራ በግ፣ አንድ ሺህ የበግ ጠቦት ሲሆን፣ ከመጠጥ ቊርባኖቻቸውና ከሌሎች መሥዋዕቶች ጋር ስለ እስራኤል ሁሉ በብዛት አቀረቡ።

22 በዚያችም ዕለትበእግዚአብሔርፊት በታላቅ ደስታ በሉ፤ ጠጡም።

ከዚያም የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን ለሁለተኛ ጊዜ በይፋ ዐወቁ፤ ገዥ እንዲሆንምበእግዚአብሔርፊት ቀቡት፤ ሳዶቅንም ካህናቸው እንዲሆን ቀቡት።

23 ሰሎሞንም ነግሦ በአባቱ በዳዊት ምትክበእግዚአብሔርዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ ተከናወነለት፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።

24 የጦር አለቆቹና ኀያላኑ ሁሉ እንዲሁም የንጉሡ የዳዊት ወንዶች ልጆች በሙሉ ታማኝነታቸውን ለንጉሥ ሰሎሞን አረጋገጡለት።

25 እግዚአብሔርምሰሎሞንን በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ ሁሉ እጅግ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከእርሱ በፊት ለነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ያላጐናጸፋቸውን ንጉሣዊ ክብር ሁሉ ሰጠው።

የዳዊት መሞት

26 የእሴይ ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር።

27 እርሱም በኬብሮን ሰባት ዓመት፣ በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት፣ በአጠቃላይ አርባ ዓመት ነገሠ።

28 ብዙ ዘመን ባለጠግነትና ክብር ሳይጐድልበት ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ልጁ ሰሎሞንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

29 በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተከናወነው ድርጊት በባለ ራእዩ በሳሙኤል የታሪክ መጽሐፍ፣ በነቢዩ በናታን የታሪክ መጽሐፍ፣ በባለ ራእዩ በጋድ የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።

30 የተጻፈውም በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ከፈጸማቸው ዝርዝር ጒዳዮችና በዙሪያው ከከበቡት፣ ከእስራኤልና ከሌሎች አገር መንግሥታት ታሪክ ጋር ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *