2 ሳሙኤል 23

የዳዊት የመጨረሻ ቃል

1 የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው፤

“በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣

ልዑል ከፍ ከፍ ያደረገው ሰው፣

የእስራኤል ተወዳጁ ዘማሪ፣

የእሴይ ልጅ የዳዊት የትንቢት ቃል ይህ ነው፤

2 “የእግዚአብሔርመንፈስ በእኔ ተናገረ፤

ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ።

3 የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤

የእስራኤልም ዐለት እንዲህ አለኝ፤

ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣

በፈሪሀእግዚአብሔርምየሚያስተዳድር፣

4 እርሱ፣ ደመና በሌለበት፣ በማለዳ ፀሓይ በምትወጣበት ጊዜ፣

እንዳለው ብርሃን ነው፤

በምድር ላይ ሣርን እንደሚያበቅለው፣

ከዝናብም በኋላ እንዳለው የብርሃን ጸዳል ነው።’

5 “የእኔስ ቤትበእግዚአብሔርዘንድ ትክክል አይደለምን?

ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፣

ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ አይደለምን?

ድነቴን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፣

መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን?

6 ነገር ግን ክፉ ሰዎች ሁሉ፣

በእጅ እንደማይሰበሰብ እንደ እሾኽ ይጣላሉ።

7 እሾኽ የሚነካ ሁሉ፣

የብረት መሣሪያ ወይም የጦር ዘንግ ይይዛል፤

ባሉበትም ቦታ ፈጽመው በእሳት ይቃጠላሉ።

የኀያላኑ የዳዊት ሰዎች ጀብዱ

8 የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፤ የታሕክሞንሰው ዮሴብ በሴትቤትየሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፣ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው የገደለ ነው።

9 ከእርሱ ቀጥሎ የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ ኤልዔዘር ነበረ፤ እርሱም ለጦርነት አንድ ላይ ተሰብስበውየነበሩትን ፍልስጥኤማውያንን በተገዳደሩ ጊዜ፣ ከዳዊት ጋር ከነበሩት ከሦስቱ ኀያላን ሰዎች አንዱ ነበር። ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ሸሹ።

10 እርሱ ግን የቆመበትን ስፍራ አለቀቀም፤ እጁ እስኪዝልና ከሰይፉ ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን ወጋ፤ በዚያችም ዕለትእግዚአብሔርታላቅ ድልን ሰጠ። የሸሸውም ሰራዊት ወደ ኤልዔዘር የተመለሰው የተገደሉትን ሰዎች ለመግፈፍ ብቻ ነበር።

11 ከእርሱም ቀጥሎ የአሮዳዊው የአጌ ልጅ ሣማ ነበር፤ ፍልስጥኤማውያንም ሌሒ በተባለ ስፍራ ምስር በሞላበት አንድ ዕርሻ ላይ፣ በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ፣ የእስራኤል ሰራዊት ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤

12 ሣማ ግን የቆመበትን ስፍራ አለቀቀም፤ ጦርነቱንም ተቋቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ገደለ፤ በዚያችም ዕለትእግዚአብሔርታላቅ ድል ሰጠ።

13 በመከር ወራት፣ የፍልስጥኤም ሰራዊት በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ ከሠላሳዎቹ አለቆች ሦስቱ ዳዊት ወዳለበት ወደ ዓዶላም ዋሻ መጡ።

14 በዚያም ጊዜ ዳዊት በምሽግ ውስጥ ነበረ፤ የፍልስጥኤማውያንም ሰራዊት በቤተልሔም ነበረ፤

15 ዳዊትም በናፍቆት፣ “በቤተልሔም በር አጠገብ ካለችው ጒድጓድ ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ።

16 ስለዚህ ሦስቱ ኀያላን በፍልስጥኤማውያን ሰራዊት መካከል ሰንጥቀው በማለፍ፣ በቤተልሔም በር አጠገብ ካለችው ጒድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት። እርሱ ግን አልጠጣውም፤ ይልቁንበእግዚአብሔርፊት መሥዋዕት አድርጎ አፈሰሰው፤

17 “እርሱም፣እግዚአብሔርሆይ፤ እንዲህ ያለውን ነገር ላርግ? ይህስ ከእኔ ይራቅ! ይህ በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?” አለ፤ ዳዊትም ሊጠጣው አልፈለገም። እንግዲህ ሦስቱ ኀያላን ሰዎች ያደረጉት ጀብዱ እንዲህ ነበር።

18 የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱኀያላን አለቃ ነበረ። በሦስት መቶ ሰዎች ላይ ጦሩን ሰብቆ የገደላቸውና እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ እርሱም ዝናን ያተረፈ ሰው ነበረ።

19 አቢሳ ከሦስቱ ይልቅ እጅግ የከበረ አልነበረምን? ከእነርሱ እንደ አንዱ ባይሆንም አለቃቸው ነበረ።

20 የቀብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ታላቅ ጀብዱ የሠራ ሌላው ጐበዝ ተዋጊ ነበረ፤ እርሱም ሁለት በጣም የታወቁ የሞዓብን ሰዎች ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በጣለበት ዕለት በጒድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሎአል፤

21 ደግሞም አንድ ግዙፍ ግብፃዊ ገድሎአል፤ ግብፃዊው በእጁ ጦር የያዘ ቢሆንም፣ በናያስ ግን ሊገጥመው በትር ይዞ ወደ እርሱ ሄደ፤ ከግብፃዊውም እጅ ጦሩን በመንጠቅ በገዛ ጦሩ ገደለው።

22 የዮዳሄ ልጅ የበናያስ ጀግንነት እንደዚህ ያለ ነበረ፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ ዝናን ያተረፈ ሲሆን፣

23 ከሠላሳዎቹ ሁሉ በላይ የከበረ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ከሦስቱ እንደ አንዱ አልነበረም። ዳዊትም የክብር ዘበኞቹ አለቃ አድርጎ ሾመው።

24 ከሠላሳዎቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙ ባቸዋል፤

የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣

የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣

25 አሮዳዊው ሣማ፣

አሮዳዊው ኤሊቃ፣

26 ፈሊጣዊው ሴሌስ፣

የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ፣

27 ዓናቶታዊው አቢዔዜር፤

ኩሳታዊው ምቡናይ፣

28 አሆሃዊው ጸልሞን፣

ነጦፋዊው ማህራይ፣

29 የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ፣

ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣

30 ጲርዓቶናዊው በናያስ፣

የገዓስ ሸለቆ ሰው ሂዳይ፣

31 ዓረባዊው አቢዓልቦን፣

በርሑማዊው ዓዝሞት፣

32 ሸዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፣

የአሳን ልጆች፤ ዮናታን የተባለው፣

33 የአሮዳዊው የሣማ ልጅ፣

የአሮዳዊው የሻራርልጅ አሒአም፤

34 የማዕካታዊው የአሐሰባይ ልጅ ኤሌፋላት፣

የጊሎናዊው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊአም፣

35 ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፤

አርባዊው ፈዓራይ፣

36 የሱባ ሰው የሆነው የናታን ልጅ ይግዓል፣

37 አሞናዊው ጻሌቅ፣

የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጦር መሣሪያ ያዥ የነበረው ብኤሮታዊው ነሃራይ፣

38 ይትራዊው ዒራስ፣

ይትራዊው ጋሬብ፣

39 እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮ፤

በጠቅላላው ሠላሳ ሰባት ነበሩ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *