ዳዊት ተዋጊዎቹን ቈጠረ
1 እንደ ገናምእግዚአብሔርበእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ዳዊትንም በእነርሱ ላይ በማስነሣት፣ “ሂድ እስራኤልንና ይሁዳን ቊጠር” አለው።
2 ስለዚህም ንጉሡ ኢዮአብንና አብረውት ያሉትን የጦር አዛዦች፣ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወዳሉት የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፤ ብዛታቸው ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ እንድችልም ተዋጊዎቹን መዝግቡ” አላቸው።
3 ኢዮአብ ግን ንጉሡን፣ “አምላክህእግዚአብሔርሰራዊቱን መቶ ዕጥፍ ያድርገው፤ የጌታዬ የንጉሡ ዐይን ይህን ለማየት ይብቃ፤ ንጉሡ ጌታዬ ግን ይህን ለማድረግ የፈለገው ለምንድን ነው?” ሲል መለሰለት።
4 ሆኖም የንጉሡ ቃል ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች ስላሸነፋቸው፣ የእስራኤልን ሰራዊት ለመመዝገብ ከፊቱ ወጥተው ሄዱ።
5 ዮርዳኖስን ከተሻገሩ በኋላ፣ በሸለቆው ውስጥ ካለችው ከተማ በስተ ደቡብ በምትገኘው በአሮዔር አጠገብ ሰፈሩ፤ ከዚያም በጋድ በኩል አድርገው ወደ ኢያዜር ሄዱ፤
6 እንዲሁም ወደ ገለዓድና ወደተባሶን አዳሰይ፣ ቀጥሎም ወደ ዳንየዓን ከዚያም ዞረው ወደ ሲዶና ሄዱ።
7 ደግሞም ወደ ጢሮስ ምሽግ፣ ወደ ኤዊያውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች፣ በመጨረሻም በይሁዳ ደቡብ ወዳለችው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ።
8 ምድሪቱን ሁሉ ዞረው ከዘጠኝ ወር ከሃያ ቀን በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
9 ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺህ፣ በይሁዳ አምስት መቶ ሺህ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ።
10 ዳዊት ተዋጊዎቹን ከቈጠረ በኋላ ኅሊናው ስለ ወቀሰው፣ “ባደረግሁት ነገር ታላቅ ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ አሁንምእግዚአብሔርሆይ፤ የአገልጋይህን በደል እንድታርቅ እለምንሃለሁ፤ የፈጸምሁት ታላቅ የስንፍና ሥራ ነውና” አለ።
11 በማግስቱ ጠዋት ዳዊት ከመነሣቱ በፊትየእግዚአብሔርቃል የዳዊት ባለ ራእይ ወደ ሆነው ወደ ነቢዩ ወደ ጋድ መጣ፤
12 እንዲህም አለው፤ “ሂድና ዳዊትን፣ ‘እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ሦስት ነገሮችን ለምርጫ አቅርቤልሃለሁ፤ በአንተ ላይ አደርግብህ ዘንድ አንዱን ምረጥ’ በለው።”
13 ስለዚህም ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ፣ “በምድርህ የሦስትዓመት ራብ ይምጣብህ? ወይስ ጠላቶችህ እያሳደዱህ ሦስት ወር ትሸሽ? ወይስ ደግሞ በምድርህ ላይ የሦስት ቀን ቸነፈር ይምጣ? እንግዲህ አሁን ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስበህበት ወስን” አለው።
14 ዳዊትም ጋድን፣ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ታላቅ ስለ ሆነበእግዚአብሔርእጅ እንውደቅ፤ በሰው እጅ ግን አልውደቅ” አለው።
15 ስለዚህምእግዚአብሔርከዚያች ዕለት ጥዋት አንሥቶ እስከ ተወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ ቸነፈር ላከ፤ በዚህም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺህ ሰው አለቀ።
16 የእግዚአብሔርመልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ የደረሰው ጒዳትእግዚአብሔርንስላሳዘነው፣ ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ “በቃ! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
17 ዳዊት ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ ባየ ጊዜእግዚአብሔርን፣“እነሆ ኀጢአት የሠራሁም የተሳሳትሁም እኔ ነኝ፤ እነዚህ ግን በጎች ናቸው፤ ምን አጠፉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን” አለ።
ዳዊት መሠዊያ ሠራ
18 በዚያን ቀን ጋድ ወደ ዳዊት ዘንድ ሄዶ፣ “ውጣና በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይለእግዚአብሔርመሠዊያ ሥራ” አለው።
19 ስለዚህ ዳዊት፣እግዚአብሔርበጋድ በኩል ባዘዘው መሠረት ወጣ።
20 ኦርናም ቍልቍል ሲመለከት፣ ንጉሡና ሰዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ከዚያም ወጥቶ ወደ መሬት ለጥ ብሎ ለንጉሡ እጅ ነሣ።
21 ኦርናም፣ “ንጉሥ ጌታዬ ወደ አገልጋዩ የመጣው ለምንድን ነው?” አለ።
ዳዊትም መልሶ፣ “መቅሠፍቱ ከሕዝቡ እንዲከለከልለእግዚአብሔርመሠዊያ እንድሠራ ዐውድማህን ልገዛ ነው” አለው።
22 ኦርናም ዳዊትን እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ጌታዬ ደስ ያለውን ወስዶ መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች አሉ፤ ለሚነደውም ዕንጨት፣ የመውቂያው ዕቃና የበሬ ቀንበር አለ።
23 ንጉሥ ሆይ፣ ይህን ሁሉ ኦርና ለንጉሡ ይሰጣል።” እንዲሁም ኦርና፣ “እግዚአብሔርአምላክህ ይቀበልህ” አለው።
24 ንጉሡ ግን ኦርናን፣ “እንዲህማ አይሆንም፤ ዋጋውን ላንተ መክፈል አለብኝ፤ ለአምላኬምለእግዚአብሔርየሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው።
ስለዚህም ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅልብር ገዛ፤
25 በዚያም ዳዊትለእግዚአብሔርመሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕትአቀረበ። ከዚያምእግዚአብሔርስለ ምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የመጣውም ቸነፈር ቆመ።