2 ነገሥት 22

የሕጉ መጽሐፍ ተገኘ

1 ኢዮስያስ ሲነግሥ ዕድሜው ገና ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም የባሱሮት አገር ሰው የአዳያ ልጅ ይዲዳ ነበረች።

2 ኢዮስያስምበእግዚአብሔርፊት መልካም ነገር አደረገ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም፤ አባቱ ዳዊት በሄደበት መንገድ ሁሉ ሄደ።

3 በዘመነ መንግሥቱ በዐሥራ ስምንተኛውም ዓመት ኢዮስያስ የሜሶላምን የልጅ ልጅ የኤዜልያስን ልጅ ጸሓፊውን ሳፋንን ወደእግዚአብሔርቤተ መቅደስ ላከው፤ እንዲህም አለው፤

4 “ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኬልቅያስ ውጣ፤ የበር ጠባቂዎች ከሕዝቡ ሰብስበው ወደእግዚአብሔርቤተ መቅደስ የገባው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ ራሱ እንዲቈጥረው አድርግ፤

5 ይህም የቤተ መቅደሱን ሥራ እንዲቈጣጠሩ ለተሾሙት ሰዎች ይሰጥ፤ እነርሱምየእግዚአብሔርንቤተ መቅደስ ለሚያድሱት ይክፈሏቸው፤

6 የሚከፍሉትም ለአናጺዎች፣ ለግንበኞችና ለድንጋይ ጠራቢዎች ነው። እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ እድሳት ሥራ የሚሆኑ ሳንቃዎችና የተጠረቡ ድንጋዮች ይግዙበት።

7 ሰዎቹ ታማኞች ስለ ሆኑም የተሰጣቸውን ገንዘብ መቈጣጠር አያስፈልግም።”

8 ሊቀ ካህናቱ ኬልቅያስ ጸሓፊውን ሳፋንን፣ “የሕጉን መጽሐፍ እኮበእግዚአብሔርቤተ መቅደስ ውስጥ አገኘሁት” ብሎ ሰጠው፤ እርሱም ተቀብሎ አነበበው።

9 ከዚያም ጸሓፊው ሳፋን ሄዶ ለንጉሡ፣ “ሹማምትህበእግዚአብሔርቤተ መቅደስ ውስጥ የነበረውን ገንዘብ አውጥተዋል፤ ቤተ መቅደሱን እየተቈጣጠሩ ለሚያሠሩትም አስረክበዋል” አለው።

10 ከዚያም ጸሓፊው ሳፋን ለንጉሡ፣ “ሊቀ ካህናቱ ኬልቅያስ መጽሐፍ ሰጥቶኛል” ብሎ ነገረው። ሳፋንም ለንጉሡ ከመጽሐፉ አነበበለት።

11 ንጉሡም የሕጉን መጽሐፍ ቃል ሲሰማ ልብሱን ቀደደ።

12 ከዚያም ካህኑን ኬልቅያስን፣ የሳፋን ልጅ አኪቃምን፣ የሚክያስን ልጅ ዓክቦርን፣ ጸሓፊውን ሳፋንንና የንጉሡን የቅርብ አገልጋይ ዓሳያን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤

13 “ሂዱና ስለ እኔ፣ ስለ ሕዝቡና ስለ ይሁዳም ሁሉ በተገኘው በዚህ መጽሐፍ የተጻፈው ምን እንደሆነእግዚአብሔርንጠይቁ፤ ምክንያቱም አባቶቻችን ለዚህ መጽሐፍ ቃል ባለመታዘዛቸው፣ እኛን በተመለከተም በዚሁ ላይ የተጻፈውን ሁሉ ባለመፈጸማቸው፣ በእኛ ላይ የሚነደውየእግዚአብሔርቊጣ ታላቅ ነውና።”

14 ካህኑ ኬልቅያስ፣ አኪቃም፣ ዓክቦርና፣ ሳፋን፣ ዓሳያም የሐርሐስ የልጅ ልጅ፣ የቲቁዋ ልጅ የአልባሳት ጠባቂውን የሴሌምን ሚስት ነቢዪቱን ሕልዳናን ለመጠየቅ ሄዱ። እርሷም የምትኖረው ኢየሩሳሌም ውስጥ በሁለተኛው ሰፈር ነበር።

15 ነቢዪቱም፣ “የእስራኤል አምላክእግዚአብሔርየሚለው ይህ ነው፤ ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤

16 “እግዚአብሔርየሚለው ይህ ነው፤ የይሁዳ ንጉሥ ባነበበው መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ በዚህ ቦታና በሕዝቡ ላይ አመጣለሁ።

17 እኔን ስለተውኝና ለሌሎች አማልክት ዕጣን ስላጠኑ፣ እጆቻቸው በሠሯቸውም አማልክት ሁሉስላስቈጡኝ፣ ቊጣዬ በዚህ ቦታ ላይ ይነዳል፣ አይጠፋምም።’ ”

18 እግዚአብሔርንእንድትጠይቁ ወደዚህ ቦታ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ ይህን ንገሩት፣ ‘ስለ ሰማኸው ነገር የእስራኤል አምላክእግዚአብሔርየሚለው ይህ ነው፤

19 “ለርግማንና ለጥፋት የተዳረጉ ስለ መሆናቸው በዚህ ቦታና በሕዝቡ ላይ የተናገርኩትን ስትሰማ ልብህ ስለ ተነካና ራስህንበእግዚአብሔርፊት ስላዋረድህ፣ ልብስህንም ቀደህ በፊቴ ስላለቀስህእግዚአብሔርሰምቼሃለሁ ብሏል።

20 ስለዚህ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፤ ወደ መቃብር በሰላም ትወርዳለህ፤ በዚህ ቦታም የማመጣውን መከራ ሁሉ ዐይኖችህ አያዩም።’ ” ሰዎቹም መልሱን ለንጉሡ ይዘውለት ሄዱ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *