የይሁዳ ንጉሥ አብያ
1 ኢዮርብዓም በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት አብያ በይሁዳ ነገሠ።
2 በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ዓመት ገዛ። እናቱ ሚካያትባላለች፤ እርሷም የገብዓ ተወላጅ የኡርኤል ልጅ ነበረች።
በአብያና በኢዮርብዓምም መካከል ጦርነት ነበር።
3 አብያ አራት መቶ ሺህ ብርቱ ተዋጊዎች ይዞ ዘመተ፤ ኢዮርብዓምም ስምንት መቶ ሺህ ብርቱ ተዋጊዎች ይዞ በመውጣት ጠበቀው።
4 አብያ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ፣ እንዲህ አለ፤ “ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ አድምጡኝ!
5 የእስራኤልአምላክእግዚአብሔር ዳዊትና ዘሮቹ በእስራኤል ላይ ለዘላለም እንዲነግሡ በጨው ኪዳን የሰጣቸው መሆኑን አታውቁምን?
6 የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ባሪያ የነበረው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ግን በጌታው ላይ ዐመፀ።
7 የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ገና ሕፃን ሳለ፣ ምንም ማድረግ በማይችልበትና እነርሱንም ለመቋቋም አቅሙ በማይፈቅድለት ጊዜ የማይረቡ ጥቂት ወሮበሎች በዙሪያው ተሰበሰቡበት፣ በረቱበትም።
8 “አሁንም እናንተ በዳዊት ዘርዐ-ትውልድ እጅ ያለውንየእግዚአብሔርንመንግሥት ልትቋቋሙ አስባችኋል። በእርግጥም በሰራዊት ረገድ እጅግ ብዙ ናችሁ፤ አማልክቶቻችሁ ይሆኑ ዘንድ ኢዮርብዓም የሠራቸውንም የወርቅ ጥጆች ይዛችኋል።
9 ደግሞስ የአሮን ልጆች የሆኑትን ካህናትና ሌዋውያን አባርራችሁ፣ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ፣ እናንተም የራሳችሁን ካህናት አልሾ ማችሁምን? አንድ ኮርማና ሰባት አውራ በግ ይዞ ራሱን ለመቀደስ የሚመጣ ማናቸውም ሰው አማልክት ላልሆኑ ለእነዚያ ጣዖታት ካህን ይሆናል።
10 “ለእኛ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱንም አልተውንም፤እግዚአብሔርንበማገልገል ላይ ያሉት ካህናት የአሮን ልጆች ሲሆኑ፣ ረዳቶቻቸውም ሌዋውያኑ ናቸው።
11 እነርሱም በየጧቱና በየማታው የሚቃጠል መሥዋዕትና ሽታው ደስ የሚያሰኝ ዕጣንለእግዚአብሔርያቀርባሉ፤ የገጹን ኅብስት በሥርዐቱ መሠረት በነጻው ጠረጴዛ ላይ ያኖራሉ፤ በየማታውም በወርቁ መቅረዝ ላይ ያሉትን ቀንዲሎች ያበራሉ፤ እኛምየአምላካችንንየእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንፈጽማለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል።
12 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤ መሪአችንም እርሱ ነው። መለከት የያዙ ካህናቱም የጦርነቱን ድምፅ በእናንተ ላይ ያሰማሉ። እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ አይቀናችሁምና፣ ከአባቶቻችሁአምላክከእግዚአብሔር ጋር አትዋጉ።”
13 በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከሰራዊቱ ከፊሉን ከይሁዳ ሰራዊት በስተ ጀርባ እንዲያደፍጡ ላከ፤ የቀረውም ሰራዊት ከእርሱ ጋር የይሁዳን ሰራዊት ፊት ለፊት እንዲገጥሙ አደረገ።
14 የይሁዳም ሰዎች ዙሪያቸውን ሲመለከቱ ከፊትና ከኋላ መከበባቸውን አዩ፤ ወደእግዚአብሔርምጮኹ፤ ካህናቱም መለከታቸውን ነፉ።
15 የይሁዳም ሰዎች በፉከራ የጦርነት ድምፅ አሰሙ፤ እግዚአብሔር ኢዮርብዓምንና እስራኤልን ሁሉ በአብያና በይሁዳ ፊት ፊጽሞ መታቸው።
16 እስራኤላውያን ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።
17 አብያና ሰዎቹም ከባድ ጒዳት አደረሱባቸው፤ ከዚህ የተነሣም ከእስራኤል ብርቱ ተዋጊዎች መካከል አምስት መቶ ሺህ ሰዎች ተገደሉ።
18 በጦርነቱም የእስራኤል ሰዎች ተዋረዱ፣ የይሁዳ ሰዎች ግን በአባቶቻቸውአምላክበእግዚአብሔር ታምነዋልና ድል ነሡ።
19 አብያም ኢዮርብዓምን አሳድዶ የቤቴልን፣ የይሻናንና የዔፍሮንን ከተሞች ከነ መንደሮቻቸው ወሰደበት።
20 ኢዮርብዓም በአብያ ዘመን እንደ ገና ሊያንሠራራ አልቻለም፤ ከዚያምእግዚአብሔርስለ ቀሠፈው ሞተ።
21 አብያ ግን ይበልጥ እየበረታ ሄደ፤ ዐሥራ አራት ሚስቶች አግብቶም ሃያ ሁለት ወንዶችና ዐሥራ ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት።
22 በአብያ ዘመን የተከናወነው ተግባር፣ እርሱ የፈጸመውና የተናገረው ሁሉ በነቢዩ በአዶ የታሪክ መዛግብት ተጽፎአል።