2 ዜና መዋዕል 27

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአታም

1 ኢዮአታም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ሲሆን፣ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። እናቱም ኢየሩሳ የተባለች የሳዶቅ ልጅ ነበረች።

2 አባቱ ዖዝያን እንዳደረገው ሁሉበእግዚአብሔርፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ይሁን እንጂ እንደ አባቱ ወደእግዚአብሔርቤተ መቅደስ አልገባም። ሕዝቡም በበደሉ እንደ ገፋበት ነበር።

3 ኢዮአታምየእግዚአብሔርንቤተ መቅደስ የላይኛውን በር እንደ ገና ሠራው፤ በዖፌልም በኩል ባለው ቅጥር ላይ፣ አያሌ የማሻሻል ተግባር አከናወነ።

4 በይሁዳ ኰረብታዎች ላይ ከተሞችን፣ ደን በለበሱ ስፍራዎችም ምሽጎችንና ማማዎችን ሠራ።

5 ኢዮአታም የአሞናውያንን ንጉሥ ወግቶ ድል አደረጋቸው። በዚያ ዓመትም አሞናውያን አንድ መቶ መክሊትጥሬ ብር፣ ዐሥር ሺህ ቆሮስስንዴና ዐሥር ሺህ ቆሮስ ገብስ ገበሩለት። አሞናውያን በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ይህንኑ ግብር አመጡለት።

6 ኢዮአታምበአምላኩበእግዚአብሔር ፊት በታማኝነት ስለተመላለሰ፣ እየበረታ ሄደ።

7 በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባር፣ ያደረጋቸው ጦርነቶችና የሠራቸው ነገሮች በሙሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።

8 እርሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ።

9 ኢዮአታም እንደ አባቶቹ ሁሉ አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁ አካዝም በእርሱ ፈንታ ነገሠ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *