1 የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአሐዝን ወስደው በአባቱ ፈንታ በኢየሩሳሌም አነገሡት።
የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአሐዝ
2 ኢዮአሐዝ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ሦስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ወር ገዛ።
3 ከዚያም የግብፅ ንጉሥ በኢየሩሳሌም ካለው ዙፋኑ አወረደው፣ በአገሩም ላይ አንድ መቶ መክሊትብርና አንድ መክሊትወርቅ ግብር ጣለበት።
4 የግብፅም ንጉሥ የኢዮአሐዝን ወንድም ኤልያቄምን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው፤ ስሙንም ለውጦ ኢዮአቄም አለው። ኒካዑም የኤልያቄምን ወንድም ኢዮአሐዝን ይዞ ወደ ግብፅ ወሰደው።
የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም
5 ኢዮአቄም በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ።በአምላኩምበእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ።
6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በእርሱ ላይ ዘመተ፤ ወደ ባቢሎንም ይወስደው ዘንድ በናስ ሰንሰለት አሰረው።
7 እንደዚሁም ናቡከደነፆርየእግዚአብሔርንቤተ መቅደስ ዕቃ ወስዶ፣ ባቢሎን ባለው በራሱ ቤተ ጣዖትአኖረው።
8 በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባሩ የፈጸመው አስጸያፊ ድርጊትና በእርሱ ላይ የተገኘበት ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል። ልጁ ዮአኪንም በእርሱ ፈንታ ነገሠ።
የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን
9 ዮአኪን በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ዐሥራ ስምንትዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ወር ከዐሥር ቀን ገዛ፤ እርሱምበእግዚአብሔርፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ።
10 በጸደይም ወራት ንጉሡ ናቡከደነፆር ልኮበእግዚአብሔቤተ መቅደስ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ካላቸው ዕቃዎች ጋር ወደ ባቢሎን ወሰደው። የዮአኪንንም አጎትሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ
11 ሴዴቅያስ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ።
12 እርሱም በአምላኩበእግዚአብሔርፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ፤ የእግዚአብሔርን ቃል በተናገረው በነቢዩ በኤርምያስ ፊትም ራሱን ዝቅ አላደረገም።
13 እንደዚሁም በእግዚአብሔር ስም አምሎት በነበረው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ አንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ እንጂ ወደ እስራኤል አምላክ ወደእግዚአብሔርአልተመለሰም።
14 ከዚህም ላይ የካህናቱና የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ፣ አስጸያፊ የሆኑትን የአሕዛብን ልማዶች በመከተልና በኢየሩሳሌም የተቀደሰውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በማርከስ፣ ባለ መታመናቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሱ ሄዱ።
የኢየሩሳሌም መውደቅ
15 የአባቶቻቸውአምላክእግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ስላዘነ፣ መልእክተኞቹን ይልክ ነበር፤
16 እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቊጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነሣሣና ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሳለቁ፤ ቃሉን ናቁ፤ ነቢያቱንም አቃለሉ።
17 ስለዚህ የባቢሎናውያንንንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ፈጀ፤ ወጣቱንም ሆነ ወጣቲቱን፣ ሽማግሌውንም ሆነ በዕድሜ የገፋውን አላስቀረም፤ እግዚአብሔር ሁሉንም ለናቡከደናፆር አሳልፎ ሰጠው።
18 እርሱም ትልልቁንም ሆነ ትንንሹን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዕቃ በሙሉ፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሀብት፣ የንጉሡንና የሹማምቱን ሀብት ሁሉ ወደ ባቢሎን አጋዘ።
19 የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በእሳት አቃጠሉ፤ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች አፈረሱ፤ ቤተ መንግሥቶቹን በሙሉ አቃጠሉ፤ በዚያ የነበረውንም የከበረ ዕቃ በሙሉ አጠፉ።
20 ከሰይፍ የተረፉትን ቅሬታዎች በምርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ እስከ ፋርስ መንግሥት መነሣትም ድረስ የእርሱና የልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ።
21 ምድሪቱም የሰንበት ዕረፍት አገኘች፤ በኤርምያስ የተነገረውየእግዚአብሔርቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ሰባው ዓመት እስኪያበቃ ድረስ፣ ባድማ በነበረችበት ዘመን ሁሉ ዐረፈች።
22 በኤርምያስ የተነገረውየእግዚአብሔርቃል ይፈጸም ዘንድ፣ በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ዓመት፣ በግዛቱ ሁሉ ዐዋጅ እንዲያስነግርና ይህም እንዲጻፍእግዚአብሔርየፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሣሣ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤
23 “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፤
“ ‘የሰማይአምላክእግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳ በምትገኘው በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እሠራለት ዘንድ አዝዞኛል፤ ከሕዝቡ በመካከላችሁ የሚገኝ ማናቸውም ሰው፣እግዚአብሔርአምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም ወደዚያው ይውጣ።’ ”