1 መልካም ስም ከብዙ ብልጽግና ይመረጣል፤
መከበርም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል።
2 ባለጠጋና ድኻ የሚጋሩት ነገር፣
እግዚአብሔርየሁላቸውም ፈጣሪ መሆኑ ነው።
3 አስተዋይ ሰው አደጋ ሲያይ መጠጊያ ይሻል፤
ብስለት የጐደለው ግን በዚያው ይቀጥላል፤ መከራም ያገኘዋል።
4 ትሕትናናእግዚአብሔርንመፍራት፣
ሀብትን፣ ክብርንና ሕይወትን ያስገኛል።
5 በክፉዎች መንገድ ላይ እሾህና ወጥመድ አለ፤
ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነዚህ ይርቃል።
6 ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፤
በሚሸመግልበት ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።
7 ባለጠጋ ድኻን ይገዛል፤
ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው።
8 ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፤
የቊጣውም በትር ይጠፋል።
9 ቸር ሰው ራሱ ይባረካል፤
ምግቡን ከድኾች ጋር ይካፈላልና።
10 ፌዘኛን አስወጣው፤ ጠብ ይወገዳል፤
ጥልና ስድብም ያከትማል።
11 የልብ ንጽሕናን ለሚወድና ንግግሩም ሞገስ ላለው ሰው፣
ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።
12 የእግዚአብሔርዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤
የማይታመኑትን ሰዎች ቃል ግን እርሱ ከንቱ ያደርጋል።
13 ሰነፍ፣ “አንበሳ ውጪ አለ፤
መንገድ ላይ እገደላለሁ” ይላል።
14 የአመንዝራ ሴት አፍ ጥልቅ ጒድጓድ ነው፤
እግዚአብሔርየተቈጣውም ይገባበታል።
15 ሞኝነት በሕፃን ልብ ታስሮአል፤
የተግሣጽ በትር ግን ከእርሱ ያርቅለታል።
16 ሀብቱን ለማካበት ድኻን የሚበድል፣
ለባለጠጋም ስጦታ የሚያቀርብ፣ ሁለቱም ይደኸያሉ።
የጠቢባን ምክር
17 የጠቢባንን ቃል ልብ ብለህ ስማ፤
ልብህም ወደ ትምህርቴ ያዘንብል፤
18 በልብህ ስትጠብቃቸው፣
ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ ደስ ይላልና።
19 ስለዚህ እምነትህበእግዚአብሔርላይ እንዲሆን፣
ዛሬ አንተን ራስህን አስተምርሃለሁ።
20 የምክርና የዕውቀት ቃል የሆኑ፣
መልካም ትምህርቶችንአልጻፍሁልህምን?
21 ለላከህ ተገቢውን መልስ ትሰጥ ዘንድ፣
እውነተኛውና የታመኑ ቃሎችን እንዳስተምርህ አይደለምን?
22 ድኾች በመሆናቸው ብቻ ድኾችን አትበዝብዛቸው፤
ችግረኛውንም በአደባባይ አታንገላታው፤
23 እግዚአብሔርይፋረድላቸዋልና፤
የሚቀሟቸውንም ይቀማቸዋል።
24 ከግልፍተኛ ጋር ወዳጅ አትሁን፤
በቀላሉ ቱግ ከሚልም ሰው ጋር አትወዳጅ፤
25 አለበለዚያ መንገዱን ትማራለህ፤
ራስህም ትጠመድበታለህ።
26 በዋስትና ቃል እጅ አትምታ፤
ለብድር ተያዥ አትሁን፤
27 የምትከፍለው ካጣህ፣
የምትተኛበት ዐልጋ ከሥርህ ይወሰድብሃል።
28 የቀድሞ አባቶችህ ያስቀመጡትን፣
የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ።
29 በሙያው ሥልጡን የሆነውን ሰው አይተሃልን?
በነገሥታት ዘንድ ባለሟል ይሆናል፤
አልባሌ ሰዎችን አያገለግልም።