መዝሙር 148

ፍጥረተ ዓለም ሁሉ ያመስግን

1 ሃሌ ሉያ።

እግዚአብሔርንከሰማያት አመስግኑት፤

በላይ በአርያም አመስግኑት።

2 መላእክቱ ሁሉ አመስግኑት፤

ሰራዊቱ ሁሉ አመስግኑት፤

3 ፀሓይና ጨረቃ አመስግኑት፤

የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት።

4 ሰማየ ሰማያት አመስግኑት፤

ከሰማያትም በላይ ያላችሁ ውሆች አወድሱት።

5 እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና፣

የእግዚአብሔርንስም ያመስግኑት።

6 ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው፤

የማይሻርም ሕግ ደነገገላቸው።

7 የባሕር ውስጥ ግዙፍ ፍጥረትና ጥልቅ ውሆች ሁሉ፣

እግዚአብሔርንከምድር አመስግኑት።

8 እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣

ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣

9 ተራሮችና ኰረብቶች ሁሉ፣

የፍሬ ዛፎችና ዝግቦች ሁሉ፣

10 የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት ሁሉ፣

በምድር የሚሳቡ ፍጥረታትና የሚበሩ ወፎችም፣

11 የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ፣

መሳፍንትና የምድር ገዦች ሁሉ፣

12 ወጣት ወንዶችና ደናግል፣

አረጋውያንና ልጆች ያመስግኑት።

13 ስሙ ብቻውን ከፍ ያለ ነውና፣

ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ነውና፣

እነዚህ ሁሉየእግዚአብሔርንስም ያመስግኑ።

14 እርሱ ለሕዝቡ ቀንድንአስነሥቶአል፤

ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣

እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ፣ ለእስራኤል ልጆች።

ሃሌ ሉያ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *