በእግዚአብሔር መታመን
የዳዊት መዝሙረ መዓርግ
1 እግዚአብሔርሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤
ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤
ሐሳቤ ለዐጒል ትልቅነት አልተነሣሣም፤
ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም።
2 ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሰኘኋት፤
ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣
ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች።
3 እስራኤል ሆይ፤ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣
በእግዚአብሔርተስፋ አድርግ።