መዝሙር 130

ለርዳታ የቀረበ ጥሪ

መዝሙረ መዓርግ

1 እግዚአብሔርሆይ፤ ከጥልቅ ወደ አንተ እጮኻለሁ።

2 ጌታ ሆይ፤ ድምፄን ስማ፤

ጆሮዎችህ የልመናዬን ቃል፣

የሚያዳምጡ ይሁኑ።

3 እግዚአብሔርሆይ፤ ኀጢአትን ብትቈጣጠር፣

ጌታ ሆይ፤ ማን ሊቆም ይችላል?

4 ነገር ግን በአንተ ዘንድ ይቅርታ አለ፤

ስለዚህም ልትፈራ ይገባሃል።

5 እግዚአብሔርንደጅ እጠናለሁ፤ ነፍሴም በትዕግሥት ትጠብቀዋለች፤

በቃሉም ተስፋ አደርጋለሁ።

6 ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣

አዎን፤ ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣

ነፍሴ ጌታን ትጠባበቃለች።

7 በእግዚአብሔርዘንድ ምሕረት፣

በእርሱም ዘንድ ማዳን አለና፣

እስራኤል ሆይ፤በእግዚአብሔርተስፋ አድርግ።

8 እርሱም እስራኤልን፣

ከኀጢአቱ ሁሉ ያድነዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *