የስደት ተመላሾች መዝሙር
መዝሙረ መዓርግ
1 እግዚአብሔርየጽዮንን ምርኮበመለሰጊዜ፣
ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም።
2 በዚያን ጊዜ አፋችን በሣቅ፣
እንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤
በዚያን ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣
“እግዚአብሔርታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።
3 እግዚአብሔርታላቅ ነገር አደረገልን፤
እኛም ደስ አለን።
4 እግዚአብሔርሆይ፤ በነጌቭ እንዳሉ ጅረቶች፣
ምርኳችንን መልስ።
5 በእንባ የሚዘሩ፣
በእልልታ ያጭዳሉ።
6 ዘር ቋጥረው፣
እያለቀሱ የተሰማሩ፣
ነዶአቸውን ተሸክመው፣
እልል እያሉ ይመለሳሉ።